(ኤርሚያስ ለገሰ) – የመለስ ትሩፋት ባለቤት አልባ ከተማ መፅሐፍ ” የአዲስአባ ፓለቲካ ምህዳር” በሚል ርእስ ስር በገፅ 252 ላይ የሚከተለውን ትለናለች፣

1998 • የአዲሳአባ የፓለቲካ ስራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከአቶ መለስ ጋር በነበረን ስብሰባ ” ከእንግዲህበአዲስአባ ምድር የብሔር አደረጃጀት መከተል ራስን ለተደጋጋሚ ሽንፈት ማዘጋጀት ነው። የመዲናይቱ ነዋሪበተለይም ወጣቱ በብሔር አደረጃጀት መታቀፍ አይፈልግም” በማለት አቶ መለስ ተናግሮ ነበር። ይህን የአቶመለስ ውሳኔ ተከትሎ ከህውሓት ውጭ ያሉት የብሔር ድርጅቶች እጃቸውን ከአዲስአባ ላይ አነሱ። ህውሓቶችአስቀድመው ራሳቸውን ከኢህአዴግ ቢሮ ስላገለሉ ውሳኔውን አልቀበልም በማለት በመዲናይቱ የትግራይአደረጃጀት እስከማቋቋም የሚደርስ የትእቢት እርምጃ ወሰዱ። ለድርድር ቢጠሩም ፍቃደኛ ሳይሆኑቀሩ።ሌሎቹንም የእነሱን እርምጃ እንዲከተሉ ከጀርባ አደራጁ። እሰጣ ገባው ሳይጠናቀቅ የኢህአዴግ ጉባኤበአዋሳ ተጠራ።

መንደርደሪያ ሁለት:- 2010 

“የኢህአዴግ ሊቀመንበሩ!” አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ(HD) በትላንትናው እለት ( ከ12 አመት በኃላ) የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ሊግ ኮንፍረንስ ላይ ተገኘ። “ተወዳጁ ኢቲቪ” ( EBC) በዜና ዝግጅቱ ከሐይለማርያም ንግግር ውስጥ የሚከተለውን ቀንጭቦ አሰማን፣

የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ሊግ አደረጃጀት ኢህአዴግ ከግንባር ወደ አንድ ፓርቲ ለሚያደርገው ሽግግር ምሳሌይሆናል። ሕብረብሔራዊ ሆናችሁ መደራጀታችሁ ለተለያየ ጥገኛ አስተሳሰቦች ( ትምክህት፣ ጠባብነትያለውቦታ ምን እንደሚመስል ኢህአዴግ ከእናንተ ትምህርት ይወስዳል።

መንደርደሪያ ሶስት:- 2010 

በዛሬው እለት “ተወዳጁ ኢቲቪ”(EBC) እና የኤፈርት ንብረት የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ለተመሳሳይ ኩነት የተለያየ መሪ ርዕስ ያለው ዜናይዘው ወጡ። ኢቲቪ ” የህውሓት የአዲስ አበባ ልዩ ዞን ከፍተኛ አመራሮች የዘጠኝ ቀናትኮንፍረንስ በማካሄድ ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ስብሰባው ተጠናቀቀ በማለት ዘገበ። የህውሓት ንብረት የሆነው ሬዲዬ ፋና ዜና ደግሞ ” ከትግራይ ክልል ውጭ የሚገኙ የህውሓት ከፍተኛ አመራሮች ኮንፍረንስተጠናቀቀ የሚል ነበር።

መንደርደሪያ አራት:- መሪ ጥያቄዎች

ጥያቄ አንድ : – በሶስቱ መንደርደሪያዎች መካከል ያለው ተዛምዶ እና ልዩነት ምንድነው?

ጥያቄ ሁለት: – ህውሓት ከ12 አመታት በኃላ በ HD ውስጥ አድሮ ለምን ስለ ኢህአዴግ ወደ አንድ ፓርቲ መምጣት ዶሰኮረ? ኢህአዴግ አንድ ወጥ ፓርቲ መሆን ይችላል ወይ? ወደ አንድ ፓርቲ ለመምጣት ምን የተቀየረ መዋቅራዊ ለውጥ አለ? የብሔር አደረጃጀት እንዲጠፋ ህውሓት ይፈልጋል ወይ? ህውሓት ድርጅታዊ ፕሮግራሙ ( ህገ መንግስቱ) እንዲቀየር ይፈልጋል ወይ?

ጥያቄ ሶስት: በኢቲቪ እና ሬዲዬ ፋና የዜና ዘገባ ላይ ምን ልዩነት አለ? ህውሓት እንዴት የአዲስ አበባ ልዩ ዞን አደረጃጀት ኖረው? መቼ የተፈጠረ አደረጃጀት ነው? ህውሓት ትግራይን የምመራ ድርጅት ነኝ ብሎ ሲያበቃ እንዴት ከትግራይ ክልል ውጭ አደረጃጀት ሊኖረው ቻለ? የህውሓት የአዲስ አበባ ልዩ ዞን አመራሮች እና አባላት ያነገቡት አላማ እና ተልእኮ ምንድነው?

***

መንደርደሪያ አምስት:- ታሪካዊ ዳራ

እስከ 1995 • ድረስ:-

እስከ 1995 አም ድረስ አዲስ አበባ ስትተዳደር የነበረው ካዛንችስ በሚገኘው የኢህአዴግ ጥምር ኮሚቴ ነበር። ስያሜው የኢህአዴግ ጥምር ኮሚቴ ይባል እንጂ የበላይ አመራሮቹ በሙሉ የህውሓት ታጋዬች ነበሩ።ሊቀመንበር ተስፋማርያም ፣ የፕሮፐጋንዳ ጠርናፊ ፍስሀ ዘሪሁን መአሲ ( አሁንም የህውሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ) ፣ የድርጅት ጉዳይ ጠርናፊ ፈትለወርቅ ሞንጆሪኖ(አሁንም የህውሓት ሰአኮ) ነበሩ። በዚህን ሰአት ኢህአዴግ የነበረው አባል ከ500 የማይበልጥ ሲሆን 350 ያህሉ የትግራይ ተወላጆች( ህውሓት) ነበሩ። በወቅቱ ህውሓት የአዲሳአባን ህዝብ በጥላቻና ጥርጣሬ የሚመለከተው በመሆኑ የነዋሪ መዋቅር ለመመልመል አልቻለም። በህዝቡ ውስጥም ” የኢህዴግ አባል ነኝ” ብሎ መናገር የሚያሳፍር ከመሆኑም በላይ ” የትግሬ ቂጥ ላሽ!” የሚል ስያሜ በማህበረሰቡ ስለሚሰጥ በጣም ያሸማቅቅ ነበር።

በሌላ በኩል የፌዴራል መስሪያቤቶች የኢህአዴግ ጥምር ኮሚቴ አደረጃጀት በሚል ሁሉንም የኢህዴግ አባላት( ህውሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን) የሚጠረንፍ መዋቅር ነበር። የዚህ አደረጃጀት የበላይ አመራሮቹ በሙሉ የህውሓት ታጋዬች ነበሩ። የደህንነት ሀላፊዎቹ ኢሳያስ እና ወልደስላሴ፣ የዋልታው ነጋሽ እና ዘርአይ አስግዶም የፌዴራሉ ፕሮፐጋንደሰ እና ድረረጅት ጠርናፊዎች ነበሩ።

የተለያዩ አደረጃጀቶች ቢሆኑም የአዲስ አበባው ጥምር ኮሚቴ (ተስፋማርያም፣ ሞንጆሪኖ ፣መአሲ) እና የፌዴራሉ ጥምር ኮሚቴ ( ወልደስላሴ፣ ኢሳያስ፣ ነጋሽ፣ ዘርአይ) በወር አንድ ጊዜ ካዛንችስ በመገናኘት አፈፃፀማቸውን እና የቀጣይ ወራት ተግባሮችን ይገመግማሉ። ከተግባሮቻቸው ቁልፍ ስራ ተደርጐ የሚወሰደው የስለላ መዋቅር መዘርጋትና መገምገም ነበር። ከዚህ በተጨማሪ የፓለቲካ መሪዎችና የመንግስት ባለስልጣን መሾምና ማባረር ትልቁ ስራቸው ነበር።

1995 • እስከ 1998 • ድረስ:-

እነዚህ ሶስት አመታት አርከበ እቁባይ ከድርጅቱም በላይ ገዝፎ የታየበት ነበር። በዚህ ምክንያት አባላቱን በሙሉ እንዲባረሩ አድርጐ የመንግስት፣ የድርጅት እና የፕሮፐጋንዳውን ሰራ ብቻውን ተያይዞት ነበር። በከተማው የኦህዴድ እና ብአዴን አባላት በመባረራቸው ባይ ዲፎልት ድርጅቶቹ አልነበሩም። ኦህዴድ እና ደኢህዴንን አቶ መለስ ” የዝንብ ጥርቅሞች!” በማለት በድርጅቱ ሪፓርት ላይ ማካተቱ ለአርከበ እቁባይ ጠራርጐ ለመጣል ምቹ ሁኔታ ፈጥሮለት ነበር። ስለዚህም የቀሩት የህውሓት አባላት ብቻ ነበሩ። በዚህ ምክንያት ” የህውሓት የአዲስ አበባ ዞን” የሚል አደረጃጀት ተፈጠረ። የዚህ አደረጃጀት ዋነኛ አላማ በአዲስ አበባ የትግራይ (ህውሓት) የበላይነትን በፅኑ መሰረት ላይ መገንባት ነበር። ( ዝርዝሩን ለመመልከት የመለስ ትሩፋት: ባለቤት አልባ ከተማ መፅሐፍን ይገርቡ!)

የፌዴራል ጥምር ኮሚቴው በነበረበት የቀጠለ ሲሆን ግንኙነቱ ” ከህውሓት የአዲስ አበባ ዞን” ጋር ብቻ ነበር። አመራሮቹም ከዋልታው ነጋሽ ውጭ ሁሉም በቦታቸው ነበሩ። በተለይ ግን የደህንነት ሐላፊዎቹ ኢሳያስ እና ወልደስላሴ የጐላ ሚና ነበራቸው።

1998 • በኃላ:-

የምርጫ 97 ውጤት ሁሉንም ነገር ቀያየረው። በአዲሳአባ ውስጥ የትግራይ ተወላጅ እጅግ በጣም የተጠላበት ሰአት ስለነበር ፊትለፊት የሚወጣ ማግኘት ከባድ ሆነ። አቶ መለስ የአዲሳአባ ህውሓት መዋቅር አመራሮቹን በሙሉ ሰብስቦ ” የአዲሳአባ ህዝብ ጠልቷችኃል” በማለት ወደ ትግራይ እና ህውሓት በሀይል የተቆጣጠራቸው ቦታዎች ሰደዳቸው። ለምሳሌ የዛሬው የአዲሳባ ስራ አስኪያጅ( የድሪባ ኩማ አለቃ) የሁመራ ዋና አስተዳዳሪ ሆኖ ተላከ። ቦሌን ወደ መቀሌ የቀየረው የቦሌ ከንቲባ የነበረው ሀይለስላሴ የአንዱ የትግራይ ዞን አስተዳዳሪ ሆነ።

ከወራቶች በኃላ 30ሺህ የሚጠጉ የአዲሳአባ ወጣትና ሴት ሊግ አባላት በሞሉት መጠይቅ ላይ የብሔር አደረጃጀት አንፈልግም የሚል ከ90 በመቶ በላይ ምላሽ ሰጡ። አቶ መለስም የብሔር አደረጃጀትን ይዞ ሙጭጭ ማለት እንደማያዋጣ ተረድቶ ይሁን አሊያም ለጊዜያዊ ስልት ” የብሔር ፓለቲካ በአዲስ አበባ አያዋጣም” የሚል ውሳኔ ወሰነ። የከተማዋን ህዝብ በነዋሪ፣ ወጣት እና ሴት ፎረምና ሊግ እንዲደራጁ መመሪያ አስተላለፈ። የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት አመራሮችም ትልቁ ስራ እነዚህን ማህበራዊ አደረጃጀቶች ማጠናከር እንደሆነ ጥብቅ ትእዛዝ ተሰጠን። ኦህዴድ፣ ብአዴን እና ደኢህዴግ ከአዲሳአባ ላይ እጃቸውን አነሱ። የቀረው ህውሓት ነበር።

ህውሓት የአዲሳአባ ዞን አደረጃጀቱን እንዲያፈርስ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም አሻፈረኝ አለ። በረከት፣ ታደሰ ጥንቅሹን ጨምሮ የአዲሳአባ የኢህአዴግ ኮሚቴ የህውሓትን እንቢተኝነት ለአቶ መለስ ነገርነው። እየሳቀ ” ለቴዎድሮስ እና ጐበዛይ በረከት ንገራቸው” ብሎ አጀንዳውን ዘጋው። በወቅቱ ቴዎድሮስ እና ጐበዛይ የህውሓት የፕሮፐጋንዳና ድርጅት ሀላፊዎች ነበሩ። በረከት በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ቢጠራቸውም ” አንተ ስለ ህውሓት አደረጃጀት ምን አገባህ?” በማለት አፍንጫህን ላስ አሉት።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ህውሓት ባደረገው የአደረጃጀት ለውጥ በሰባት ዞኖች መደራጀቱን ይፋ አደረገ። ስድስቱ በትግራይ የሚገኙ መሆናቸውን ተናገረ። የተቀረው ” የህውሓት የአዲስ አበባ ልዩ ዞን የሚል ስያሜ እንደተሰጠው ተበሰረ።የዚህ የአዲሳባ ህውሃት ልዩ ዞን አባላት… የአዲሳአባ መዋቅር፣ የፌዴራል መስሪያቤት የትግራይ ተወላጆች፣ የልማት ድርጅት የትግራይ ተወላጆች፣በሚዲያ ተቋማት የሚሰሩ የትግራይ ተወላጆች፣ በኢምግሬሽን፣ ደህንነት፣ ፌዴራል ፓሊስ የሚሰሩ የትግራይ ተወላጆች፣ በኤፈርት የሚሰሩ የትግራይ ተወላጆች፣ ከትግራይ ውጭ የሚኖሩ የትግራይ ባለሀብቶች፣ ከትግራይ ውጭ ባሉ ክልሎች የሚሰሩ የትግራይ ተወላጆች፣ በኤንባሲ እና ቆንስላ የሚሰሩ የትግራይ ተወላጆችን የሚያቅፍ መዋቅር እንደሆነ ተገለፀ። “ልዩ” የምትለው ቅፅል የተጨመረችው በዚህ ምክንያት መሆኑ ተነገረ።

***

የህውሓት የአዲስ አበባ ልዩ ዞን” ተልእኮ ምንድነው?

አንደኛ:- ለህውሓት ከፍተኛ ገንዘብ ማሰባሰብ። እንደሚታወቀው ህውሓት ባለስልጠናት፣ አመራሮችና ካድሬዎች ከወር ገቢያቸው ውስጥ 10 በመቶ ድርጅታዊ መዋጮ የመክፈል ግዴታ አለባቸው። ስለዚህም ከላይ የተጠቀሱት የህውሓት አባላት በልዩ ዞኑ አማካኝነት በሚሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ ለህውሃት ገቢ ያደርጋሉ። ለምሳሌ በአንድ ወቅት የደህንነት ምክትል ሀላፊ የነበረው ኢሳያስ ወ/ ጊዬርጊስ ለህውሓት በወር 3ሺህ ብር ይከፍል ነበር። ኢሳያስ ከደህንነት ሹመቱ በተጨማሪ በአቶ መለስ ምደባ የተባበሩት መንግስታት ፀጥታው ም/ቤት ኢትዬጲያን ይወክል ነበር።

ሁለተኛ:– የህውሓት የአዲሳአባ ልዩ ዞን ከትግራይ ክልል ውጭ በሌሎች ክልሎች፣ አዲስ አበባ፣ ድሬደዋ፣ ፌዴራል ተቋማት፣ ኤምባሲ እና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች ውስጥ የስውር መንግስትነት ሚና አለው። በጀት ይደለድላሉ። ባለስልጣናት ሊሆኑ የሚችሉ ይመለምላሉ። ለህውሓት አይመችም የሚሉትን ካድሬ እና ባለስልጣን ያባርራሉ። በሚኖሩበት አካባቢ ለትግራይ ልማት ማህበር ገቢ ይሰበስባሉ።

ሶስተኛ:- የስለላ መዋቅርም በሁሉም ቦታዎች ይዘረጋሉ። በሁሉም የኢትዬጲያ አካባቢ ለስርአቱ ተገዥ ያልሆኑትን በመሰለል ለፀጥታው መስሪያቤት ያቀብላሉ። የተለያዩ ባለሀብቶችን፣ የሐይማኖት ተቋማት አባቶችን፣ አገር አቀፍ እና አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ይሰልላሉ። ሀብትና ፍቃዳቸውን እስከማስነጠቅ የሚያደርስ መረጃ ያቀብላሉ።

አራተኛ:– ከትግራይ ክልል ውጪ ኤፈርት እና የትግራይ ተወላጆች ሊሰማሩባቸው የሚገቡ አዋጭ የኢኮኖሚ ሴክተሮችን ይለያሉ። ኤፈርትና ህውሓት ለሚሰሩት ህገወጥ ተግባራት ከለላ ይሰጣሉ። ሚስጥር ይደብቃሉ። ኤፈርትን የሚግደረደሩ ባለሀብቶች ኢኮኖሚክ ኢንስትሩመንት ( ታክስ በመጫን፣ ጉምሩክ በማጉላላት፣ መሬት በመከልከል) ከጨዋታ ውጭ እንዲሆኑ ያደርጋሉ።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *