” የፓርላማው አባላት አዋጁን እንዲሰረሰ ካላደረጉ፣ እስረኞችን ያስፈትው፣ ማስተር ፕላኑንን ያስቀየረው፣ ማእከላዊን ያዘጋው ቄሮ እጅ ባምስጠምዘዝ አዋጁን ያመክነዋል። ይደልዘዋል”

” እጅ ማውጣት ከህዝብ ጋር መታረቅ ወይም ለመጨረሻ መቆራረጥ ነው”
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የሚስተዋለው የፖለቲካ ከባቢ አየር የሚጨንቅ መሆኑን የሚከራከሩት ጉዳይ አይመስልም። መንግስት ይህንኑ አሳሳቢ ቀውስ በሃይል ለማርገብ በአዋጅ ተደግፎ እየሰራ መሆንኑ ይናገራል። ተቃዋሚዎች፣ “ወዳጅ” አገሮች፣ አክቲቪስቶች፣ ምሁራኖች ከየአቅጣጫው የመንግስት አካሄድ ፍሬ አያመጣም እያሉ ነው። ቄሮ ግን ነገሩን ይበልጥ ሊያከር እንደሆነ እየተሰማ ነው።
አሁን ያለውን የኢህአዴግ አካሄድ የሚቃወሙ አካላትና ወዳጅ መንግስታት ቀደም ሲል ጀምሮ አገራዊ እርቅ ግድ እንደሆነ በተደጋጋሚ ቢናገሩም ተግባሪው አካል ” የለም፣ አይሆንም፣ እኔው በጥልቅ ታድሼ ሁሉም አበጀዋለሁ” በሚል ላለፉት ሁለት ዓመታት ሮጠ። ተቀመጠ። መከረ። ተገማገመ። ራሱን በራሱ አንድበት አበሻቅጦ ሰደበ። ዳፍቆ ዳፍቆ መጨረሻው አስቸኳይ አዋጅ ሽሮ፣ አስቸኳይ አዋጅ ማወጅ ላይ ተንጠለጠለ።
በታወጀ በአናቱ “ነጻ እርምጃ ውሰዱ” በሚል ትዕዛዝ የተደገፈው አዲሱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ገና ከጅምሩ የከረረ ተቃውሞ አጋጥሞታል። ከተቃውሞው ሌላ መዘዙ የአገሪቱን ኢክኖሚያዊ እምሽክ እድርጎ እየበላው ሲሆን፣ ማህበራዊ ድሩንም እየተለተለው ነው። በማህበራዊ ጉዳዮችን ከኑሮ ዘይቢያቸው ጋር ክፉኛ እያላጋ ያለው ይህ ቀውስ ድሮም ችግር ያልተለየው ኢኮኖሚና የእንቦጭ አረም ሆኖበታል።
በዚሁ ሳቢያ የውጪ ምንዛሬ ችግር የሚያፋጅ፣ የገቢ እቃዎች እጥረት፣ በተለይም እንደ መድሃኒት ያሉ የነብስ አድን ነጥረ ነገሮች ህልም እየሆኑ መሆኑንን ዘገባዎች እያረጋገጡ ነው። ባለስልጣናትም እየመሰከሩ ናቸው።ችግሩ አደገኛ ቢሆንም የምንዛሬ እጥረት መፍጠር የሰላማዊ ትግሉ አንድ አካል በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እየተሰማ ነው። እናም ኢህአዴግ በጉልበት፣ ታጋዮች በኢኮኖሚ ትግል እስከመቼ ? ይህ ችግርስ ሄዶ ሄዶ የት ያደርሳል? የሚለው የበርካቶች ጥያቄና ጭንቀት ነው።
በዚሁ በትግሉ መነሻነት ኢህአዴግ ፓርላማውን ሰብስቦ የአስቸኳይ አዋጁን ካጸደቀ፣ ሊጠራ የታሰበው አድማ ከላይ የተገለጸውን ችግር ይብልጥ እንደሚያወሳስበው ከወዲሁ ፍርሃቻ አለ። ቄሮን ጥቅሶ ጃዋር መሀመድ ይፋ እንዳደረገው ” ቄሮ ሁሉንም ያደርገዋል” ሲል ለፓርላማ አባላት አንድ እድል እንዳላቸው ነግሯቸዋል።
በአቸኳይ አዋጁ አናት ላይ የወጣውን የነጻ እርምጃ ውሰዱ ትዕዛዝ አስመልክቶ ኮማንድ ፖስት ” ለህጉ አልገዙ ያሉ” በሚል ትዕዛዙ እንደማስታገሻ መውጣቱን ያትታል። በሌላም በኩል በትዕግስት ሰው እንዳይሞት ሙከራ መደረጉን አክሎ በዚህ መልኩ ግን መቀጠል እንደማይቻል ያሳስባል። በተመሳሳይ ቄሮ እና የአካባቢያቸው ነዋሪዎች ለፓርላማ አባላት ማስፈራሪያ መላካቸውን እንደ አንድ አስፈሪና ህገወጥ ጉዳይ አቅርቦታል።
ጃዋር እንደሚለው ” አንድን እንደራሴ እኔ እገሌ እባላለሁ። የሰፈርዎ ነዋሪ ነኝ። ይህንን አዋጅ አትጽደቅ። እጅህን አታውጣ። ታሪክ ስራ። ሃያ ሰባት ዓመታት አቸበጨብክ ዛሬ ታሪክ ስራ። ወደ ህዝብ ተቀላቀል” ብሎ ስልክ ቢደውል፣ ይህንን የተባለው ሰው ሊኮራ ይገባል እንጂ ሊፈራ አይገባም። እንደዚህ መባሉ ህወሃትን ሊያሳስበው አይገባም።
ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ለወከሉት ሕዝብ ያልሰሩ የፓርላማ አባላት ከፊት ለፊታቸው ባለው ስብሰባ ላይ አዋጁ እንዳይጸድቅ ቢቃወሙ ታሪክ የሰራሉ። ካልሆነና በተቃራኒው “ልለጉምህ ሲባል ለጉመኝ ” በማለት እጅ ማውጣት ህዝብ ላይ ክህደትን እንደማወጅ እንደሚቆጠር የኦሮሞ አክቲቪስቶችና የአማራ አክቲቪስት አቻም የላህ ያሳስባሉ።
ፐሮፌሰር ሕዝቄል ገቢሳ ” ሰው ሁኑ። ህሊናቸሁን አክብሩ። እንግዶችን ለመቀበል በተዘጋጀ ህዝብ ላይ እንዲህ ያለ ወረራ ሲፈጸም ያሳዝናል። እባካችሁን ሰው ሁኑ። እንደ ሰው አስቡ። ይህ የመጨረሻ እድል ነው። ወደ ህዝብ ተመለሱ። አለበለዚያ የመጨረሻ መቆራረጥ ይሆናል” ሲሉ ማሳሰቢያ ለፓርላማው አባለት አስተላልፈዋል።
አቶ ጃዋር ግን ” የፓርላማው አባላት አዋጁን እንዲሰረሰ ካላደረጉ፣ እስረኞችን ያስፈትው፣ ማስተር ፕላኑንን ያስቀየረው፣ ማእከላዊን ያዘጋው ቄሮ እጅ ባምስጠምዘዝ አዋጁን ያመክነዋል። ይደልዘዋል” ሲሉ ዝተዋል። በኦ ኤም ኤን የቀጥታ ውይይት ” ይህንን ለኢትዮጵያ ህዝብ አስረግጬ እናገራለሁ” ሲሉ የተደመጡት አቶ ጃዋር ” ኦህዴድ መህዝብና በወያኔ መካከል የጀመረውን ዳንስ ያቁም። በርገጠንኝነት ደግሜ እናገራለሁ የአብይ ጸሃዬን ቃል እንገለብጠዋለን። አዋጁ እንዳይሰራ እንዳእርገዋለን። ቄሮ ሁሉንም ያደርገዋል”ብሏል። ከመፈራት ወደ መከበር የተሸጋገረው የኦሮሚያ ፖሊስም በያዘው አቋም እንዲገፋበት ጥሪውን አስተላልፏል” ፓርላማው ስብሰባውን አድርጎ ወሳኔው ሲታወቅ እንገናኝ ሲል ቀጠሮውን ይዟል።

Jawar Mohammed

ማስታወቂያ: በምእራብ ኦሮሚያ እየተፈፀመ ባለው ግድያ እና በዛሬው ዕለትም ለሠራዊቱ ሕዝባችንን እንዲገድል በተሰጠው ግልፅ ትእዛዝ ሃገሪቱ ወደ አደገኛ ሁኔታ እያሽቆልቆልች ነው። የፓርላማ አባላት በ አስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁ ላይ አቋም እስኪወስዱና አስኪያግዱት ወይም እስኪያፀድቁት ቄሮ የራሱን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል። የፓርላማ አባላት የፊታችን አርብ በሚደረገው የፓርላማ ስብሰባ የ አስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁን እንዲያፀድቁ በስልጣን ላይ ያለው ቡድን እያስፈራራቸው እንደሆነ እየሰማን ነው። ፓርላማው ይህን ሕገ ወጥ የ አስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ የሚያፀድቀው ከሆነ በቁርጠኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዲቀለበስ ይደረጋል። በመሆኑም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረግም ሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊደርግ የታሰበ ጉዞ በሙሉ ከፊታችን አርብ ጀምሮ ሁኔታዎች እስኪረጋጉ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም አበክረን እናሳስባለን።

ስለ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት ሲናገር ” የአስቸኳይ አዋጁ እያለና በህገመንግስት የተደነገገው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በኮማንድ ፓስት ስም በወታደርና ደህንነት ሃይል ተወስዶ ባለበት ሁኔታ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት ዋጋ ቢስ ነው። አቅም አልባ ነው። አዲስ መሪ የማሻሻያ እርምጃዎች የሚወስደው በስድስት ወይም በአመት ጊዜ ውስጥ ስለሆነ ህጋዊ መብቱ በአዋጅ የተገፈፈ መሪ ለመሆን የሚደረገው ግብግብም ዋጋ የለውም” ብሏል። አይይዞም የአቶ ለማ መገርሳ ስልጣን አሳሳቢ እንደሆነም አመልክቷል። ኦህዴድ አዋጁን እንዲቀበል ፈቃደኛ ከሆነ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ሃላፊነት እንደሚሰጠው ቃል እንደተገባለት አመልክቷል። ይህም ተቀባይነት እንደሌለው፣ ከሆነም ኦህዴድ ወደ ህዝብ ለመቀላቀል የጀመረውን ጉዞ እንደሚያጨናግፍ ከወዲሁ እንዲረዳ አሳስቧል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

በመህግስት በኩል አገሪቱ አሁን አንጻራዊ መሻሻል የሚታይበት ሰላም ላይ መሆኗን በማስታወቅ ይህንን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የአስቸኳይ አዋጁን በማያከብሩ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ መተላለፉን ነው በኮማንድ ፓስቱ አማካይነት ያሳወቀው። አስቸኳይ አዋጅ ለስድስት ወር እንዲጸና ፓርላማው ፈቃድ መስጠት ስለሚገባው አስቸኳይ ስብሰባ መጠራቱ ይታወሳል። በዚሁ መሰረት ፓርላማው ለዕረፍት በተበተነበት ወቅት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አሥራ አምስተኛ ቀኑን የሚይዘው በመጪው ዓርብ የካቲት 23 ይሆናል። በዚሁ ቀን ፓርላማው ጥሪውን አክብሮ በስብሰባው ላይ ተገኝቶ አዋጁን እንዲደገፍ ይጠየቃል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *