ቢቢሲ አማርኛ – የአሜሪካው ፔንታጎን እቃ ግዥ ክፍል ኤጀንሲ 800 ሚሊዮን ዶላር ምን ላይ እንደዋለ የሚያሳየው መረጃ መጥፋቱን አንድ የኦዲት ምርመራው አሳወቀ። ኧርነስት ኤንድ ያንግ ድርጅት ኤጀንሲውን ኦዲት ባደረገበት ወቅት 800 ሚሊዮን ዶላር ምን ላይ እንደዋለ መረጃ እንደሌለው ፖሊቲኮ ዘግቧል።

ገንዘቡ ለወታደራዊ ግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የኮምፒውተር ሲስተሞችን ለመዘርጋት እንደዋለም ተዘግቧል። ኤጀንሲውም በበኩሉ “ኃላፊነት የጎደለው” ነው ባይልም ገንዘቡ ምን ላይ እንደዋለ በትክክል ቁጥጥር አለመዘርጋቱን ስህተት መሆኑን አምኗል።

“በኧርነስት ኤንድ ያንግ ግምገማ መሰረት ገንዘቡ ምን ላይ እንደዋለ በትክክል አለመቆጣጠጠር አለመቻላችንና እና ምን አይነት ግንባታዎችም እንደተገነቡ አለማወቃችን እንስማማበታለን” በማለት የኤጀንሲው ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል “ምንም እንኳን መረጃዎቹ ላይ ችግር ቢኖርም ከተጠያቂነትም መሸሽም ሆነ የጠፋ ንብረት የለም” ብለዋል።

በመከላከያ ክፍል ውስጥ በኦዲት ያለፈው የመጀመሪያ ኤጀንሲ ሲሆን ትልቅና ውስብስብም ነው ።”በዚህም አንፃር በመጀመሪያው ዙር ጥርት ያለ የኦዲት ውጤትም እንጠብቃለንም ብለው አልጠበቁም” በማለት ተናግረዋል።

ቃል አቀባይዋ እንደሚሉት ኤጀንሲው በሁለተኛው ዓለም ጦርነት የተቋቋመ ሲሆን አሰራሩንም ለማሻሻልም የተለያዪ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው ብለዋል። “በአሜሪካ ግብር ከፋዮች ከመተዳደራችን አንፃር ግባችን ለመጪው ኦዲት ዙር ሙሉ በሙሉ ተገዥነትን ማሳየት ነው። “ብለዋል።

በየዓመቱ 700 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ በጀት ያለው መከላከያ ሙሉ በሙሉ ኦዲት ተደርጎ አያውቅም። ፕሬዚዳንት ትራምፕና የሪፐብሊካኖቹ ኮንግረስ ለመከላከያ ዲፓርትመንት በቢሊዮኖች ዶላር ጭማሪ እንዲደረግ በተደጋጋሚ መቀስቀሳቸው የሚታወስ ነው።

የተለያዩ ሪፖርቶችም እንደሚያሳዩትም ይህ የኦዲት ሪፖርት ክፍተት ከማሳየቱም ጋር ተያይዞ ኤጀንሲው በጀቱን ምን ላይ እንደሚያውል ከፍተኛ ጥያቄም አስነስቶበታል ተብሏል። ” ገንዘቡ ምን ላይ እንደሚውል መቆጣጠር ካልተቻለ ኦዲት ማድረግ ከባድ ስራ ነው ” በማለት የሪፐብሊካኑ ሴናተር ቼክ ግራስሌይ ተናግረዋል።

ኤጀንሲው በፔንታጎን ካሉት አንደኛው ትልቁ ክፍል ሲሆን 40 ቢሊየን ዶላር አመታዊ በጀት እንዲሁም 25 ሺ ሰራተኞች አሉት። የፔንታጎን አመታዊ በጀት ከግማሽ ትሪሊየን ዶላር ይበልጣል።

ይህ ሪፖርት የአውሮፓውያኑን 2016 ዓ.ም ይሸፍናል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *