አዲስና ከዚህ ቀደም ያልተገለጸ ወይም ከአድማጩ አውቀትና መረጃ ሻል ያለ አዲስ ነገር ምንድን ነው? ይዘው የቀረቡት የየራሳቸው ጥናትና ምርምር የታል? ዳታውና ትንተናው የታል? የችግሮቻችንን ምክነያት ተመራማሪዎቻችን አንጥረው ይዘው የሚያቀርቡልን መቼ ነው? ምርምሮቻቸውና ጥናቶቻቸው የታሉ? በፖሊሲዎቻችን ላይ ያሉ ግድፈቶቻችንን ፈትሸውት አብጥርጥረው እንደ ልሂቅ የሚያመላክቱን በምን ዓይነቱ መድረክ ይሆን? እንደው ኢኤንኤንን እመለክት ስለነበር ይህን ጻፍኩ እንጂ በሁሉም ሚዲያዎች ላይ የሚታይ ገደል የሚያህል ስንኩልነት ነው፡፡

Kalkidan Ambachew  – ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ ሶስት ተመራማሪዎች እና አንድ ደራሲ ከኢኤንኤን አወየያይ ጋር በጥቅሉ አሁን አገራችን ስለተዘፈቀችበት ችግር እና መውጫ መንገዱን፤ ስለ ብሔረተኝነት እና የጎሳ ፖለቲካ፤ ማንነት እና ባህል ስብጥር እንዲሁም ሃገራዊ ተቋማቶቻችን እየገጠማቸው ስላለው ቅቡልነትን የማጣት ችግር እና ሌሎችንም በርካታ ጉዳዮች አንስተው ሲወያዩ ነበር፡፡ ውይይቱ ጥሩ ጎኖች የነበሩት ሲሆን ያሉኝን ግርታዎችና ምልከታዎች ማንሳት ፈለኩ —
1ኛ – አንደኛው ተወያይ ከስሙ ስር የተሰጠው ማዕረግ ወይንም ሙያ አሊያም ዘርፍ እንበለው “ደራሲ” የሚል ነው፡፡ እንዲህ ባለ ውይይት ላይ ትንታኔን እና ምሁራዊ አሊያም ምርምራዊና ሊህቅ ሃሳብ የሰጥልናል ብለን የጋበዝነው ሰው “ደራሲ” ብለን ብቻ ማቅረባችን አያደናግርም፡፡ ስለልብ ህመም የሚያማክረኝ ሃኪም በደፈናው ሃኪም ተብሎ ሳይሆን የልብ እንጂ የአጥንት እስፔሻሊስት ብቻ አለመሆኑን ማወቅ ይገባኛል፡፡ በእነዚህ ጥልቅ ውይቶች ላይ የቀረበውም “ደራሲ” የምን መጻህፍ “ደራሲ” ይሆን? ምን ጻፈ? የሚለውን ብናውቅ የሚያቀርብልንን ትንታኔዎች የምንመዝንበትን ማዕቀፍ ይፈጥርልናል፡፡ ለምሳሌ ሌሎቹ በድፍን “ተመራማሪ” ተብለው አልቀረቡም፡፡ ይልቁንም የታሪክ እና የማህበረሰብ ተመራማሪ፡ የፌደራሊዝም ተመራማሪ፡ የፎልክሎር ተመራማሪ በሚል ቀርበዋል፡፡ የቶም ኤንድ ጄሪን የህጻናት መጻህፍ ተርጓሚ ቢሉን እና ባለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙርያ መጻህፍት የጻፉ ቢሉን አስተያየቱን የምናይበት መነጽር ለየቅል ስለሚሆን፡፡
2ኛ – አንድ ጊዜ ደረጄ በላይነህ አንድ ፊልም ላይ የሠራ ወይም በሆነ ማስታወቂያ ላይ ብቅ ብሎ የታየ በማግስቱ የኢትዮጵያን ህዝብ መካሪ ሆኖ በሚድያ የሚቀርብበት አጋጣሚ እንዳለ የሚመስል ሃሳብ በፌስቡክ ሼር ያደረገን ይመስለኛል፡፡ ተመራማሪ መብዛቱ ባይጠላም ለመሆኑ ተመራማሪ የሚለው ታይትል የሚሰጠው እንዴት ነው? ሚድያው ይሆን ሰያሚ? ተቋማት ይሆኑ የሚሰጡት? ወይንስ ግለሰቡ ያከናወነወን እና እያከናወነ ያለውን ጥናትና ምርምር በራሱ ከግምት በማስገባት “ተመራማሪ” ነኝ ብሎ የሚወስደው ስያሜ ይሆን? ወይንስ በሃገርም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ቅቡልነት ባገኙ ጆርናሎች ላይ ምርምሮቻቸውን ባሳተማቸው ያገኙት ይሆን? የጻፏቸውና ያሳተሟቸው መጻህፍትስ ለዚህ ያበቁ ይሆን? ለማንኛውም ቢገለጽ፡ ቢብራራና ቢታወቅ ይጠቅም እንጂ አይጎዳም፡፡ ብዥታን ከመቀነሱም በላይ የሆነውንና ያልሆነውን ለመለየትም ይረዳል፡፡ በነገራችን ላይ ይገለጽ፡ ብናውቀው የውይይቱን ዳራና አመንክዮ ለማሰናሰል ይጠቅመናል ብዬ እንጂ አነሰባቸው፡ በዛባቸው የሚለው ልኬት ውስጥ አልገባሁም፡፡ እዮብ ምህረተ አብ አደራ በሚቀጥለው የማህበራዊ ሚድያ ተመራማሪ ተብለህ በቴሌቨዥን ከተፍ እንዳትልብን፡፡ “የቼ በለው” ምርጥ መጽሀፍ ደራሲ ተብለህ በፌስ ቡክ ቀደዳና በከተማ ፉገራዎች ዙርያ ፍተላህን ለማስማት ግን ተሸቀዳዳሚ ንኝ ——-
3ኛ – አሁንም ውይይቱ በጎ ጎኖች እንዳሉት እየጠቀስኩ ነገር ግን ተወያዮቹ የነገሩን፤ የተነተኑልን፡ ያመሰጠሩልን አዲስና ከዚህ ቀደም ያልተገለጸ ወይም ከአድማጩ አውቀትና መረጃ ሻል ያለ አዲስ ነገር ምንድን ነው? ይዘው የቀረቡት የየራሳቸው ጥናትና ምርምር የታል? ዳታውና ትንተናው የታል? የችግሮቻችንን ምክነያት ተመራማሪዎቻችን አንጥረው ይዘው የሚያቀርቡልን መቼ ነው? ምርምሮቻቸውና ጥናቶቻቸው የታሉ? በፖሊሲዎቻችን ላይ ያሉ ግድፈቶቻችንን ፈትሸውት አብጥርጥረው እንደ ልሂቅ የሚያመላክቱን በምን ዓይነቱ መድረክ ይሆን? እንደው ኢኤንኤንን እመለክት ስለነበር ይህን ጻፍኩ እንጂ በሁሉም ሚዲያዎች ላይ የሚታይ ገደል የሚያህል ስንኩልነት ነው፡፡ ሰው ሬድዮ ላይ ይወጣል በዚህ ጉዳይ ላይ ምሁራዊ ዕይታ ይሰጣል ይባላል አንድም የራሱ ጥናትና ምርምር፤ የሰበሰበውና የተነተነው ዳታ፤ ወይም በእኛ ዐውድ የሆነ ሳይንሳዊ ምልከታ፤ አሊያም የተደራጀና አመንክዮ ያለው የራሱ ኦፒኒየን ሳያቀርብ ምሁሩ እንዲሁ አውርቶ የሚሄድበት አጋጣሚ በርክቷል፡፡ ሚድያዎቻችን ይህንንም መድረክ ስለፈጠሩልን ብናመሰግንም ተመራማሪዎቻችን እና ምሁራኖቻችንን ከዚህም ላቅ ባለ በጥናትና በዳታ ላይ የተመሠረተ ውይይት እንዲፈጥሩልን ቢያመቻቹ—–

አስተያየቱ የተወሰደው ከቃል ኪዳን አምባቸው የፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ ነው

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *