ከአራት አመታት በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው የሆነው የሙዚቃ ድግሴ እጅግ ባማረ መልኩ ተጠናቋል ።
የባህርዳር ህዝብ ወደ ከተማዋ ስገባ ካደረገልኝ አቀባበል ጀምሮ በነበረኝ ቆይታ ባሳዩኝ ፍቅርና ክብር እንዲሁም በተደረገልኝ መስተንግዶ ልቤ ተነክቷል- እወዳችዋለሁ ! የዝግጅቱ ዕለት ስቴዲየም ተገኝታችሁ የታደማችሁ በሙሉ በተለይም ደግሞ ከሩቅ አካባቢዎች ከአራቱም ማዕዘን መጥታችሁ ዝግጅቱን ለተካፈላችሁ ሁሉ ምስጋናዬና ፍቅሬ ከልብ ነው።
የሙዚቃ ስራዎቼን ማቅረብ ከጀመርኩ ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የማይገባኝን ሁሉ እንዳደረገልኝ በድጋሚ በመመስከር ሁሌም በፍፁም ታማኝነት እናንተን እንደማገለግል ሳረጋግጥ በታላቅ ኩራት ነው።
እግዜር ያክብርልኝ !
አመሰግናለሁ ባህር ዳር !
አመሰግናለሁ ኢትዮጵያ !
Related stories The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam
Powered by Inline Related Posts
ቴዲ አፍሮ (ቴዎድሮስ ካሳሁን)