ሶስት ወር ግድም ሲሟገትና የ ” ሰላ” በተባለ ቃላት ሲገራረፍ የከረመው የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የክልሉን መሪ አባይ ወልዱን ” ብቃት የለህም” በሚል ማንሳቱ በታወጀ ሳምንታት ውስጥ ኢትዮጵያ አምባሳደር አድርጋ ለዲፕሎማሲያዊ ስራ እንደሾመቻቸው ተገለጸ። ሹመቱን አስመልክቶ በማህበራዊ ገጾች በምክንያት የታጀቡ ትችቶች እየቀረበ ነው።

የጠነከረ ጹሁፍ በመጻፍ የሚታወቀው አቻሜለህ ታምሩ ” … የኢትዮጵያ አምባሳደር ለመሆን መስፈርቱ በተመደቡበት የስራ ዘርፍ በብቃት ማነስ ተገምግሞ ከኃላፊነት መወገድ ሆኗል” ሲል ግራሞቱን በፌስቡክ ገጹ አስፍሯል። 

አቶ ሰማኽኝ ጋሹ በበኩሉ ” ዲፕሎማሲያችን አንድ ቁልፍ ሰው ተጨመረለት” ሲል በግል የፌስ ቡክ ገጹ አስተያየቱን ገልጿል። በርካቶች ደግሞ ” አምባሳደር ለመሆን መስፈርቱ ምንድን ነው” በሚል ጥያቄያቸውን ግራ በመጋባት ገልጸዋል።

በተደጋጋሚ እንደታየው በህወሃት ውስጥ አምባሳደርነት የማግለያና የካሳ ጉዳይ ተደርጎ እንደሚወሰድም የጠቀሱ አሉ። በከፋና በጠነከሩ ቃላቶች ስሜታቸውን የገለጹም አሉ። በብቃት ማነስና በጥፋት የተገመገሙ ሰዎችን በዲፕሎማሲ ስራ ማሰማራት ምን አልባትም ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚከናወን ስለመሆኑ ስጋት እንዳላቸው የጠቀሱ ቀሪው ጊዜ ለአምባሳደር አባይ ወልዱ የተሳካና የመልካም እረፍት እንዲሆን በምጸት ተመኝተዋል። ” አጥፉና በግምገማ ተባረሩ። ከዛም አምባሳደር ትሆናላችሁ” ሲልም የተሳለቀ አለ። 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *