ሩዋንዳ ድምፃቸው ይረብሻል ያለቻቸውን 700 አብያተ ክርስትያናትን ዘጋች። አብያተ ክርስትያናቱ የተዘጉት የአገሪቱን የህንፃዎች አስተዳደር ህግ ባለማክበርና በድምፅ ብክለት መሆኑ ታውቋል።

ሩዋንዳ ድምፃቸው ይረብሻል ያለቻቸውን 700 አብያተ ክርስትያናትን ዘጋች። አብያተ ክርስትያናቱ የተዘጉት የአገሪቱን የህንፃዎች አስተዳደር ህግ ባለማክበርና በድምፅ ብክለት መሆኑ ታውቋል። ከተዘጉት ብዙዎቹ አነስተኛ የጴንጤ ኮስታል አብያተ ክርስትያናትን ሲሆኑ አንድ መስጊድም ይገኝበታል።

አንድ የመንግሥት ሃላፊ ለቢቢሲ እንደገለፁት ደግሞ ከተዘጉት አብያተ ክርስትያናትን አብዛኞቹ ቅኝት ከተደረገና ማረጋገጫ ካገኙ በኋላ እንዲከፈቱ ተደርጓል። ገና ያልፀደቀው የአገሪቱ ህግ እንደሚለው ሁሉም ሰባኪዎች ቤተ ክርስትያን ከመክፈታቸው በፊት የሥነ-መለኮት ስልጠና ማረጋገጫ መያዝ ይኖርባቸዋል።

የተወሰኑት አብያተ ክርስትያናትን በይዞታም ትልቅና ከፍተኛ ቀጥር ያለው ተከታይ ያላቸው ሲሆን ብዙዎቹ ትንሽ ተከታይና ይዞታቸውም ከግንባታ ውጭ የሆነ ነው።

የእነዚህ አብያተ ክርስትያናትን መሪዎች ብዙ ተከታይ ለማፍራት አካባቢን የሚረብሽ ከፍተኛ ድምፅ በመጠቀምም ይወቀሳሉ። የአንዳንዶቹ ቤተክርስትያኖች አሰራር ምእመናንን ለአደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል የሩዋንዳ ባለስልጣናት ጠቁመዋል። በሩዋንዳ አብዛኛው ህዝብ ክርስትያን ሲሆን ባህላዊ አምልኮን የሚከተሉም አሉ።

bbc

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *