የአርበኞች ግንቦት 7 አላማን በመቀበል በቃፍታ ሁመራ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ከሰኔ 25/2007 እስከ ሰኔ 28/2007 ዓም ከትግራይ ክልል ሚሊሻ፣ ከትግራይ ክልል ልዩ ኃይልና መከላከያ ጋር ውጊያ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳይ አድርሰዋል የተባሉ 14 ግለሰቦች ከ 15 አመት እስከ ሞት በሚያስቃጣ ከባድ ድንጋጌ ስር እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል።

በእነ ገብሬ ንጉሴ ክስ መዝገብ ተከሰው የተበየነባቸው ገብሬ ንጉሴ፣ አገናኝ ካሱ፣ ስማቸው አምበሉ፣ ባባዬ አዛናው፣ አስቻለው ክፍሌ፣ ደሴ ክንዴ፣ ክብረት አያሌው፣ ብርሃን ዳርጌ፣ አወቀ መኮንን፣ አበረ ፋንታሁን፣ሻንቆ ብርሃኑ፣ ጌትነት ዘሌ፣ ተሻገር መስፍን እና ሰጤ ጎባለ ናቸው።

ተከሳሾቹ 4 የሰራዊት አባላት እንደገደሉ እና 10 የሰራዊት አባላትን እንዳቆሰሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በብይኑ ገልፆአል። ከተበየነባቸው መካከል አገናኝ ካሱ፣ ስማቸው አምበሉ፣ ባባዬ አዛናው፣ አስቻለው ክፍሌ፣ ደሴ ክንዴ፣ ክብረት አያሌው፣ ብርሃን ዳርጌ፣ አወቀ መኮንንና አበረ ፋንታሁን አንከላከልም በማለታቸው ለፍርድ ለጥር 17፣ እንዲሁም እንከላከላለን ያሉት ገብሬ ንጉሴ፣ ሻንቆ ብርሃኑ፣ ጌትነት ዘሌ፣ ተሻገር መስፍን እና ሰጤ ጎባለ ምስክር እንዲያቀርቡ ለየካቲት 8/2010 ቀጠሮ ተይዟል።’

(በጌታቸው ሺፈራው)

Related stories   በእነ ጃዋር የህክምና ጥያቄ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሁሉንም ተከራካሪዎች ጥያቄ ውድቅ አደረገ፤ ቃሊቲ ሆነው ይታከማሉ፤

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *