አገሩ በሙሉ በባንዲራ አሸብርቋል። ከበሮ ይደለቃል። ለቁጥር የምታክቱ ሃውልቶች የሚፈስባቸው ብርሃን ያጥበረብራል። መኪኖች ጥሩምባ እየነፉ ይከንፋሉ። ሁሉም ዘንድ ” ደርብ” ይጨፈራል። ሁሉም መንደር ስካር ሆኗል። ቀይ፣ ቢጫና፣ በውል የማይለይ ቀለም የለበሱ ሕጻናት በሰልፍ ይተማሉ። “በታላቁ” መሪ ሃውልት አናት ላይ የሚንቀለቀል እሳት ይነዳል። የሃውልቱ ቁመት ትልቅ በመሆኑ ለሁሉም ይታያል። ከሃውልቱ ግርጌ ” እድሜ ላንተ” የሚል ክታብ ብልጭ ድርግም ይላል። የሱዳን ባንዲራ መንገዱን ሞልቶታል። ጀለቢያ የለበሱ የሱዳን ሰዎችም ያወካሉ። 

የታላቋ ትግራይ ምስረታ እውን ሊሆን ተቃርቧል። ለተሰበሰበው ህዝብ ንግግር የሚያደርጉት ሰው እየተጠበቁ ነው። ፌሽታው ቀልጧል። ለሪፐብሊኩ ምስረታ የተጉ ስማቸው በትልቁ ሃውልት ስር ሰፍሯል። ግራ የተጋቡ አይታዩም። ገራ የሚያጋቡ ግን ስፍር ናቸው። ትግራይ ለትሰናበት ነው። ትግራይን የሚያሰናበታት ምክንያት በውል አልታወቀም። አድሮ ካልሆነ የሚገባቸው ያሉም አይመስሉም። ትግራይ፣ ትግራዋይ፣ ታላቋ የአፍሪቃ አብሪ ኮከብ… 

ተናጋሪው በባለ ቀስቱ ባንዲራ ታጅበው መድረክ ላይ ወጡ። እልልታው ቀለጠ። አስተጋባ። የእልልታው ድምጽ ምጽዋ ድረስ ይሰማል። የምጽዋ ነዋሪዎች ይሰማሉ። ተናጋሪው ” እንኳን ለዚህ ቀን አበቃችሁ፣ አበቃን” ሲሉ ጩኸቱ ጋለ። የኦሮሚያ ተወካዮች የሉም። ከአማራ ክልል እግረ ጠባብ የለበሱ ሶስት አሉ። ሃይለማሪያም ኩታ ለብሰው ይገልፍጣሉ። የሶማሌ ክልል መሪ ንግግሩን አይሰሙም። ይጨፍራሉ። አንዳንዴም ተንበርክከው እስክስታ ይላሉ። ሊሎቹ በውል አይታወቁም። የሱዳን ሊቀመንበር ወርቅ ላይ ተቀምተዋል። ያበራሉ። አምላክ ሆነው ታይተዋል። ኢሳያስ የጥሪ ድብዳቤ ቢደርሳቸውም …..

ተናጋሪው ቀጠሉ ” ዛሬ አገር ሆን” ሲሉ አወጁ። ፈንዲሻ ተበተነ። ተጮኸ። እልልታው አሁን የመን ድረስ ደረሰ። ከየመንም አለፈ። ድንበር ላይ ያለው ሰራዊት ግን አይሰማውም። ተናጋሪው ቀጠሉ ” ዛሬ ስማችን ተቀየረ። ነጻ ወጣን። ታላቅ ነበርን፣ ተመልሰን ታላቅ ሆን!!” ህዝብ አበደ። አወካ። እልልታው ቀይ ባህርን ተሻገረ። ” የአፍሪካ እስራኤል ነን” ሲሉ ዙሪያቸውን የከበቡዋቸውን አገራት በሃማስና በፌሊስጤም ደረጃ መደቡ። እስራኤል!!

መድፍ ተተኮሰ። መድፉ ” ቀሃስ” ይላል። ከአዲስ አበባ የተጋዘ ነው። ተናጋሪው አከሉ ” አንድም እዳ ሳይኖርብን አገር አቀናን” እልልታው ጦፈ። ቲማቲምና ቂጣ ይዘው የመጡ የገጠር ነዋሪዎች እልል አሉ። የገባውም ያልገባውም ሰከረ። ኢትዮጵያ አልሞቃትም አልበረዳትም። ዝም ብላለች። ተረኛ እያለች ነው። እነ ጃዋር ምን እያሰቡላት ነው?

ያበደውን የቀሰቀው ደጎል ነው። ደጎል!! የሰሞኑ የፌስ ቡክ ወሬና ፉከራ የትግራይ ጓዙእን ጠቅልላ መሄድ!! ደህና ሁኑ!! የሚመቻችሁን አድርጉ!! ግን ሰው አትግደሉ። ኢትዮጵያ ምን ይዋጥሽ? ያበደው ጠየቀ። ኢትዮጵያ በለሆሳስ ” ምንም” አለች። አዎ ፍቅር ከሌለ መሰነባበቱ ይበጃል። አደጋው ስዩም እንዳሉት አሳሳቢ ነው!! እስኪ ይቅናችሁ። 

ሃሳቡ አዲስ አይደልም። የኖረ ነው። ዝግጅትም የተደረገበት ነው። አትደንግጡ። ካርታውም ተሰርቷል። እነ ለማ እውቀና የሰጣሉ? እነ አብይስ? ሃይሌ እንኳን ….. ሰላም ሰንብቱ!!

syum mesfine.png

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *