መማር ቢፈለግ በኢሬቻ በዓል ላይ ከደረሰው መማር በተቻለ ነበር። ለዜጎች ልዩ ክብር ቢሰጥ በጨለንቆ የተፈጸመው ግድያ የመጨረሻ ተሞክሮ በሆነ ነበር። አሁን አሁን ተኩሶ መግደል የተወሰኑ ሃይሎች ልዩ መብት ሆኗል። አልቅሶ መቅበር እስከመከልከል ደርሷል። አስከሬን ተሸክመው ለቀብር በወጡ ላይ አስለቃሽ ጋዝ ማፈንዳት የግፍ ጽዋ መሙላቱን የሚያሳይ ነው። ጽላት ስር መርዝ መርጨት ማንም ያድርገው ማን በእብሪት መነፋትና በግፍ የመደንደን ውጤት ነው። ሁሉም እናቶች ዘጠኝ ወር በሆዳቸው ተሸከመው፣ አምጠው ወልደው ፣መከራ በልተው ነው ያሳደጉት። ማንም ልዩ የለም። ደም ክፉ ነው። ከደም አዙሪት ካልወጣን ዋ!! 

“መከላከያ ሰራዊት ወልድያ እንዲገባ ፈቃድ አልተሰጠሁም” አቶ ገዱ “ግድያው ሆን ተብሎ የተፈጸመ ቂም በቀል ነው “ነዋሪዎች

በወልደያ “ለትግራይ መጸዋ!!” የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ወደ ስፍራው ያቀኑት የክልሉ ሊቀመንበር አቶ ገዱ ንጹሃን ላይ ግድያ የፈጸመው የአጋዚ ሰራዊት ወደ ክልሉ እንዲገባ ፈቃድም ሆነ ይሁንታ አለመስጠታቸውን ፣ በጉዳዩ ላይ ምንም መረጃም እንደሌላቸው መናገራቸው ተሰማ። የግድያው መነሻ ቂም በቀል መሆኑን ነዋሪዎች አስታወቁ፤ የአቶ ገዱ ቃል እስካሁን አንዳልተከበረና የአጋዚ ሰራዊት ከከተማዋና አካባቢዋ አለመውጣቱ ተጠቆመ። የአማራ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አንጻራዊ ሰላም እየታየ ነው ይላሉ። የትግራይ ተወላጆች ንብረት ወድሟል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በመሩት ህዝብን የማረጋጋት ስብሰባዎች ላይ የታየው ስሜት እጅግ የጎሸ ነበር። ሕዝብ ምሬቱንና ቁጣውን የገለጸው ከወትሮው በተለየ እጅግ የከፋና ህሊናን በሚፈታተኑ ቃላቶች ሲሆን ” አለንበት ድረስ መጥተው ይጨፈጭፉናል ” ሲሉም ብሄር በመጥራት ተናግረዋል። ” ለምንና ምን ፍለጋ መጡ? አይድረሱብን ” ሲሉ በጩኸት ማስተጋባታቸው ለዛጎል መልዕክት ደርሷል።

በዚህን መሰሉ ስብሰባ ላይ አቶ ገዱ ” መከላከያ ወደ ወልዲያ እንዲገባ አልፈቀድኩም፤ አላውቅም” ሲሉ ለሕዝብ ይፋ አድርገዋል። የጥምቀትም ይሁን የተለያዩ ሃይማኖታዊ በዓላት በመትረየስ ታጅቦ ሲከበር አይተው እንደማያውቁ ያመለከቱ አስተያየት ሰጪዎች ድርጊቱን በኳስ ከተነሳው ግጭት ጋር ያያዙታል። ” ቂም ነው” ሲሉ ሆን ብሎ የተፈጸመ ስለመሆኑም የድርጊቱን አፈጻጸም በማስረዳት ያሳያሉ። ይሞግታሉ።

ከክልሉ እውቅና ውጪ በጨለንቆ የደረሰውን የጅምላ ግድያ አደባባይ ወጥተው ያወገዙት አቶ ለማ መገርሳን ያስታወሱ እንዳሉት፣ አቶ ገዱም ህዝብ እንዲረጋጋ በስፍራው ተገኝተው ያከናወኑት ተግባር የሚመሰገን ቢሆንም፤ እንደ ክልል መሪ ድርጊቱን በአደባባይ በማውገዝ አቶ ለማን ሊሆን እንደሚገባ ይጠቁማሉ። እሳቸውም ብቻ ሳይሆኑ የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ንጉሱ የተውተፈተፈ ሃረግ ሞንጭረው በፌስ ቡክ ገጻቸው ከሚለጥፉት በዘለለ አቋም የያዘ ነገር አለመናገራቸው እያስወቀሳቸው ነው።

አቶ ገዱ በሚዲያ ወጥተው ባይናገሩም በሰበሰቡት ሕዝብ መነሻ ጥያቄ የአጋዚ ሰራዊት ከተማዋን ለቆ እንደሚወጣ አረጋግጠዋል። ቪኦኤ አማርኛ እንደዘገበው እሳቸው ይህንን ቢሉም እንደውም ተጨማሪ ሃይል እንደገባና መትረየስ ደግኖ ከተማዋ ውስጥ እንደሚመላለስ ነው የተገለጸው። በድምጽ አስተያየት የሰጡ እንዳሉት የክልሉ ፖሊስም ሆነ የጽጥታ መዋቅር ህዝብ ላይ አልተኮሰም። የተኮሱትና ” ጨፈጨፉን” የተባሉት ስም ተጠቅሶ የአንድ ብሄር አባላት አንጋቾች እንደሆኑ ተጠቁሟል። በከፋ ምስል ሰይሞ ድርጊቱን የገለጸው የቪኦኤ እማኝ በቀጣዩ ቀን የብሄር ግጭት መታየቱን አመልክቷል።

weledeya 2

“ማሰብ የሚችሉ የሰራዊት አመራሮች ታቦት ዘንድ አስለቃሽ ጋዝ አይተኩሱም” ሲል ለጎልጉል መረጃ የላከ የወልደያ ነዋሪ “ካሁን በሁዋላ ወልዲያ ላይ ተቻችሎ መኖር ያከተመ እንደሆነ ለአቶ ገዱ ተነግራቸዋል። ሕዝቡም እየመረጠ ንብረት በማውደም ይህንኑ አሳይቷል” አስተያየት ሰጪው ካለው ጋር በተመሳሳይ በስፋት በማህበራዊ ገጾች እንዲሁም በቪኦኤና በተለያዩ ሚዲያዎች የሚወጡት መረጃዎች ይህንኑ ያመላክታሉ።

ለቪኦኤ መረጃ የሰጠ የአይን እማኝ እንደሚለው  ሃሙስ ታቦት ወደ ማደሪያው አድርሰው በሚመለሱ ላይ እና መንገድ ላይ በነበሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ድብደባ ይፈጸም ነበር። በበነጋው አርብ እነፍናለን አትዘፍኑም ንትርክ መሳሪያ ተመዘዘ። ነብስ ጠፋ። አማራ ክልል እንዳለው ሰባት ሲሞቱ፣ ከአስራ ዘጠኝ በላይ ቆስለዋል። /የሟቾች ቁጥርና የቆሰሉት ወገኖች ብዛት እንደሚጨምር እየተጠቆመ ነው/ እማኙ እንዳለው ጉዳዩ እዚህ ሳይደርስ በእንጭጩ ሊገታ ይችል ነበር። አሁን ነገሮች ተበላሽተዋል። ሁለቱ ለዘመናት አብረው የኖሩ ህዝቦች ላይስማሙ ተለያይተዋል። 

የሁለቱ ህዝቦች መለያየት እና “አትደረሱብኝ” በሚል በር ቀርቅሮ መቀመጥ የማይቻል እንደሆነ ከመካምድራዊ ጠቃሚነት አንጻርም የሚያዩት አሉ። ወልድያ ለትግራይ ቁልፍ ምድር መሆኗን የሚናገሩ፣ ትግራይ ወደ በርካታ የአገሪቱ ክልልሎች ለመድረስ መውጪያ መግቢያዋ ወልድያ ናት። በኖርዌይ ነዋሪ የሆኑት ልጅ ግሩም በፌስ ቡክ ገጻቸው ይህንን አስፈረዋል

ልጅ ግሩም  ወልድያ ቁልፍ የህዋሃት ከተማ ሆናለች። ከሃያ አምታት በፊት የነበረው ትግሪኛ ተናጋሪ ለቁጥር የሚገባ አልነበረም። በሺዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎችና ደህንነትም ሆነው የሚሰሩ የህዋሃት ሰዎች ሰፍረውባታል። የትግራይ ነፃ አውጪ ነጋዴዎች ከመቀሌ ወደ ምስራቅ በአፋር ወደ ጅቡቲ ወደብ፤ የኤፈርትን ምርት ኤክስፖርት የሚያደርጉበት፣ ወደ ምዕራብ ንፋስ መውጫ፣ ወደ ጎጃም የሚጓዙበትና ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ለመመላለስ ማቋረጥ ያለባቸው ወልድያ ከተማን ነው። ለወያኔ ወልድያ ማለት ግብፅ ለአባይ የምትሰጠው ዋጋን ይተካከላል። ትግራይን ከመሃል አገር የሚያገናኘው መተላለፊያቸው ቁልፍ የኤኮኖሚ አውታር ከተማ ወልድያ …ምን ማድረግ ይቻላል?  ሲል ወልድያና ለትግራይ ቁልፍ ከተማ መሆኗን ይጠቁማል።

No automatic alt text available.

አቶ ንጉሱ ለቪኦኤ ሲናገሩ ጥፋቱ ያደረሰውን አካል “የጽጥታ መዋቅሩ”  ነው የሚሉት። አጋዚ ወይም መከላከያ አላሉም። ይሁን እንጂ ሁሉም ከስሩ ተጣርቶ ርምጃ እንደሚወሰድና ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ከስምምነት ላይ መደረሱን ነው ያስታወቁት። አክለውም ” የዘጋችሁትን መንገድ ክፈቱ” ሲሉ አቶ ገዱ መናገራቸውን ጠቁመዋል። ሕዝብ ለአቶ ገዱ “የራሳችንን ሰላም ራሳችን እናስጠብቃለን። የማንንም ጣልቃ ገብነት አንፈልግም” ማለቱን አስታውቀዋል። 

አንጻራዊ መረጋጋት መታየቱን አቶ ንጉሱ አስታውቀዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት አሁንም ችግር አለ። በከተማዋ የሚኖሩ የትግራይ ነዋሪዎች ንብረት ወድሟል። አሁንም እርምጃ እየተወሰደ ነው። በከተማዋ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች መኖራቸውን፣ አብዛኞቹ በንግድ ስራ ተሳታፊ መሆናቸውን የሚናገሩት ክፍሎች ደግሞ እነዚሁኑ ወገኖች ለመጠበቅ ሲባል የአጋዚ ሰራዊት ወልድያን እንደማይለቅ አመላክተዋል።

” …..መማር ቢፈለግ በኢሬቻ በዓል ላይ ከደረሰው መማር በተቻለ ነበር። ለዜጎች ልዩ ክብር ቢሰጥ በጨለንቆ የተፈጸመው ግድያ የመጨረሻ ተሞክሮ በሆነ ነበር። አሁን አሁን ተኩሶ መግደል የተወሰኑ ሃይሎች ልዩ መብት ሆኗል። አልቅሶ መቅበር እስከመከልከል ደርሷል። አስከሬን ተሸክመው ለቀብር በወጡ ላይ አስለቃሽ ጋዝ ማፈንዳት የግፍ ጽዋ መሙላቱን የሚያሳይ ነው። ጽላት ስር መርዝ መርጨት ማንም ያድርገው ማን በእብሪት መነፋትና በግፍ የመደንደን ውጤት ነው። ሁሉም እናቶች ዘጠኝ ወር በሆዳቸው ተሸከመው፣ አምጠው ወልደው ፣መከራ በልተው ነው ያሳደጉት። ማንም ልዩ የለም። ደም ክፉ ነው። ከደም አዙሪት ካልወጣን ዋ!! …..” የሚል አስተያየተ የላኩልን የዛጎል ተከታትይ ሁሉም ወገኖች ከስሜትና ከተራ የጥጋብ ስሜት ሊወጡ እንደሚገባ መክረዋል።

አሮማራ በቅርቡ መሰማት የጀመረው የኦሮሞና አማራ ህበረት መሆኑ የነገራል። ይህ ህብረት እንዴት እንደሚሰራና የስምምነቱ ስፋት ይፋ አይደለም። ሆኖም ግን ምሬት እንዳጋመዳቸው ነው የሚጠቆመው። ይህ ሕብረት ህወሃትና የህወሃት ደጋፊ የሚባሉትን በሙሉ ለሚደርሰው ማናቸውም ጥፋቶች ተጠያቂ ያደርጋል። አሁን እየተካረረ በሄደው የህዝብ አመጽና የኢህአዴግ ተሀድሶ መካከል ልዩነቱ እየሰፋ በመሄዱ የትግሬና የኦሮማራ መጨረሻ ምን ይሆን? የሚለው ጉዳይ በስጋትም ይሁን “ራስን ከማዳን” አንጻር ትልቁ የውስጥ ለውስጥ ስራ ሆኗል።

 

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *