ለውሳኔ የተቀጠሩት የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና የንግስት ይርጋ ክስ ተቋረጠ። ከወልቃይት አማራ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ ከነበሩት ሰዎች መካከል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ንግስት ይርጋ እንዲሁም፣ ከአንድ መቶ በላይ እስረኞቸ የክስ መዝገባቸው እንዲቋረጥ ተወስኗል። በተጨማሪም ተሻገር ወልደ ሚካኤል ጌታቸው አደመና አታላይ ዛፌ ተካተዋል።
ክሳቸው ከተቋረ ውስጥ 56 የግንቦት ሰባት እንዲሁም 41 ከኦነግ ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው ናቸው። በተመሳሳይ ዜና ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ አሳምነው ጽጌና ሌሎች ተከሳሾሽና ፍርደኞች በይቅርታ እንዲፈቱ ጉዳያቸው ” እየተጠና ” መሆኑ ተሰምቷል።
በአማራ ክልል ሰፊ የስራ ማቆምና ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ ለማካሄድ በስፋት ዘመቻ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ይህ ዜና ይፋ መሆኑ የታሰበውን አድማ አያደናቅፈውም የሚሉ መረጃዎችም እየተሰራጩ ነው። የተለያዩ ይቅርታ የተደረገላቸው እንደገለጹት ሰፊ ቁጥር ያላቸው እስረኞች በየማጎሪያ ቤቱ መኖራቸውን ነው።
በዚሁ እስረኞችን የመልቀቅ ጉዳይ ላይ የኢህአዴግ ደጋፊ ባለጠጋ አገራት ኢህአዴግ በጀመረው እንዲገፋበት እያሳሰቡ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።