የህወሃት ደጋፊዎችም ሆኑ ተቃዋሚዎች፣ ራሱ ህወሃት፣ የክልሉ አስተዳደር፣ የቀበሌና የዞን መሪዎች፣ የቤትክርስቲያን አለቆች፣ ትንሽ ትልቅ፣ ሳይል በወልደያ የደረሰውን አይተናል። አይተዋል። በወልደያ እናቶች ” እንጀራ ሸጠን አሳድገን… ቆሎ ቸርችረን አሳድገን… ማን ልጅ ያልሞተበት አለ?” እያሉ ደርታቸውን በመድቃት ሲያለቅሱ በአይን ብረታችን አይተናል። ዛሬ ድብቅ ነገር የለምና መረጃው ሁልም ዘንድ አለ። የተገደሉትን ውድ ልጆች በደም ተነክረው እንደወደቁ መካድና ማስተባበል በማይቻልበት ደረጃ እያመመን አይተናል። ምስሉን መለጠፉ ምን ያህል ሰነ ምግባራዊ እንደሆነ ቢያነጋግርም የታየው ሁሉ የሆነ ነው። ይህ ድርጊት የሚያስደስተው አካል አውሬ ብቻ ነው። በደም የሚረኩ እርኩሶች ብቻ ናቸው። ይህንን ሁሉ እያየን በጭፍን ጥላቻና በጭፍን ድጋፍ የሚሰጠው አስተያይተም ሆነ መረጃ ሃዘኑንን ያብሰዋል። ያሳፍራልም። ያናድዳልም። በዚህች አገር ሰው መግደል የሚቆመውስ መቼ ነው?

የሚያስጨንቀንና የሚያሳስበን ይህ ቂም እያስቋጠረ ያለው ግድያና እስር፣ ስቃይና የፍትህ መዛባት እንዴት ይቁም የሚለው ሆኖ ሳለ፣ በምስኪን ወገኖች ህይወት ተራ የልወደድ ባይ ፖለቲካ መቆመር እጅግ ህሊና ማጣት ይሆናል። ከሰውነትም ተራ መራቅና ሉሲፈርን የመሆንም ያህል ነው። በማህበራዊ ገጾች እገሌ ከእገሌ ሳይባል ተሳደቡ፣ ድንጋይ ወረወሩ፣ የጀመሩት እነሱ ናቸው፣ ፖለቲካኛች ናቸው፣ መመሪያ የተሰጣቸው ናቸው… ወዘተ የሚሉ ጽሁፎች ” ባገኘነው መረጃ” በሚል ናኝተዋል። እናም ወላድ ስታነባ፣ አገር ሲያነባ ከወዲህ ማዶ የሞላላቸው የፖለቲካ አታሞ ይመታሉ።

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

ዛሬ ላይ ማንም ይሁን ማን ቢያንስ የሚያዝን ልብ ከሌለ ዝምታን የሚመርጥበት ወቅት በሆነ ነበር። ጎረምሶች ለዛሬ ተሳድበውና አውግዘው ወደ ቤታቸው ቢገቡ ምን አለበት? ሲሳደቡ ቢውሉ ምን ችግር አለው። ለመቃውምና ቅሬታን ለመግለጽ መሰብሰብና መሰለፍ ከተከለከለ ሰዎ የት ይተንፍስ? መቼ ነው ወደ ህሊናቸን የምንመለሰው? ጥፋትም ሆኖ ከተወሰደ ግድያን ምን አመጣው? አልሞ መግደልን ለምን? የሰው ልጅ እንደ ምናምን እየተደፋ እስከመቼ ይቀጥላል። ደምስ ሲበዛ ደግ ነው?

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

ሕዝብ እንደተቆጣና ንብረት እንዳወደመ፣ ያወደመውም ንብረት ደግሞ በተወሰኑ ላይ ማተኮሩ አሁን የት ለመድረስ እየተጣደፍን እንደሆነ ያሳያል። ይህ አሳሳቢ በሽታ እንዳይበላን የተበላሸውን ማቃናት ሲገባ እንደገና ደም? በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ እናቶች ምን እያሉ እንደሚያለቅሱ አድምጡ። ከዚህ በላይ መልዕክት የለም። ብሶት ሁሌም ጀግኖችን ይወልዳል። የከፋቸው ሁሉ ጀግና ይሆናሉ። አሁን እየሆነ ያለው ህዝብን ” ተነስና ተገዳደል፣ መሳሪያ የሌለህ በጥርስ ተጫረስ” የሚሉት አይነት ይመስላል።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

የሰው ይህወት ጠፋ፣ አገር ሃዘን ተቀመጠች፣ ንብረት ወደመ፤ ነገስ? እንደሚሰማው ከሆነ ችግሩ አድማሱን እያሰፋ ነው። ወዴት እያመራን ይሆን? ከሰባት በላይ ተገለዋል። ሲል አማራ ክልል አስታውቋል። ሌሎች የሟቾች ቁጥር ከፍ እነደሚል እየተናገሩ ነው። የአማራ ክልል ሊቀመንበር እስፍራው ሄደው ለማረጋጋት ሞክረው ባይሳካላቸውም በህዝብ ጥያቄ እስረኞቸንዲፈቱ ማዘዛቸውን አንድ የአይን ምስክር ለቪኦኤ ሲናገሩ ተደምጧል ። እኙሁ ሰው እንዳሉት ህዝቡም እስር ቤት ሰብሮ እስረኞችን አስፈትቷል። የግጭቱ መጠን ሰፍቶ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል። ተሽከርካሪ ነዷል። የነዳጅ ቦቴ ወድሟል።

ስማቸው የተጠቀሱ ሆቴሎችና የንግድ ተቋማት ጋይተዋል። ወልደያ በቃጠሎ ጭስና በሃዝን ተመታለች። አሁን ድረስ ድባቡ የስጋት እንደሆነ የሞናገሩ አሉ።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *