ዛሬ ቢጫ ለብሳ ” ትንቢት” ያሰራጨች አንዲት ሴት የቲዎድሮስ ካሳሁንን፣ የሃይሌ ገብረስላሴን፣ የኤልሳ ቆሎን በመጥራት ” ወዮላችሁ ” ስትል ማስጠንቀቋ እያነጋገረ ነው። መልዕከቱን በቪዲዮ የሰራጨው አዲስ ነገር በሚል የዩቲዩብ ሊንክ ሲሆን በበጎና በትችት ሰፊ አስተያተም ተሰንዝሮበታል።

መምህር ግርማን በማድነቅ የጀመረችው ይህቺ ሴት ቴዲ አፍሮን ” ወዮልህ ” ያልችው ሀዳም በመዝፈኑና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች ስላሉት ” ህዝቤን ያዝክብኝ” በሚል ማሪያም እንደተቆጣችው በመናገር ነው። በ2007 እንግሊዝ እያለሁ መልዕክቴን በጥልቅ አስተላልፌያለሁ የምትለዋ ሴት ” ስላነት የምለው ብዙ የለም። ተንበርከክና እግዚአብሄርን ምን እንደበደልክ ጠይቅ” ስትል ኤልሳ ቆሎን በጥቅሉ ነው ያስጠነቀቀቻት።

የተቆረጠ የሚመስለው ይህ ቪዲዮ ለምን ዓላማ እንደተለጠፈ ማብራሪያ የለውም። ይሁን እንጂ የቴዲ አፍሮን ዘፈን በአንድ በኩል እያሳየ ” ትንቢቱን” የሚተርከው ቪዲዮ ላይ የምትታየው ተናጋሪ ይህንን የምትናገረው ከራስዋ ሳይሆን ማሪያም ልካት እንደሆነ አስታውቃለች። ቴዲ አፍሮ አዲስ ዓለም ገዳም ግብቶ መዝፈኑን ሃጢያት እንደሆነ በካፍተኛ ሃይለቃልና ቁጭት ተናግራለች። እናም ” ሁለተኛ ” ስትል ቲዴ ይህንን እንዳያደርግ አሳስባለች። ” ተዋህዶን ልቀቅ” በማለትም አስጠንቅቃዋለች።

የቴዎድሮስን ልብ የሚያውቁ፣ እርጋታውን የሚረዱና የህይወት መርሁን በተግባር የሚያጤኑ ” ትንቢት ተናጋሪዋን ትችተዋል” አንዳንዶቹም አጥጥለዋታል። ሌሎች ደግሞ ትንቢት ተናጋሪዋ የምትናገረው ትክክል ስለመሆኑ በመመስከር ድጋፍ ሰጥተዋል። እሷ እንደምትለው አገር መውደድ መተዛዘን፣ መፋቀር፣ መከባበር እንደሆን ” እመቤቴ ትናገራለች” ማለቷን ተከትሎ ቴዲ የቱን አጓደለ ሲሉ ጠይቀዋል። ስለ ፍቅር መስበኩንም አወደሰዋል።

ምንም ተባለ ምን ” ሃይለኛ ቁጣ አለ፣ በንስሃ ብትመለስና ዳግመኛ ቤተ ክርስቲያንን ካልነካህ ሃጢያትህ ይታጠብልሃል” በሚል ምክር የለገስችው ሴት ” አልበዛም” ስትል በተደጋጋሚ ወቅሳለች። ቴዲን የሚወዱ ቢሰድቧት፣ እሷ ግን በደሙ ለተዋጀላት አምላኳ ስትል ይህንን እንደምትናገር ገልሳለች።

ያስጀተለችው አህይሌ ገብረ ስላሴን ሲሆን ” አንተ ብቻ ንስሃ ግባ” ብላዋለች። ” ምንም ብታደረግ ” እመቤቴ ባንተ ደስተኛ አይደለችም ” አስከትላም ቤትክርስቲያን ማሰራት፣ ዣንጥላ ማስገባት ፣ ገንዘብ መስጠት ጽድቅ ያመታል ብሎ ማሰብ አግባብ እንዳልሆነ አመልክታለች። “ብቻ” አለችው ሃይሌን ” ተንበርከክና እግዚአብሄርን ምን እንደበደልከው ጠይቀው ይዘረዝርልሃል” ብላዋላች።

ቀጥይዋ ኤልሳ ቆሎ ስትሆ፣ የተላለፈላት ትንቢት ” ቅጣትሽ ቀርቧል። ይህንን መልዕክት ሳስተላልፍ ጊዜ አልቋል። በንስሃ ተመለሱ” የሚል ነው።

ይህ ዘመን ትንቢት ተናጋሪና ነቢይ ነን የሚሉ የበዙበት፣ ሁሉም ማሀብራዊ ሚዲያዎችን የሚጠቀሙና ” ታምራት” የሚሉትን የሚያሳዩበት በመሆኑ ” ቀልብ የገዙ” አገልጋዮች በእግዚአብሄር ቃል ላይ የተመሰረተ ትምህርት በተከታታይ እንዲሰጡ በርካቶች ይጠይቃሉ። የሞተ አስነሳን ከሚሉ ጀመሮ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚለቀቁ ትንግርቶች ማህበረሰቡን ወደ አለተፈለገ የስነልቦና ጣጣ ውስጥ እንዳይከት ጥንቃቄ ሊወሰድ እንደሚገባም ይመክራሉ።

በአንድ ወቅት በቀጨኔ መድሃኒያለም አካባቢ ከትመው የነበሩት ባህታዊ ገብረ መስቀል ገና ተከታዮቻቸው እንደ ደራሽ ወሃ ሳይጎርፉ አለቃ አያሊወ ታምሩ ” ይህ መንፈሳዊ ዛር ነው ” በማለት ህዝብ ክርስቲያኑ ሊጠነቀቅ እንደሚገባ መክረው ነበር።የሳቸውን ምክር አንሰማም ያሉ ብዙ ዋጋ ከከፈሉ በሁዋላ በመጨረሻው ሁሉንም ሲረዱና ቀጨኔ እተከራዩት ግቢ ውስጥ የሆነውን የተመለከቱ አዝነው መቀመጣቸው የሚታወስ ነው። መጽሃፉ ” ሁሉንም መርምሩ” እንደሚለው በግልብ ከመጓዝ ማስተዋል የተሻለ እንደሚሆን፣ ሚዲያውም ለገበያ ብሎ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን ተቀብሎ ከማሰራጨት ሊቆጠብ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ሃሳብ ሲሰጥ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። ቪዲዮውን እዚህ ላይ ይመልከቱ

https://www.youtube.com/watch?v=nO_M8fq7j7U

 

 

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *