አብረን መሄድ አንችልም። ይገሉናል። የደበድቡናል። በየመንደራችን ቤት ድረስ እየገቡ እርምጃ ይወስዱብናል። ምንም ማደርግ አልቻልንም። በዚህ ሁኔታ እንዴት አገር ይረጋጋል? ህዝብ ላይ በጅምላ ይተኩሳሉ። በጥይት ያቆስላሉ። አዛውንት፣ ህጻን ትልቅ አይሉም። ጠይቆ ለመረዳት ጊዜ አይሰጡም። ማስረዳትም አይቻልም። የሚሰሙምም አይመስሉም። ደም የጠማቸው ናቸው። ….

በኦሮሚያ ክልል ሰዎች እየተገደሉ፣ እየቆሰሉና እየታሰሩ መሆኑንን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከባልደረባ ወይም ከቤተሰብ ጋር አብሮ መሄድ የማይቻልበት ደረጃ መደረሱንም ችግሩ ባለባቸው አካባቢ የሚኖሩ ሲናገሩ እየተሰማ ነው። የኦሮሚያ ፖሊስ ሳይቀር ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ የሞቱም አሉ። መንገድ ተዘጋግቷል። የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሏል። በክልሉ ያለው አጠቃላይ ሁኔታ አያምርም። ወታደራዊ ኮማንድ ፖስቱ አዲስ ትዕዛዝ አስተላልፏል። በኦሮሚያ ህዝቡ ራሱን በሚችለው ሁሉ እንዲከላከል ተነግሮታል።

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ” ጸደቀ” ከተባለበት ቀን ጀምሮ ነገሮች በኦሮሚያ ተካረዋል። ይህንኑ የሚያረጋግጡ ዜናዎች በአሜሪካ ሬዲዮ፣ በጀርመን ድምጽ፣በድምጽ የቀረቡ ሲሆን፣ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችና ማህበራዊ ገጾች በምስል እያስደገፉ አስከፊውን ኩነት በማሰራጨት ላይ ናቸው። 

ከኢህአዴግ ወገን በይፋ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ማስተባበያ አልቀረበም። አገሪቱን በኮንትራት ለስድስት ወር እያስተዳደረ ያለው የወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ” ማንኛውንም ዓይነት እርምጃ ውሰዱ” በሚል ካዘዘ በሁዋላ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው። ይህንኑ የሚዘግቡ ሚዲያዎች እንዳሉት የመንግስት የቀድሞው የመዋቅር አካላት መግለጫ እንዲሰጡ ሲደወልላቸው አይመልሱም። በዚህም የተነሳ ከኢህአዴግም ሆነ ከኦህዴድ በኩል ስለ ጉዳዩ መረጃ ማግኘት አልተቻለም። ኮማንድ ፖስቱ መረጃ መስተትን በመከልከሉ የተነሳ ይህ ሊሆን ችሏል።

አብረን መሄድ አንችልም። ይገሉናል። የደበድቡናል። በየመንደራችን ቤት ድረስ እየገቡ እርምጃ ይወስዱብናል። ምንም ማደርግ አልቻልንም። በዚህ ሁኔታ እንዴት አገር ይረጋጋል? ህዝብ ላይ በጅምላ ይተኩሳሉ። በጥይት ያቆስላሉ። አዛውንት፣ ህጻን ትልቅ አይሉም። ጠይቆ ለመረዳት ጊዜ አይሰጡም። ማስረዳትም አይቻልም። የሚሰሙምም አይመስሉም። ደም የጠማቸው ናቸው። … ሲሉ ስሜታቸውን የገለጹ አሉ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጊታቸው አምባዬ በራሱ አባላት ተቃውሞ ላጋተመው የኢሃዴግ ፓርላማ እንዳሉት ” የፌደራልና የክልል መንግስታት በመደበኛው የህግ አግባብ አገሪቱን መምራት አልቻሉም” እንደሳቸው አባባል ወታደራዊ ኮማንድ ፖስት አገሪቱን የመምራቱን ስራ ተረክቧል። ይህ ወታደራዊ ሃይል በይፋ አገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ቀን አንስቶ የዜጎች መሞት የአገሪቱን ሁኔታ እያወሳሰበው መሆኑንን የሚጠቁሙ መረጃዎች በሚወጡበት በአሁን ሰዓት ነው አዲስ ትዕዛዝ የተላለፈው።

ከዛሬ ጀምሮ በኦሮሚያ የተጠራው አድማ ስራ ላይ መዋሉን ከሰልፉ ጋር ግንኙነት ያላቸው እየዘገቡ ነው። በምስል አስደግፈው ከተሞች ግብይትና እንቀስቃሴ ማቆማቸውን እያሳዩ ነው። ስም ጠርተው ቦታዎችን በመዘርዘር መረጃ እያሰራጩ ነው። አብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች የኢንተርኔት መቋረጥ በመኖሩ የግንኙነት ችግር መፍጠሩንም እነዚሁ ክፍሎች እየተናገሩ ነው።

በማህበራዊ ገጾች አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ በመስራት ጫና የፈጠሩት የለውጥ አቀንቃኞች ያሉትና ያሰቡትን ሁሉ ሲያሳኩ በተደጋጋሚ በማሳየታቸው የዛሬውን የአድማ ዘመቻ ተከትሎ የወታደራዊ ኮማንድ ፖስቱ ለሕዝብ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ” ለሚነዙ ውዥንብሮችን ቅስቀሳዎች ተኩረት አትስጡ” ሲል ያሳሰበው መግለጫ ” … በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ሊደረጉ የማይገቡ ተግባራትን በማውጣት ዜጎች እንዲያውቁት በማድረጉን የተነሳ መመሪያውን የተላለፈ ወይም የጣሰ ግለሰብ ላይ ኮማንድ ፖስቱ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል” የሚል ማስጠንቀቂያ በመመሪያው ላይ ተካቷል።

የቀድሞውን የክልከላ ዘርዘር በማስታወስ የተላለፈው አዲስ የወታደራዊ ኮማንድ ፖስቱ ትዕዛዝ ከዚህ የሚከተለው ነው 

ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ ለሚነዙ ቅስቀሳዎች ትኩረት ሳይሰጥ መደበኛ ህይወቱን ያለ ስጋት እንዲመራ ኮማንድ ፖስቱ አሳሰበ

ህብረተሰቡ ለሚነዙ ውዥንብሮችና ቅስቀሳዎች ትኩረት ሳይሰጥ መደበኛ ህይወቱን እንዲመራና የዕለት ተዕለት ተግባሩን ያለስጋት እንዲያከናውን ኮማንድ ፖስቱ አሳሰበ።

ከሰሞኑ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዜጎችን የተረጋጋ ህይወት ለብጥብጥና ሁከት ለመዳረግ ያለመ መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገፆች አማካይነት መሰራጨቱን አስመልክቶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ማሳሰቢያ መስጠቱን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

ኮማንድ ፖስቱም ሆን ተብሎ ህገ ወጥ ቅስቀሳ በማድረግ የዜጎችን ሰላማዊ ህይወት ለማወክና ስጋት ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑንን በመጥቀስ፥ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ያለምንም ስጋት መደበኛ ተግባሩን እንዲያከናውን ገልጿል።

መንግስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ሊደረጉ የማይገቡ ተግባራትን በማውጣት ዜጎች እንዲያውቁት ማድረጉን የተነሳ ሲሆን፥ መመሪያውን የተላለፈ ወይም የጣሰ ግለሰብ ላይ ኮማንድ ፖስቱ አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል መገለጹም ይታወሳል።

በመሆኑም የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ማስተጓጎልና ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብትን የሚገድቡ እንቅስቃሴዎች፣ የህዝብ መገልገያ ተቋማትን፣ የንግድ ስራዎች ወይም ሱቆችን፣ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማትን መዝጋት ወይም ምርትና አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረግ ኮማንድ ፖስቱ ባወጣው መመሪያ ተከልክሏል።

ከዚህ ባለፈም ከስራ ቦታ ያለ በቂ ምክንያት መጥፋት ወይም ስራ ማቆምና ስራን መበደል፣ በህዝብና በመንግስት ተቋማት እንዲሁም በግል ንብረት ላይ በማንኛውም መንገድ ጉዳት ማድረስ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን በኮማንድ ፖስቱ ዝርዝር መመሪያ ላይ መስፈሩም የሚታወስ ነው።

የህዝብና የዜጎች ሰላምና ጸጥታን ለማስከበር ሲባል ከኮማንድ ፖስቱ ፍቃድ ወይም እውቅና ውጭ ማናቸውንም ሰልፎችና የአደባባይ ስብሰባዎች ማድረግም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ የተከለከለ ነው ብሏል።

በትምህርት ቤቶችና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደቶችን የማወክ፣ አድማ ማድረግ፣ የትምህርት ተቋማትን መዝጋት፣ እንዲዘጉ ቅስቀሳ ማድረግ ወይም የትምህርት ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት ማድረስ የተከለከለ መሆኑን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር መመሪያ ተደንግጓል።

አድማና ህገ-ወጥ ተግባር መፈጸም ወይም እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ይፋዊም ሆነ ድብቅ ቅስቀሳ በማናቸውም በኩል ማድረግ ጽሁፍ ማዘጋጀት፣ ማተምና ማሰራጨት፣ ትዕይንት ማሳየት፣ በምልክት መግለጽ ወይም መልዕክትና በማናቸውም መንገድ መግለጽና ይፋ ማድረግ የተከለከለ መሆኑንም ተጠቅሷል።

ፍቃድ ሳይኖር ማንኛውንም ህትመት ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባትና ወደ ውጭ ሃገር መላክ፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ፣ በጽሁፍ፣ በቴሌቪዥን በሬዲዮ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በሌሎች የግንኙነት ዘዴዎች መለዋወጥም የተከለከለ መሆኑ በመመሪያው ሰፍሯል።

የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት፣ ዝውውርና ስርጭትን ማስተጓጎልም በጥብቅ የተከለከለ መሆኑም ይታወቃል።

ህግ አስከባሪ አካላትና የድርጅት ጥበቃዎች አስቸኳይ ጊዜ አዋጁና መመሪያውን ለማስፈጸም የራሳቸውንና የሰዎችን ህይወትና ንብረት በመጠበቅ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ሃይል ሊጠቀሙ እንደሚችሉም በመመሪያው ተጠቅሷል።

በግልና የመንግስት ተቋማት ውስጥ አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝና ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ የህግ አስከባሪ አባላት በእነዚህ ተቋማት ውስጥ መግባት አስፈላጊ ከሆነም መቆየት እንደሚችሉ ዝርዝር መመሪያው ላይ በግልፅ ሰፍሯል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *