‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር፤ ለክቡር አቶ ተፈራ ደግፌ

ለኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረ ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጋሩ፣ ለሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራቶች፡- ቀጣዮን ብሄራዊ የወጣቶች ተግባራዊ የትግል አቅጣጫ ማሳየት ይጠበቅባችኃል፡፡ ከከ2003 እስከ  2010 ዓ/ም ባሉት ዓመታት ብሔራዊ ባንክ ብዙ ቢሊዩን ብር ሱዳን አሳትሞ፣ በሃገር ውስጥ ብሩን ሞቅ አድርጎ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ማሰራጨቱ ሃገሪቱን ለከፍተኛ ውድቀት እንደሚዳርጋት የምጣኔ ኃብት ምሁራን በጋራ ጥናታቸው በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡

  • ‹‹ከ2003 እስከ 2007 ዓ/ም የባንክ የውጭ ምንዛሪ ሀብት ከአገር ውስጥ ብድር ሀብት ጋር ሲነፃፀር፣በ2003 ዓ/ም ከነበረበት 41 በመቶ በየዓመቱ ቀንሶ በ2007ዓ/ም ዘጠኝ ነጥብ አምስት በመቶ ብቻ ሆኖል፡፡››…‹‹ይህ የውጭ ምንዛሪ ሃብትና የአገር ውስጥ ብድር ሀብት ንፅፅር ሁኔታ በብር የውጭ ምንዛሪ መጣኝ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የአገሪቱ ቁልል የውጭ ዕዳ ክምችትም (Outstanding Debt Stock) ይጨምራል፡፡›› ብዙ ሰዎች ስለ ጥሬ ገንዘብ ሲነገር በገበያ ውስጥ የሚዘዋወርን ጥሬ ብር ማለት ሊመስላቸው ይችላል ነገር ግን በንግድ ባንኮች ቆጣቢዎች የሚያስቀምጡት ተቀማጭ ወይም ንግድ ባንኮች በተቀማጩ ላይ ተመርኩዘው ተቀማጩን አርብተው በማበደር የሚፈጥሩት ብድርም ጥሬ ገንዘቦች ናቸው፡፡
  • በብሔራዊ ባንክ የጥሬ ገንዘብ ፖሊሲ የተዛባ በመሆኑ ምክንያት በሃገሪቱ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ተከስቶል፡፡ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በሃገሪቱ ገበያ ውስጥ የሚዘዋወር ጥሬ ብር በ2003 ዓ/ም 32.6 ቢሊዩን ብር ሲያቀርብ፣በ2007 ዓ/ም 60.5 ቢሊዩን ብር ማለትም 54 በመቶ ሞቅ አድርጎ በገበያው ውስጥ ዘርቶታል፡፡
  • 2002ዓ/ም እስከ 2007ዓ/ም የበጀት አመት የአምስት ኣመት እድገት አማካይ እድገት በመቶኛ 29.0% ‹‹የጥሬ ገንዘብ አቅርቦቱን እድገት መጣኝ ቢመጣም በአካፋዩ መነሻ መተለቅ ምክንያት እንጂ፣የአቅርቦቱ መጠን እየጨመረ እንደመጣ እናያለን፡፡ የእርግጠኛ ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ዕድገትን በየአመቱ 11 በመቶ ይሁን ብለን ተቀብለን እንካ፣ ከአምስቱ አመት አማካይ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት እድገት 29 በመቶ ውስጥ 11 በመቶው ለምርት ዕድገት ዋለ ብንል ቀሪው 18 በመቶ የዋለው ለዋጋ ንረት ነው፡፡››
  • 2010ዓ/ም ‹‹በአገሪቱ ለሚካሄደው ልዩ ልዮ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መንግሥት በዕቅድ የያዘው የገንዘብ አቅርቦት መጠን ከኢኮኖሚው አኮያ የ28 በመቶ ድርሻ ነበር፡፡›› ‹‹ይሁንና የኢንቨስትመንት ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ ሳቢያ ከታቀደው የገንዘብ አቅርቦት በላይ ከፍተኛ የገንዘብ ፍላጎት ተፈጥሮል…በመሆኑም ከኢኮኖሚው የ40 በመቶ በላይ ድርሻ ያለው የገንዘብ አቅርቦት እንዲሆን ለማድረግ ባንኩ መገደዱን አስታውቀዋል፡፡›› በዚህም ምክንያት ብሔራዊ ባንክ ብዙ ቢሊዩን ብር ሱዳን ውስጥ በሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ አሳትሞ፣ በገበያው ውስጥ ወረቀቱን ሞቅ አድርጎ ገበያው ውስጥ መዝራቱን አምኖል!!!
  • በ2010ዓ/ም የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለግብይት ከሚያቀርባቸው ቡና ፣ሰሊጥና ቦለቄ ምርቶች 40 ሽህ ቶን ቀንሶል፡፡ ዋናው ምክንትም በሃገሪቱ የተከሰተው ህዝባዊ አንቢተኝነትና ተጋድሎ መሆኑ ታውቆል፡፡በየካቲት ወር ግብይት ካለፈው ጥር ጋር ሲነፃፀር 28 በመቶ ቀናሽ አሳይቶል እንዲሁም የየካቲት ወር ግብይት በታህሣስ ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ከ105 ሽህ ቶን ወደ 66 ሽህ ቶን ወይም 38 በመቶ ቀንሶል፣ ይህም በገንዘብ ሲሰላ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ቅናሽ ታይቶበታል፡፡ በአጠቃላይ ሃገሪቱ በውጭ ንግድ ገቢዋ በጣም እንደሚቀንስና የውጪ ምንዛሪ አግኝታ እዳዋን ለመክፈልና የእዳ ጫናዋን ለመቀነስ እድሎ የመነመነ ነው፡፡
  • በኢትዮጵያ አማካይ አመታዊ የሸቀጣ ሸቀጦች ምርቶች የዋጋ ግሽበት በ2001 ዓ/ም  (25.5 በመቶ )፣ 2005ዓ/ም (23.0በመቶ )እና 2009ዓ/ም (9.7 በመቶ) መድረሱን መረጃው ያሳያል፡፡ በ2010 ዓ/ም ሁለት አሃዝ ከ10እስከ 15.6 በመቶ የዋጋ ንረት መከሰቱን ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ አማካይ የውጭ ምንዛሪ ምጣኔ በ2001 ዓ/ም  (1 ዶላር በ 9.6 ብር )፣ 2005ዓ/ም (1 ዶላር በ 17.7 ብር ) እና 2009ዓ/ም (1 ዶላር በ 21.8 ብር ) መድረሱን መረጃው ያሳያል፡፡ በ2010ዓ/ም  ብሄራዊ የውጭ ምንዛሪ ምጣኔ 15 በመቶ በመጨመር  (1 ዶላር በ 26.96 ብር ) ሲሆን  በጥቁር ገበያ (1 ዶላር በ 33.50 ብር ) በመመንዘር ላይ ይገኛል፡፡
  • በ2010ዓ/ም መንግሥት በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመርያው ስድስት ወራት ከዕርዳታና ከብድር346 ቢሊዮን ብር ማግኘቱን፣ ከዚህ ውስጥ 50.443 ቢሊዮን ብር እንደተለቀቀለት አስታወቀ፡፡ በመጀመርያው ስድስት ወራት ከዓለም አቀፍ የልማት ተቋማት (መልቲ ላተራል) በብድር 20.971 ቢሊዮን ብር፣ ከዕርዳታ 34.58 ቢሊዮን ብር በድምሩ 55.55 ቢሊዮን ብር አዲስ ዕርዳታና ብድር መገኘቱን ይፋ አድርገዋል፡፡

የወያኔ ፋሽስታዊ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ኮማንድ ፖስት በቦረናና ሞያሌ ዜጎች ላይ የፈፀመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ለብዙ ሰው ሞት ፣ መቁሰል፣ እስራትና ለ50 ሽህ ዜጎች ስደት ተዳርገዋል፡፡ የወያኔን አጋዚ ጦር ለመከላከል የመንገድ መዝጋት፣ የድልድይ መስበር፣ የነዳጅ አመላላሽ መኪኖች ማጥቃት፣ የወያኔ የኤሌትሪክ ትራንስፎርመሮችና ከፍተኛ ኤሌትሪክ ቮልቴጅ ተሸካሚ ወደ ሱዳን፣ ኬንያ ወዘተ በዶላር የሚሸጠው ኮረንቲን በማምከንና በመምታት ኢኮኖሚውን ማሽመድመድ ይቻላል፡፡ የቄሮ ትግል በብሄራዊ መልክ እንዲቀጣጠል በማድረግ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ኃላፊነቱን መወጣት ይጠበቅበታል፣ የነዳጅ ቦቴዎች የመንቀሳቀስ እገዳ፣ የመንግሥት መኪኖች የመንቀሳቀስ እገዳ  በማድረግ  የወያኔ የኢኮኖሚ  አከርካሬ በመምታት  ኢኮኖሚውና ሽባ በማድረግና የጎረቤት ሃገር የኮረንቲ ሽያጭ ገቢን በማምከን የወያኔን አገዛዝ ማሽመድመድ ይቻላል፡፡  በኢትዮጵያ ህብረ ብሄራዊ  ትግል ማድረግና መምራት የዚህ ዲጂታል ቴክኖሎጅ ወጣቶች ታሪካዊ ግዴታ ነው፡፡ ወጣቶች የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት፣ የጥላቻ ፖለቲካን ማስወገድ፣ የዘር ፍጅት እንዳይቀሰቀስ ማስተማር፣ እድሜቸው የደረሰ የፖለቲካ አመራሮች በወጣቶች መተካት! የፖለቲካ አመራሮችና የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላቶች ቃል ኪዳናቸውን በማክበር ሀገር ቤት ደፍሮ ገብቶ ከህዝብ ጋር አብሮ መታገል ይጠበቅባቸዋል፡፡  የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››በማወጅና የኮማንድ ፖስት በማቆቆም ግድያ ጀምረዋል ህዝቡ  ‹‹ሞት መጣ›› ቢለት ‹‹አንዱን ግባ በለው!!!›› ብሎችሆል፣ ህፃናት ለሚገድሉ የወያኔ መንግሥትና የአጋዚ ጦር ነፍሰ ገዳዮች!!! በቦረናና ሞያሌና በመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ  ለፈፀማችሁት ወንጀል ፍርድ ስትቀርቡ ህዝቡ ቤቱ አይገባም!!! የወያኔ መንግሥት 7.88 ሚሊዮን ህዝብ በርሃብና ቸነፈር ላይ መሆኑን ለዓለም አቀፍ ህብረተሰብ እርዳታ እንዲረጉለት ተማፀነ፡፡ በሃገር ውስጥ 2 ሚሊዮን ህዝብ ከቀየው ተፈናቅሎ ይገኛል በቅርቡ በሱማሌ ክልል ይኖሩ የነበሩ አንድ ሚሊዮን የኦሮሞ ህዝብ ከዛ በፊትም የአማራ፣ ጋምቤላ፣ የደቡብ ወዘተ ህዝብ እንዲፈናቀል ያደረገው የወያኔ ዘረኛ ፖሊሲ ምክንያት ነው፡፡

እርኩም  ማታ ማታ ጠግቦ ወደ ጎጆው ሲገባ  ‹‹ቤት ሰርቼ! ቤት ሰርቼ!›› ይላል ጠዋት በማለዳ ሲነሳ ደግሞ ‹‹ ሆድ ይብሳል! ሆድ ይብሳል!›› እያለ ምግብ ፍለጋ ይሄዳል፡፡ እርኩም ቤት ሳይሰራ፣ ይመሻል ይነጋል፣ ዳግም ይመሻል ይነጋል፡፡ 30 ሚሊዮን ወጣቶች በሥራ አጥነት እድሜቸውን ይገፋሉ፣ እነዚህ ወጣት ጡረተኞች ሲመራቸው፣ የቤተሰብ ሸክም መሆኑ ሲሰማቸው፣ ዘመድና ወገን ሲከፋባቸው እናት ሃገራቸውን ተሰናብተው በጠዋት በማለዳ ስደት ይሄዳሉ፣ በእግራቸው ተራራ ይወጣሉ ይወረዳሉ፣ የሳህራ በርሃን አቆረጠው፣ ሜዲትራንያ ባህርን በታንኮ ቀዝፈው ይጎዛሉ፡፡ በህይወት የተረፉም፣ በሞት የተለዮም እናት አገራቸው ያበረከተችላቸው ፀጋ ይሄ ብቻ ነው፡፡  ከዚህ በኃላ ወጣቶች በሃገራቸው ሰርተው ለመቀየር የወያኔን ሥርዓት አንኮታኩተው በመጣል ለትግል ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ይች ሃገር የእነሱም ናት፣ ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት፣ የፖለቲካ ነፃነት የለም፡፡ ስለዚህ ፍህታዊ የኃብት ክፍፍል፣ የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ነፃነት፣ የወያኔ መንግሥታዊ ዘርፍ ኢፈርትና ሜቴክ፣ ጥረት፣ ዲንሾ፣ ወንዶ የመሳሰሉት    የፖለቲካ ፓርቲዎች ከንግዱ ዘርፍ እስካልወጡ፣ አምራቹን ኃይል እንደ ኮሶ የሚጣባ ተዋስያን በመሆን የሃገር ኢኮኖሚ የሚያቆረቁዝ፣ ህዝቡን በድህነት አረንቆ የሚዶል፣ ርሃብ፣ ድህነትና ድንቁርና የሚዘራ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዘርፍ ቀውስ ፈጣሪ የወያኔ ፖሊሲና ስትራቴጅ መሆኑን ተገንዝበዋል፡፡ ከህወሓት አገዛዝ የወረስንው  ውርስ ይሄን ብቻ ነው ስንጠይቅና ስንቃወም እስር፣ ግርፋት፣ ግድያ ይፈፀምብናል፡፡ የእናንተ አያትና ቅድመ አያት ከጣልያን ፋሽስቶች ተዋግተው ነፃነት አቀዳጅተዋችኃል፡፡ ለእናንተ ህይወታችውን ሰውተው፣ ደማቸውን አፍሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቦችሁ ሃገር ናት፡፡  እናንተ ለእኛ ያወረሳችሁን ኢትዮጵያ የህዝባች እስር ቤት ናት!!!  የዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመን ወጣቶች፣  የኦሮሞ ቄሮ፣ የአማራ ፋኖ፣ የደቡብ አቦሸማኔ (የጉራጌ ዘርማ)፣ የሰሜኑ አናብስት!!! ጥያቄ  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በብሄራዊ ትግላችን ለማንሳት ነው፡፡ ዘመኑ የዴሞክራሲ እንጅ የዘር አይደለም፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ችግራችንን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት እንጅ በ‹‹አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በማወጅ አይፈታም!!! እንላለን፡፡ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ችግራችንን በእውቀት እንጅ በጠመንጃ አፈሙዝ አይፈታም፡፡

‹‹ብሔራዊ ባንክ ብዙ ቢሊዩን ብር ሱዳን ውስጥ ሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ አሳትሞ፣ በገበያው ውስጥ ወረቀቱን ሞቅ አድርጎ ዘርቶታል!!!››

ሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ፤ Sudan Currency Printing Press (SCPP)

Sudan Currency Printing Press (SCPP) is a private enterprise of limited liability established in May 1994 in accordance with the 1925 company law. The Company had started the real production at the end of 1994. የሱዳን የገንዘብ ማተሚያ ፕሬስ፤ኃላፊነቱ ተወሰነ የግል ኢንተርፕራይዝ በግንቦት 1994 እኤአ መጨረሻ ላይ በሃገረ ሱዳን የተመሰረተ የገንዘብ ማተሚያ የግል ፋብሪካ ነው፡፡ በምን መለኪያና መሥፈርት የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ የብር ኖቶችና ቼክ እንዲሁም የአገር ግዛት ሚኒስትር መስሪያ ቤት (Ministry of Interior) ፓስፖርቶችና፣ከሃገር መውጫና መግቢያ ቪዛ፣ፓስፖርት ላይ የሚመታ የሚያብለጨልጭ የቪዛ ስቲከር ብሄራዊ ዶክመቶች፣ መታወቂያ ካርዶችና የተለያዩ የመታወቂያ ዶክመንቶች የህትመት ሥራ ለአዲስ ጀማሪው ካንፓኒ ተሠጠ፡፡ የሃገራችን ሉዓላዊነትና የህዝባችን ደህንነት በሱዳን የግል የገንዘብ ኖቶችና ፓስፖርት በሚያትም ካንፓኒ እግር ስር ወደቀ፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች  መንግሥት በሃገሪቱ ታሪክ ሆኖ የማያውቅ ሚስጢራዊ የህትመት ሥራ ለሱዳን የግል ካንፓኒ መስጠት ውሎ አድሮ ከሱዳን በተጣሉ ጊዜ ሀገራችን ከፍተኛ ኪሣራ ያስከትላል፡፡  ወያኔ የኢትዩጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች በሱዳን ምድር እንዳይገቡ ለማድረግ የሃገሪቱን መሬት፣ የግብርና ምርትና የቁም እንሰሳት፣ የወርቅ ማዕድን ኃብት ወዘተ በህገወጥ የድንበር ንግድ ከሱዳን መንግሥት ጋር አብሮ ይዘርፋል፡፡ የሱዳን የግል ካንፓኒ የኢትዩጵያ ብር ኖቶች፣  ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ የማተም ሚስጢር ለምን ለህዝብ ይፋ አልሆነም፡፡ የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ፤ዋና ተግባራት ውስጥ፤ የብር ኖቶችንና ሣንቲሞችን ማሳተም፣ እንደ መንግሥት ወኪል ሆኖ መስራት፣ የውጭ ምንዛሪ ምጣኔን መወሰንና መቆጣጠር ሃላፊነት በህዝብ ቃል የገባበት ሙያዊ ሥነ-ምግባር በንዋይ ፍቅር ተሸጦ ቢያዩ እውቁ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ክቡር አቶ ተፈራ ደግፌ እውቁ ኢኮኖሚስት ፕሮፊሰር እሸቱ ጮሌ ምን ይሎችሁ፡፡ ሞት አይቀር፣ስም አይቀበር!!!

Enterprise to Print Ethiopian Birr, Electronic Passport, Cheque: The Ethiopian Herald (Addis Ababa), 6 March 2016፡ By Solomon Mekonnen

The Berhanena Selam Printing Enterprise (BSPE) Friday announced plan to cooperate with Sudanese Currency Printing Press to build capabilities to print Ethiopian Birr, electronic passport and cheque locally. Speaking at a Security Printing Technical Conference, Enterprise CEO Teka Abadi said: “We believe the printing of currency, electronics passport and cheque locally will have great role in saving hard currency that our country spends. It is also necessary to localize them for economic and security reasons.” According to him, the win- win relationship with Sudan Currency Printing Press and Koenig & Bauer AG (KBA) Notasys will help each party to achieve their goals. “The printing industry is rapidly growing and the world is continuously applying new technologies from time to time. This makes the competition fierce and puts our local printing houses in a very challenging situation. We need to work together with companies engaged in security printing area,” Teka said. Sudan Currency Printing Press General Manager Assistant Omer Ahmed Mokhtar on his part said that his company is committed to transfer know how through training, maintenance and development and other areas with BSPE. The two Enterprises have signed a Memorandum of Understanding to work together in the fields of technical support, training, capacity building and in areas that could help to build institutional capacities.  Copyright © 2016 The Ethiopian Herald.  Distributed by AllAfrica Global Media (allAfrica.com).

የኢትዩጵያ ብር ኖቶች ማተም፣ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ የሚያትም ኢንተርፕራይዝ

ኢትጵያ ሄራልድ ጋዜጣ (አዲስ አበባ) 6 ማርች 2016 በሰሎሞን መኮንን

የብርሃነ ሰላም ማተሚያ ቤት ኢንተርፕራይዝ ከሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ፤ Sudan Currency Printing Press (SCPP) ጋር በመተባበርና ችሎታ ለማዳበር ብሎም የኢትዩጵያ ብር ኖቶች ማተም፣ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ በሃገር ውስጥ ለማተም ስምምነት ተደርጎል፡፡ የደህንነት ህትመትና የቴክኒካል ኮንፍረንስ ስብሰባ ላይ ቺፍ ኤክስኪዩቲፍ ኦፊሰር ተካ አባዲ በተናገሩት መሠረት ‹‹ የኢትዩጵያ ብር ኖቶች ማተም፣ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ በሃገር ውስጥ ማተም ውጪ ምንዛሪ ወጪን ለማዳንና ለኢኮኖሚ እድገትና ለሃገር ሉዓላዊነት ደህንነት በጣም አስፈላጊ ምክንያት ናቸው፡፡›› ከሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ እና ኮኒግና ባወር ኤጂ ኢንተርፕራዞች ጋር ተባብሮ መስራት ዓላማችንን ለማሳካት ይጠቅማል፡፡  የሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ ምክትል ጀነራል ማነጀር ኡመር አህመድ ሙክታር የህትመት ካንፓኒያቸው ከብርሃነ ሰላም ማተሚያ ቤት ኢንተርፕራይዝ ጋር እውቀት ለማጋራት፣ በስልጠና ክህሎት ለማዳበር፣ ጥገናና የልማት ሥራዎች፣ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ፣ የሰው ኃይል ግንባታ ክህሎት ለማሳደግና በሌሎች የህትመት ዘርፎች አብሮ በጋራ ለመስራትና ግዳጃቸውን እንደሚወጡ በስምምነቱ ላይ ገልፀዋል፡፡

የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ የኢትዩጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረቱ በሃገሪቱ ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም በግብርና፣በኢንዱስትሪና የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ አስፈላጊውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመተግበር ለህዝብ ብልፅግናና ለኢኮኖሚ እድገት የሚሆን ፖሊሲ መንደፍ ነው፡፡ የኢኮኖሚ ፖሊሲው ስርዓት በግብርና ታክስ፣  በመንግሥት በጀት፣ በገንዘብ አቅርቦት፣ የወለድ መጠን፣ እንዲሁም የሠራተኛ /የጉልበት ገበያ፣ ብሄራዊ ኃብትና  ሌሎች ኢኮኖሚ ዘርፎች በማበልፀግ እንዲሁም  የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ ከፍተኛውን ሚና እንዲጫወት በማድረግ፣ የመንግስት ጣልቃ ገብነት በተወሰኑ የኢኮኖሚ ዘርፍ በተለይም  በማዕድን ዘርፍ (በወርቅ ፣ታንታለም፣ ፖታሽ ወዘተ) ውስጥ ብቻ እንዲወሰን ማድረግ አስፈላጊ ነበር፡፡ ሆኖም የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በመንግሥታዊ ድርጅቶች (አየር መንገድ፣ ቴሌኮም፣ ባቡር፣ መርከብ፣ መብራት ኃይል፣ ስኮር ኮርፖሬሽን ወዘተ) በመፈልፈልና የፓርቲ የንግድ ካንፓኒዎችን (ኢፈርት፣ ሜቴክ፣ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ወዘተ) የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ እንዳይሰራ በሩን ዘግተውበታል፡፡ የአንድ አገር መንግሥት  የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ዘርፈ ብዙ ፈርጆች በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ፤ እነሱም ፊሲካል ፖሊሲና ሞኒተሪ ፖሊሲ በመባል ይታወቃሉ፡፡

ፊሲካል ፖሊሲ፤(Fiscal Policy) የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት የግብርና ታክስ እንዲሁም የመንግሥትን ወጪ ሥርዓትን አፈፃፀም ፖሊሲን ያሳያል፡፡ የመንግሥትን ገቢና ወጪና የበጀት ጉድለትና ትርፍ ያሰላል፡፡ የመንግስትና የታክስና የግብር ገቢ አሰባሰብ ሥርዓትና ፖሊሲን እንዲሁም የመንግሥታዊ ዘርፍ ወጪን ይቆጣጠራል፡፡  የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥትና የብሄራዊ ባንክ ፊሲካል ፖሊሲ፤የግብርና ታክስ ስርዓት ፍትሃዊ ባለመሆኑ ምክንያት በሃገሪቱ ያስከተለውን ህዝባዊ አመፅ መመልከት ብቻ በቂ ነው፡፡

ሞኒተሪ ፖሊሲ፤(Monetary Policy) የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥትና ብሄራዊ ባንክ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የገንዘብ ዝውውር፣ገንዘብ ፍላጎትና አቅርቦት በመቆጣጠር የዋጋ ግሽበት መከላከልና የወለድ መጠን በመወሰን የገንዘብ ሥርዓት የሚቆጣጠርበት ሲሆን ከዓለም ዓቀፍ ኢንስቲቲውሽን ማለትም ከዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ እንዲሁም የሃገራቱን የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የማህበረሰብ ልማት ፖሊሲዎች ጋር አዛምዶ መስራት ያካትታል፡፡ ሞኒተሪ ፖሊሲ ከሚያካትታቸው ውስጥ፤የገቢ ፖሊስ፣የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርት የዋጋ ቁጥጥርና የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችትን ያካትታል፡፡‹‹የዓለም ባንክ የኢትዩጵያን ብር የማርከስ እሰጥ አገባና የአሥራ አንደኛው ሰዓት ንስሐ››1 በሚለው ጥናታዊ ፁሁፉ አቶ ጌታቸው አሰፋው በሪፖርተር ጋዜጣ የብሄራዊ ባንክ ሥራና ሃላፊነትን ተንትኖ ከማስረጃ ጋር ያቀረበውን ፅሁፍ በመጥቀስ አንባቢዎች በቀላሉ መረዳት ይችላሉ፡፡ ‹‹የብሔራዊ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች የሚያጠነጥኑት በሁለት ዓይነት የፖሊሲ መሣሪያዎች በመንግሥት ገቢና ወጪ የበጀት ፖሊሲና በጥሬ ገንዘብ አቅርቦት ፖሊሲ ላይ ነው፡፡›› የጥሬ ገንዘብ ፖሊሲ ‹‹አስፋፊ የጥሬ ገንዘብ ፖሊሲ (Expansionary Monetary Policy) በሕግ ገደብ (By the Rule of the Law) ካልተገደበ፣በልክ ካልተመጠነና በዘፈቀደ (By Discreation) ካደገ በአጭር ግዜ ውስጥ ምርትንም ቢያሳድግ፣በረጅም ጊዜ ግን ውጤቱ ዋጋን ማናርና ጥሬ ገንዘቡን ዋጋ በማሳጣት የብራችንን የምንዛሪ መጣኝ ማርከስ ነው፡፡›› በባንክ ሁለት ዓይነት የገንዘብ ኃብቶች አሉ እነሱም አንደኛው የውጭ ምንዛሪ ኃብት ሲሆን ሁለተኛው የአገር ውስጥ ብድር ኃብት ናቸው፡፡

{1} 2003ዓ/ም በጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 55.5 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 135.5 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 41.0%

{2} 2004ዓ/ም በጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 39.8 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 189.1 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 21.0%

{3} 2005ዓ/ምየበጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 45.6 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 233.4 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 19.5%

{4} 2006ዓ/ምየበጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 56.1 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 299.7 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 18.7%

{5} 2007ዓ/ምየበጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 37.5 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 393.5 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 9.5%

ከ2003 እስከ  2007 ዓ/ም የባንክ የውጭ ምንዛሪ ሀብት ከአገር ውስጥ ብድር ሀብት ጋር ሲነፃፀር፣በ2003 ዓ/ም ከነበረበት 41 በመቶ በየዓመቱ ቀንሶ በ2007ዓ/ም ዘጠኝ ነጥብ አምስት በመቶ ብቻ ሆኖል፡፡›ይህ የውጭ ምንዛሪ ሃብትና የአገር ውስጥ ብድር ሀብት ንፅፅር ሁኔታ በብር የውጭ ምንዛሪ መጣኝ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የአገሪቱ ቁልል የውጭ ዕዳ ክምችትም (Outstanding Debt Stock) ይጨምራል፡፡›› ብዙ ሰዎች ስለ ጥሬ ገንዘብ ሲነገር በገበያ ውስጥ የሚዘዋወርን ጥሬ ብር ማለት ሊመስላቸው ይችላል ነገር ግን በንግድ ባንኮች ቆጣቢዎች የሚያስቀምጡት ተቀማጭ ወይም ንግድ ባንኮች በተቀማጩ ላይ ተመርኩዘው ተቀማጩን አርብተው በማበደር የሚፈጥሩት ብድርም ጥሬ ገንዘቦች ናቸው፡፡   ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥትና ለንግድ ባንኮች የሚሰጠውን ብድር ከመቆጣጠርም በላይ፣በጥሬ ገንዘብ አቅርቦት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱትን የንግድ ባንኮችን እንቅስቃሴ መቆጣጠር ይገባዋል፡፡ በኢትዩጵያ ለጥሬ ገንዘብ አቅርቦት መጠን ከፍተኛውን አስተዋፅኦ ያደረገው በብሔራዊ ባንክ የቀረበው በገበያ ውስጥ የሚዘዋወረው ጥሬ ብር መሆኑን በሚከተለው ቀላል አገላለጽ ማስተዋል ይቻላል፡፡

{1} 2003 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 32.6 ቢሊዩን ብር + የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 112.8 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 145.4 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 32.6/112.8 X100=29.0%

{2} 2004 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 38.5 ቢሊዩን ብር + የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 151.0 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 189.5 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 38.5/151.0 X100=26.0%

{3} 2005 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 45.7 ቢሊዩን ብር  + የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 189.6 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 235.3 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 45.7/189.6 X100=24.0%

{4} 2006 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 53.2 ቢሊዩን ብር + የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 244.5 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 297.7 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 53.2/244.5 X100=22.0%

{5} 2007 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 60.5 ቢሊዩን ብር + የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 310.7 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 371.2 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 60.5/310.7 X100=20.0%

  • በብሔራዊ ባንክ የጥሬ ገንዘብ ፖሊሲ የተዛባ በመሆኑ ምክንያት በሃገሪቱ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ተከስቶል፡፡ ባንኩ በሃገሪቱ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት መጠን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማድረጉን ከገላጭ ሠንጠረዡ ላይ ማስተዋል ይቻላል፡፡ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በሃገሪቱ ገበያ ውስጥ የሚዘዋወር ጥሬ ብር በ2003 ዓ/ም 32.6 ቢሊዩን ብር ሲያቀርብ፣በ2007 ዓ/ም 60.5 ቢሊዩን ብር ማለትም 54 በመቶ ሞቅ አድርጎ በገበያው ውስጥ ዘርቶታል፡፡
  • በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር ጥሬ ብር አቅርቦት የምንዛሪ መጣኙን አዛብቶታል፡፡ በዓለም ታላላቅ ከተሞች እንካን ባልታየ ዓይነት በአዲስ አበባ የአንድ ካሬ ሜትር መሬት ዋጋ ሥስት መቶ ሃምሳ አምስት ሽህ ብር ደርሳል፡፡ በካንትሪ ክለብ፣ የአንድ ቪላ ቤት ዋጋ 10 ሚሊዩን ብር ደርሶል፡፡ የአንድ እንቁላል ዋጋ 3 ብር ከሰባ አምስት፣ አንድ ኪሎ ሙዝ፣ብርቱካን ዋጋ 25 ብር፣ አንድ ኪሎ ሥጋ ዋጋ 250 እስከ 300 ብር ወዘተ በአጠቃላይ ምርት ሳያድግ ብር ማተም፣ ብር ወረቀት እየሆነ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡ ህዝቡ ለዳቦ፣ለዘይት፣ለስኳር ይሰለፋል!፣ ህዝቡ ለታክሲ፣ለባቡር፣ለነዳጅ ይሰለፋል! ህዝቡ ለስድት፣ ለሞት ይሰለፋል!!! የኢትዩጵያ ሕዝብ በአንድ ድምፅ ሁላችንንም ሁሌም ማታለል አይቻልም ይላል፡፡ በዚህም የተነሳ በሃገሪቱ ውስጥ ምን እንደተከተለ ለማወቅ ስለ ጥሬ ገንዘብ ፅንሰ-ሃሳብ እንመርምር ይለናል ጸሀፊው በመቀጠልም፡፡

{ሀ} ‹‹ጥሬ ገንዘብ የተፈጠረው የምርት ኢኮኖሚውን ለማገበያየትና ለመለካት እስከሆነ ድረስ የምርት ዋጋ አመልካች ከመሆን አልፎ የራሱ ዋጋ የለውም፡፡ የጥሬ ገንዘብ ዋጋ የሚተመነው ሊገዛ በሚችለው ምርት መጠን ነው፡፡ ስለዚህ ምርቱ ሳይኖር ጥሬ ገንዘቡን ማብዛት የምርቱን ዋጋ መጣል ነው፡፡ ለዚህ ነው በብሔራዊ ኢኮኖሚ ደረጃ የውጭ ሸቀጥ ለመግዛት ከሚያስችለው የውጭ ምንዛሪ በቀር የአገር ውስጥ ጥሬ ገንዘብ ለአገር ሀብትን ይለካል እንጂ ሀብት አይደለም የሚባለው፡፡››

{ለ} ‹‹የአገር ውስጥ ምንዛሪ (currency) ከሌላ አገር ምንዛሪ ጋር በመገበያያ ዋጋ የሚለካው በእርግጠኛ መመነዛዘሪያ መጣኝ፣ የአንድ አገር ምንዛሪ ሸቀጦችን በመግዛት አቅሙ ከሌላ ተገበያይ አገር ምንዛሪ ሸቀጦችን በመግዛት አቅም ጋር ሲወዳደር፣ወይም ከጊዜ ወደ ጊዜ በተመናዛሪዎቹ አገሮች ውስጥ ያለውን የዋጋ ንረት ልዩነት ከግምት ባስገባ የመመነዛዘሪያ መጣኝ ነው፡፡›› በ2003 ዓ/ም አንድ የአሜሪካ ዶላር 14.06 ብር ነበር፣ 2004ዓ/ም (18.65ብር)፣ 2005ዓ/ም (18.65 ብር)፣ 2006ዓ/ም (19.65ብር)፣ 2007ዓ/ም (19.85 ብር)፣2008ዓ/ም (21.83ብር)፣በ2009ዓ/ም (23.23 ብር) በ2010ዓ/ም (26.96 ብር) የብር የመመንዘሪያ መጣኝ (የጥቁር ገበያ ምንዛሪ 33.50 ደርሶል)ከዓመት ዓመት እየረከሰ በመሄዱ ከውጭ ሸቀጣ ሸቆችና ኮፒታል ጉድስ ማለትም (ማሽነሪዎች፣ መኪኖች፣ ትራንስፎርመር፣ ወዘተ) የመግዛት አቅማችን የመነመነ ለመሆን ችሎል፡፡ የሃገራችን የውጪ ንግድ ገቢ እያሽቆለቆለ በመሆዱ የታሰበው እድገት ውሃ በልቶታል፡፡

{ሐ} የብር ምንዛሪ ማርከስ( Devaluation of currency) የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ምርቱ ሳይኖር ጥሬ ገንዘቡን በማብዛት በሃገር ውስጥ ገበያ ገንዘብ በማሰራጨቱ የምርቱን ዋጋ መጨመር አስከተለ፡፡  የሃገሪቱም የብር የመግዛት አቅም በመውደቁ ምክንያት የሃገር ውስጥ ምርቶችን የመግዛት አቅሙ ተዳከመ፡፡ ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ ብሔራዊ ባንክ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦቱን  ከልኩ በላይ በሃገሪቱ ገበያ ውስጥ በማሰራጨቱ ነው፡፡ የሸቀጣ ሸቀጥ ዋጋ ግሽበት 15.6 በመቶ ከፍ በማለቱ ህብረተሰቡ በትልቅ ችግር ውስጥ ይገኛል፡፡

ያለፉት ዓመታት የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት ዕድገት

{1} 2002ዓ/ም በጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 104.0 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት  — ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ –%

{2} 2003ዓ/ም በጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 145.4 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 41 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 39.0%

{3} 2004ዓ/ም በጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 189.5 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 44 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 30.0%

{4} 2005ዓ/ምየበጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 235.3 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 46 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 24.0%

{5} 2006ዓ/ምየበጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 297.7 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 63 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 27.0%

{6} 2007ዓ/ምየበጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 371.2 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 73 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 25.0%

2002ዓ/ም እስከ 2007ዓ/ምየበጀት አመት፤የአምስት ኣመት እድገት አማካይ እድገት በመቶኛ 29.0% ‹የጥሬ ገንዘብ አቅርቦቱን   እድገት መጣኝ ቢመጣም በአካፋዩ መነሻ መተለቅ ምክንያት እንጂ፣የአቅርቦቱ መጠን እየጨመረ እንደመጣ እናያለን፡፡ የእርግጠኛ ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ዕድገትን በየአመቱ 11 በመቶ ይሁን ብለን ተቀብለን እንካ፣ ከአምስቱ አመት አማካይ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት እድገት 29 በመቶ ውስጥ 11 በመቶው ለምርት ዕድገት ዋለ ብንል ቀሪው 18 በመቶ የዋለው ለዋጋ ንረት ነው፡፡››

በ2008 ዓ/ም የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በኢትዩጵያ የሚገኙ የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ670 ቢሊዩን ብር ሲሆን በአንጻሩ ለደንበኞች የሠጡት ብድር መጠን 480 ቢሊዩን ብር ነው፡፡ በሌላ በኩል የመንግሥትና የግል ባንኮች አጠቃላይ ተቀማጭ ካፒታል ደግሞ ወደ 30 ቢሊዩን ብር አካባቢ ነው ያላቸው፡፡ ከህዝብ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብን ከባንኮች ተቀማጭ ካፒታል ስናቀናንሰው (670 ሲቀነስ 30 ቢሊዩን ብር) 640 ቢሊዩን ብር ከህዝብ የተሠበሰበ ተቀማጭ ገንዘብ የህዝብ ኃብት ነው፡፡ የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ670 ቢሊዩን ብር ነበር፡፡ የመንግስትና የግል ባንኮች፣ ለደንበኞች የሠጡት ብድር መጠን 480 ቢሊዩን ብር ነበር፡፡ የግል ባንኮች፣ ባለ አክሲኖች ተቀማጭ ካፒታል ደግሞ ወደ 30 ቢሊዩን ብር ነበር፡፡ በአጠቃላይ የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ670 ሲቀነስ ተቀማጭ ካፒታል ደግሞ ወደ 30 ቢሊዩን ብር 640 ቢሊዩን ብር ከህዝብ የተሠበሰበ ተቀማጭ ገንዘብ የህዝብ ኃብት ነበር፡፡ በተመሳሳይ በ2003 ዓ/ም 680 የቅርንጫፎች ባንኮች ቁጥር የነበረ ሲሆን፣ በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ላይ 2800 ደርሶል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ወደ 3900 ደርሶል፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማትም 1600 ቅርንጫፎች መድረስ ችለዋል፡፡ ከባንክ ቅርንጫፎች ከ3900 ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የግል ባንኮች ናቸው፡፡ 18 ሽህ የነበረው የባንክ ሠራተኛ አሁን ከ20 ሽህ በላይ ሆኖል፡፡

በአጠቃላይ ሃገሪቱ ያላት ሃብት ከግዜ ወደ ግዜ እየመነመነ፣ወደ ባህር ማዶ  የውጭ ምንዛሪያችን እየኮበለለ፣የገንዘባችን የመግዛት አቅም በዲቨሊዌሽን እየቀነሰ መምጣትን ያሳያል፡፡ በአዲስአበባ ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት  355 ሽህ ብር የሊዝ መጫረቻ ዋጋ መቅረቡ አመላካች የኢኮኖሚ ውድቀት መሆኑንና የብራችን እሴት  ወደ ወረቀትነት  መቀየርን እንደሚያሳይ  የምጣኔ ኃብት ጠበብት ይገልፃሉ፡፡ በተጨማሪም የሉዓላዊ ቦንድ የቃል ኪዳን ሰነድ አንድ ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ብድር በአጠቃላይ ሦስቱም የኢኮኖሚ ዘርፎች ምሦሶ መወላለቃቸውን ያሳያል፡፡

በ2009 ዓ/ም የመንግስት ባንኮች፣ የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣ የሚከታተላቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትጵያ ልማት ባንክና የኢትዩጵያ መድን ድርጅት የ2009 ዓ/ም የዕቅድና አፈፃፀም

ጠቅላላ ሀብት፤በሶስቱ የመንግሥት የፋይናንስ ተቆማት የ2009 ሂሳብ ዓመት ክንውን መሠረት የ523 ቢሊዩን ብር ጠቅላላ ሀብት መመዝገቡን ሲገለፅ፣ ከታቀደው የ517 ቢሊዩን ብር አኮያ ከ100 በመቶ በላይ ጭማሪ መመዝገቡን ኤጀንሲው አስታውቆል፡፡ በ2008 ዓ/ም ከነበረው የ440.4 ቢሊዩን ብር ጠቅላላ ሀብት አኮያ የ82.6 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቦል፡፡ ከጠቅላላው ሀብት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ የተመዘገበው 60 ቢሊዩን ብር ገደማ መድረሱም ታውቆል፡፡ በብድር መልክ የተመዘገበው ሃብት 184 ቢሊዩን ብር ሲሆን፣ በኢንቨስትመንት መልክ ከ269 ቢሊዩን ብር በላይ ነው፡፡

አጠቃላይ የዕዳ መጠን፤ በሦስቱ ተቆማት በ2009ዓ/ም ያስመዘገበት አጠቃላይ የዕዳ መጠን 490 ቢሊዩን ብር ሲሆን፣ በ2008ዓ/ም የነበራቸው የእዳ መጠን 415 ቢሊዩን ብር ነበር፡፡ በዚህም መሠረት የፋይናንስ ተቆማቱ ካፒታል መጠባበቂያ ክምችታቸውን ጨምሮ 33 ቢሊዩን ብር ተመዝግቦል፡

በብድር ሥርጭት፤በሦስቱ ተቆማት  በብድር ሥርጭት ረገድ ድርጅቶቹ 124 ቢሊዩን ብር ብድር (የብድር ቦንድ ኩፖን ታክሎበት) ማሠራጨታቸው ሲገለፅ፣አብዛኛው ድርሻ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ መሆኑ ተመልክቶል፡፡ባንኩ 94.5 ቢሊዩን ብር ብድር መሰጠቱ፣54 ቢሊዩን ብር ገደማ ብድር መሰብሰቡንና የብድር ክምችቱም በቦንድ የሰጠውን ጨምሮ 420 ቢሊዩን ብር ገደማ መድረሱ ታውቆል፡፡

የተበላሸ የብድር፤ በሦስቱ ተቆማት የተበላሸ የብድር መጠኑ ከጠቅላላው ብድር ውስጥ 2.8 በመቶ መሆኑ ሲገለፅ፣የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ካስቀመጠው የአምስት በመቶ የተበላሹ ብድሮች ጣሪያ አኮያ ዝቅተኛ ሆኖል፡፡ ከዚህም በላይ 14.6 ቢሊዩን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን፣ ከ2008ዓ/ም መጠንም የ5.2 በመቶ ብልጫ እንዳለው ታውቆል፡፡

የኢትዩጵያ መንግሥታዊ ባንኮች የፋይናንስ ዘርፍ ቀውስ›› የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ኃላፊነቱን ያልተወጣ ተቆም ነው፡፡ በሃገሪቱ ለተፈጠረው የፋይናንስ ዘርፍ ቀውስ፣ የገንዘብ አቅርቦት መመጠንና መቆጣጠር አለመቻሉ፣ የገንዘብ ወጪና ብድርን መወሰንና መጠበቅ አለመቻሉ፣ የሃገሪቱን የዓለም ዓቀፍ ተቀማጭና መጠባበቂያ ገንዘብ መቆጣጠርና ማስተዳደር ደካማነቱ፣ ለባንኮች ፍቃድ መስጠት፣መቆጣጠርና ክትትል ማድረግ አቅመቢስነቱ፣ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ መያዝ፣እንዲሁም ለንግድ ባንኮች ገንዘብ ማበደር፣ የንግድ ባንኮችን ብድር መቆጣጠርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም የወለድ መጠንን መወሰን ጣልቃ ገብነቱ፣ እንደ መንግሥት ወኪል ሆኖ በመስራትና የውጭ ምንዛሪ ምጣኔን መወሰንና መቆጣጠር ተስኖቸዋል፡፡ የባንክ ሙያተኞች በሙስና ተዘፍቀው ከሹማምንቶቹ ጋር ተመሳጥረው የሃገር ሃብት መዝብረዋል፡፡ በሱዳን የግል ካንፓኒ፣የብር ኖቶችንና ሣንቲሞችን በማሳተም የሃገሪቱን የብር ኖቶችን እንደወረቀት በማሳተም የሃገር ሉዓላዊነትንና የህዝቡን ደህንነት ለባዕድ አገር አሳልፈው የሰጡ የብሄራዊ ባንክ ገዥዎችና የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም፡፡

የካቲት 28 ቀን 2010ዓ/ም ‹‹ብሔራዊ ባንክ ካቀደው በላይ የገንዘብ አቅርቦት ፍላጎት እያስተናገደ እንደሚገኝ ገለጸ›› የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ  ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚ ባለሙያ  ዶክተር  ዮሐንስ አያሌው፤ እንደገለፁት፣ በአገሪቱ ለሚካሄደው ልዩ ልዮ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መንግሥት በዕቅድ የያዘው የገንዘብ አቅርቦት መጠን ከኢኮኖሚው አኮያ የ28 በመቶ ድርሻ ነበር፡፡›› ‹‹ይሁንና የኢንቨስትመንት ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ ሳቢያ ከታቀደው የገንዘብ አቅርቦት በላይ ከፍተኛ የገንዘብ ፍላጎት ተፈጥሮል…በመሆኑም ከኢኮኖሚው የ40 በመቶ በላይ ድርሻ ያለው የገንዘብ አቅርቦት እንዲሆን ለማድረግ ባንኩ መገደዱን አስታውቀዋል፡፡›› በዚህም ምክንያት ብሔራዊ ባንክ ብዙ ቢሊዩን ብር ሱዳን ውስጥ በሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ አሳትሞ፣ በገበያው ውስጥ ወረቀቱን ሞቅ አድርጎ ገበያው ውስጥ መዝራቱን አምኖል!!!

የአገሪቱ ኢኮኖሚ በገንዘብ ሲተመን ከ750 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ20 ትሪሊዮን ብር በላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡›› መረጃው በጥናት የተደገፈ ከሆነ በጋዜጦች፣ በባንኩ ድረ-ገፆች ቢወጣ መልካም ነው፡፡ የ2009 ዓ/ም የሃገሪቱ በጀት 14  ቢሊዮን ዶላር በሆነበት አገር የአንድ ዮኒቨርሲቲ ወይም የኮስ ክለብ ባጀት መሆኑን አይዘንጉ፡፡ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በገንዘብ ሲተመን ከ750 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ20 ትሪሊዮን ብር ይሆናል ማለት የፖለቲካ ካድሬ ንግግር ያደርገዋል፡፡  የውጭ ሸቀጥ ለመግዛት ከሚያስችለው የውጭ ምንዛሪ (ዶላር፣ፓውንድ፣ ዮሮ) ሲሆኑ የኢትዮጵያ ብር  20 ትሪሊዮን ብር የአገር ሀብትን ይለካል እንጂ ሀብት አይደለም!!! ብር የውጭ ሸቀጥ የማይገዛ ወረቀት ነው!!! ዶክተር ዮሐንስ አያሌው ለህሊናዎ ይኑሩ!!! በእናንተ ዘመን የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉና፤ የኢብባ ምክትል ገዥ አቶ ዮሐንስ አያሌው፤ ባንኩ እንዴት እንደረከሰ፣ ሙያችሁን በውሽት እንደኮማሪት የሸጣችሁ፣ ለኢፈርት/ ሜቴክ ወዘተ ብድር የሰረዛችሁ፣ ጠሞርጌጅ ባንክን ያፈረሳችሁ፣ ወርቅ በባሌስትራ የተረከባችሁ፣ ልዑል ፀሓዬ የአባይ ፀሃዬ ወንድም የውጭ ምንዛሪ ሃላፊ አርጋችሁ ሀገር ያዘረፋችሁ፣ የአላሙዲንና  የወያኔ ድቤ መችዎች መሆናችሁን ህዝብ ያውቃል!!! የሀገር ኢኮኖሚ ገድላችሆል፣ አገሪቱን ዕዳ ከታችሆል፣ በሙስና ተዘፍቃችሆል፣ የፋይናንሱን ዘርፍ አዋርዳችሆል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ንዋሪዎችን በልማት ስም እያፈናቀሉ መሬቱን መሸጥና ገቢ ማግኘት ዋናው የወያኔ የገቢ ምንጭ የሆነው፡፡ ልጅ እግር ባለጸጋዎቹ ምን ሰርተው አገኙ በእርሻ ተሰማርተው፣ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ወይስ በአገልግሎት ዘርፍ ተሰማርተው ኃብት እንዳፈሩ አይታወቅም፡፡ የባንክ ብድር የገንዘብ ምንጫቸው የሆነው ወያኔ ብድር በማቻቸላቸው ገንዘብ፣ የባንክ ብድር፣ መሬት እየገዙ ሁለት ሶስተኛ የአዲስ አበባ መሬት የወያኔ ካድሬዎች ተቆጣጥረዋል፡፡ ለጀነራል ፃድቃን የቢራ ፋብሪካ በድር ታመቻቻላችሁ ሌላ ምን ሥራ አላችሁ‹ ጊዜ ለኩሉ!!!  እንደ አቶ ሱፍያን አህመድ ያለ ሌባ እንደኮበሉ ይገንዘቡ የእናንተና የወያኔ ጉድ ተቆፍሮ ይወጣል!!! ሃገር በመሸጣችሁ፣ ሙያችሁን በማርከሳችሁ፣ ነገ ለፍርድ ትቀርባላችሁ!!!

የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ኃላፊነቱን አልተወጣም ‹‹ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) አኮያ ለኢንቨስትመንት የዋለው ገንዘብ መጠን የኢኮኖሚውን 40 በመቶ ሆኖል፡፡ ለኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን የገንዘብ መጠን ሙሉ ለሙሉ ከቁጠባ መሞላት ባለመቻሉ መንግሥት ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ምንጮች ለመበደር መገደዱ ግልጽ ነው፡፡ በአገሪቱ የማይክሮ ኢኮኖሚ መዋቅር ውስጥ ሁለት መሠረታዊ ችግሮች እንዳሉ ገልፀዋል፡፡›› አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የሃገሪቱ ጂዲፒ 80 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ በቴሌቨዥን ይናገራል፣ መረጃ በኪሴ እባክዎ መረጃውን ከየት እንዳገኙ ይግለጹ፡፡ ከአንድ ምሁር ነኝ የሚል ሰው አይጠበቅም፣ 100 ቢሊዩን ዶላር ይደርሳል ይላሉ!ህዝባዊው አመፁስ!  በኢትዮጵያ የአንድ ሰው የነፍስ ወከፍ ገቢ ድርሻ በ2000 ዓ/ም(237 ዶላር )፣ 2005ዓ/ም (458 ዶላር ) እና 2009ዓ/ም (689 ዶላር) መድረሱን መረጃው ያሳያል፡፡ የወያኔ የፖለቲካ ካድሬዎችና አድርባይ ምሁራን የመረጃ ቁጥር ከፍ በማድረግ ይቀጥፋሉ፣ይዋሻሉ ትውልዱ ከነሱ ምን ይማር!!!   በኢትዮጵያ አማካይ አመታዊ የሸቀጣ ሸቀጦች ምርቶች የዋጋ ግሽበት  በ2001 ዓ/ም  (25.5 በመቶ )፣ 2005ዓ/ም (23.0በመቶ )እና 2009ዓ/ም (9.7 በመቶ) መድረሱን መረጃው ያሳያል፡፡ በ2010 ዓ/ም ሁለት አሃዝ ከ10እስከ 15.6 በመቶ የዋጋ ንረት መከሰቱን ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ አማካይ የውጭ ምንዛሪ ምጣኔ በ2001 ዓ/ም  (1 ዶላር በ 9.6 ብር )፣ 2005ዓ/ም (1 ዶላር በ 17.7 ብር ) እና 2009ዓ/ም (1 ዶላር በ 21.8 ብር ) መድረሱን መረጃው ያሳያል፡፡ በ2010 ብሄራዊ የውጭ ምንዛሪ ምጣኔ 15 በመቶ በመጨመር  (1 ዶላር በ 26.96 ብር ) ሲሆን  በጥቁር ገበያ (1 ዶላር በ 33.50 ብር ) በመመንዘር ላይ ይገኛል፡፡ እንደ ሞ- ዘመዴነህ ንጋቱ  ጊዜ የሰጠው ቅል!  በቅጥፈትዎ ትውልዱን ልጆችዎን አያሳስቱ!

ቁጠባና በኢንቨስትመንት፤‹‹አንደኛው በቁጠባና በኢንቨስትመንት መካከል ያለው ከፍተኛ ክፍተት ሲሆን፤ ማለትም በቁጠባና ኢንቨስትመንት መካከል  ያለውን ክፍተት ለማጥበበብ የቁጠባ ዘዴዎችን በመጠበቅ ለኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማሞላት የመንግሥት እቅድ ቢሆንም፣ ኢኮኖሚው ከሚፈልገው  የገንዘብ አቅርቦት አኮያ በባንኮች በኩል የሚሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ የሚጠበቀውን ያህል ሊሆን አልቻለም፡፡ በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከጠቅላላ ኢኮኖሚው ውስጥ እስከ 25 በመቶ የሚደርሰውን መጠን በቁጠባ መልክ  ማሰባሰብ ከተቻለ ትልቅ ዕርምጃ  እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በ2009 ዓ/ም ይፋ ከተደረገው  የብሔራዊ ባንክ መረጃ ለመረዳት እንደሚቻለው በአገሪቱ የተሰበሰበው የተቀማች ገንዘብ መጠን 500 ቢሊዮን ብር ገደማ ሲሆን ፣ የኢንቨስትመንት መጠን 590 ቢሊዮን ብር ገደማ ነው፡፡በመሆኑም አገራዊ የቁጠባ መጠን ከኢኮኖሚው  ውስጥ የ32 በመቶ ድርሻ ሲኖረው ኢንቨስትመንት ወይም ካፒታሉ ወደ 40 በመቶ ገደማ ይይዛል፡፡ በዚህም የተነሳም በቁጠባና በኢንቨስትመንት መካከል እስከ 7 በመቶ የሚጠጋ ክፍተት ይታያል፤ ወይም የቁጠባው መጠን ከኢንቨስትመንቱ 7 በመቶ ያነሰ ሆኖ ይታያል፡፡ አገራዊ የቁጠባ መጠን  ከፍ ለማድረግ፡ ባንኮች የቅርንጫፍ ብዛታቸውን መጨመር 4000 መድረሳቸውን ተገልፆል፤የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ ፈንድ መቆቆሙም ለቁጠባ መስፋፋት አንደኛው ተጠቃስ እርምጃ  ነው፡፡ እንዲሁም  ትልቁን ድርሻ የያዘው የ27 በመቶ የቦንድ ግዥ መመሪያዋነኛ ው የቁጠባ ምንጭ ነው፡፡በየወሩ ባንኮች ለብሄራዊ ባንክ ገቢ የሚያደርጉት የገንዘብ መጠን እስካለፈው ሁለት አመት 69 ቢሊዮን ብር እንዳስመዘገቡና ይህም ከመካከለኛ እስከ ረዥም ጊዜ የሚወሰዱ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ለማድረግ እንዳገዘ፣ በአሁኑ ወቅትም ለእነዚህ ጵሮጀክቶች የሚውለው ገንዘብ ከ11 በመቶ ወደ 21 በመቶ እንዳደገ ገልጸዋል፡፡››

ሀብትና ዕዳ፤ ሁለተኛው ደግሞ በአገሪቱ ሀብትና ዕዳ መካከል የሚታየው ክፍተት ነው፡፡ አገሪቱ ያላት የፋይናንስ ሀብትና እዳ ላይ የሚታየው ክፍተት ግን ሌላኛው ወሳኝ ፈተና እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ ከፋይናንስ ሀብት አኮ በተለይ የቁጠባ መጠን በአብዛኛው የሚሰበሰበው በባንኮች ቢሆንም፣መንግሥት ለሚፈልጋቸውና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መሰኮች የሚውል የገንዘብ መጠን ባለመሆኑ ሌሎች የቁጠባ መጠንኑን ሊያሳድጉ የሚችሉ ዕርምጃዎችን ለመውስድ ባንኩ ተገዶል፡፡››

የወያኔ መንግሥት በግማሽ ዓመቱ 89.35 ቢሊዮን ብር በብድር ዕርዳታ ‹‹አገሪቶ የምታገኘው የእርዳታና ብድር መጠን ጨምሮል›› የካቲት 17 ቀን 2010ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ፤ አገሪቶ በ2010 ዓ/ም በስድስት ወር ውስጥ  ያገኘችው ዕርዳታና ብድር ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃ በከፍተኛ መጠን መጨመሩን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አስታወቀ፡፡ የሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነትና ኢንፎርሜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ሃጂ ኢብሳ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ፤ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቆማት ፣ ከአውሮፓ ህብረትና ከተባበሩት መንግሥታት እንዲሁም ቻይናን ጨምሮ ከተለያዩ የልማት አጋር መንግሥታት ውጪ ከበይነ መንግሥታዊ ተቆማት በዚህ አመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት 55.548 ቢሊዮን ብር አዲስ ብድርና እርዳታ ተገኝቶል፡፡ ከተለያዩ የልማት አጋር መንግሥታትም 33.798 ቢሊዮን ብር እርዳታና ብድር የተገኘ ሲሆን በአጠቃላይም 89.346 ቢሊዮን ብር ብድር ማግኘት ተችሎል፡፡  …ከዚህ ውስጥ  ወደ አገሪቱ ካዝና በትክክል የፈሰሰው ገንዘብ መጠን 20.967 ቢሊዮን ብር መሆኑን ተናግረዋል፡፡  ከአጋር የልማት መንግሥታት  ደግሞ 29.476 ቢሊዮን ብር የሃብት ፍስት እንደነበረም አመልክተዋል፡፡በጠቅላላው 50.443 ቢሊዮን ብር እርዳታና ብድር ተገኝቶል፡፡››

መንግሥት በግማሽ ዓመቱ 89.35 ቢሊዮን ብር በብድር ዕርዳታ ማግኘቱን አስታወቀ 25 February 2018 ውድነህ ዘነበ

መንግሥት በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመርያው ስድስት ወራት ከዕርዳታና ከብድር 89.346 ቢሊዮን ብር ማግኘቱን፣ ከዚህ ውስጥ 50.443 ቢሊዮን ብር እንደተለቀቀለት አስታወቀ፡፡ በመጀመርያው ስድስት ወራት ከዓለም አቀፍ የልማት ተቋማት (መልቲ ላተራል) በብድር 20.971 ቢሊዮን ብር፣ ከዕርዳታ 34.58 ቢሊዮን ብር በድምሩ 55.55 ቢሊዮን ብር አዲስ ዕርዳታና ብድር መገኘቱን፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሃጂ ኢብሳ ዓርብ የካቲት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ ከመንግሥታት ትብብር (ባይላተራል) ምንጮች 16.970 ቢሊዮን ብር በብድር፣ 16.828 ቢሊዮን ብር በዕርዳታ፣ በድምሩ 33.798 ቢሊዮን ብር አዲስ ብድርና ዕርዳታ ተገኝቷል ብለዋል፡፡ ከሁለቱም የፋይናንስ ምንጮች ባለፉት ስድስት ወራት 89.346 ቢሊዮን ብር መገኘቱን፣ ከዚህ ግኝት ውስጥ ብድር 37.941 ቢሊዮን ብር፣ ዕርዳታ 51.405 ቢሊዮን ብር ድርሻ መያዛቸው ተገልጿል፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ፈሰስ ወይም የተለቀቀው 50.443 ቢሊዮን ብር መሆኑን አቶ ሃጂ ገልጸዋል፡፡ ከመልቲላተራል ምንጮች ብድርና ዕርዳታ 20.967 ቢሊዮን ብር፣ ከባይላተራል ምንጮች ደግሞ በብድርና ዕርዳታ 29.476 ቢሊዮን ብር መለቀቁን አቶ ሃጂ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ‹‹በግማሽ ዓመቱ የተለቀቀው ገንዘብ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ21.873 ቢሊዮን ብር (43.36 በመቶ) ብልጫ አለው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡ በግኝትም ሆነ በፍሰት የሚመጣው ገንዘብ በአሜሪካ ዶላር የተሰላ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ መጀመርያዎቹ ሦስት ወራት የተገኘውና የተለቀቀው ገንዘብ በወቅቱ በነበረው አንድ ዶላር 23.2520 ብር ተመን መሆኑን፣ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት የተሰላው ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ብር ከዶላር ጋር ያለው ምጣኔ በ15 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጎ በወጣው 26.6995 ብር ሒሳብ መሆኑ ተገልጿል፡፡ መንግሥት በቅርቡ ካፀደቀው 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ጋር በድምሩ ለ2010 ዓ.ም. 334.8 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት ማፅደቁ ይታወሳል፡፡ በተለይ ከውጭ ዕርዳታ 17,137,870,826 ብር፣ ከውጭ ብድር ደግሞ 28,618,622,718 ብር እንደሚገኝ ታሳቢ ተደርጎ የበጀት አዋጅ መዘጋጀቱ አይዘነጋም፡፡ ከውጭ በብድርም ሆነ በዕርዳታ ይገኛል ተብሎ ታቅዶ የነበረው 45.8 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ ሃገሪቱ ከ45 አስከ 50 ቢሊዮን ዶላር ብድር አለባት በዕዳው ጫና የተነሳ ቴሌኮም፣ የባቡር ኮርፖሬሽን፣ ንግድ መርከብ፣ ወዘተ ለቻይና መንግሥት ፕራይቬታይዝ መደረጉ አይቀርም፡፡ በግሪክ የባህር ወደባቸው ለቻይና ተሸጦል፣ 14 አውሮፕላን ማረፍያዎች ለጀርመኖች የግል ድርጅት መሸጣቸው ታውቆል፡፡ በ2010ዓ/ም የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለግብይት ከሚያቀርባቸው ቡና ፣ሰሊጥና ቦለቄ ምርቶች 40 ሽህ ቶን ቀንሶል፡፡ ዋናው ምክንትም በሃገሪቱ የተከሰተው ህዝባዊ አንቢተኝነትና ተጋድሎ መሆኑ ታውቆል፡፡በየካቲት ወር ግብይት  ካለፈው ጥር ጋር ሲነፃፀር 28 በመቶ ቀናሽ አሳይቶል እንዲሁም የየካቲት ወር ግብይት በታህሣስ ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ከ105 ሽህ ቶን ወደ 66 ሽህ ቶን ወይም 38 በመቶ ቀንሶል፣ ይህም በገንዘብ ሲሰላ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ቅናሽ ታይቶበታል፡፡ በአጠቃላይ ሃገሪቱ በውጭ ንግድ ገቢዋ በጣም እንደሚቀንስና የውጪ ምንዛሪ አግኝታ እዳዋን ለመክፈልና የእዳ ጫናዋን ለመቀነስ እድሎ የመነመነ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ያገራቸውን ኢኮኖሚ ጠንቅቀው አያውቁም፣ የጋዜጠኞች የምጣኔ ኃብት እውቀትም ገፅ አያሻግርም!!! ጋዜጠኞቹም የምጣኔ ኃብት እውቀታቸውን ሰታትስቲክስ መረጃ እየጠቀሱ ጥናታዊ ፁሁፍ እያነበቡ በመዘጋጀትና እውቀታቸውን በማበልፀግ ፖለቲከኞቹን፣ የባንክ ባለሙያዎችን፣ የሃገር የአምስት ዓመት እቅድና አፈፃፀም እንዲሁም ዓመታዊ በጀት ወዘተ መጠየቅ፣ ማሳወቅና ማጋለጥ የመጭው የዲጂታል ቴክኖሌጅ ወጣት ትውልድ አንገብጋቢ ሥራ ነው፡፡ ወደፊት የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት የፖለቲካና የኢኮኖሚክስ 101 (ዋን ኦ ዋን) ሳያልፉ ፖለቲካ መፈትፈት በትንታግ ጋዜጠኖች ጥያቄ ፈተናው ከባድ ይሆናል፡፡ ያሁን ዘመን የቴሌቨዝን፣የሬድዬ፣ የኤፍ ኤም የባህር ማዶና የሃገር ውስጥ ጋዜጠኞች ዘጠና ከመቶ ዕውቀት የተገነባው ስለ ሰነጥበብ፣ ሥነጹሁፍ፣ ትያትር፣ ፋሽን ሸው፣ ታሪክ፣ ህግ፣ ዘፋኝ፣ተዋናይ ቃለ-መጠይቅ ወዘተርፈ የዘለለ ባለመሆኑና የምጣኔ ኃብት እውቀታቸው አናሳ በመሆን የተነሳ ፖለቲከኛችን፣ የፋይናንስ የባንክ ዘርፍ ገዢዎችን፣ የኢኮኖሚ ፖሊስ አውጪዎችን፣እቅድ አውጪዎችን  የወያኔን ሹማምንቶችን በእውቀት ሲፈታተኑ አልታየም!!! ኢትዮጵያዊ የድረ-ገፆች ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ ህብረተሰቡን እንዲገነዘብ ላደረጋችሁት አስተዋፆኦ ምስጋና ይገባችሆል፡፡ ኢኮኖሚ የፖለቲካ ነፀብራቅ ነውና!!! ኢኮኖሚውን ሳያውቁ ፖለቲካውን አይነቀንቁ!!! የሚባለው ለዚህ ነው! የወያኔ ካድሬዎች ሃገር ያደህዮት የፖለቲካና የኢኮኖሚክስ እውቀት ስለሌላቸው  ነው! ድክመታችንን የጠቆመን ያጀግነናልና!!!

ያለ ኢኮኖሚ ነጻነት፣ የፖለቲካ ነፃነት የለም!!! የወርቅ ማዕድናችንና መሬታችንን እናስመልስ!! በፕራይቬታይዜሽን በሙስና የተሸጡ እርሻ፣ ፋብሪካዎች፣ ሆቴሎች፣ ለጸረ-ሙስና ለፍርድ ይቅረቡ!!! ብር ወረቀት፣…. ወረቀት ብር፣….. የብር ወረቀት፣ ……የወረቀት ብር!!!……

በህዝብ ትግል ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ይነሣል!!! የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይከበራል!

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የአምነስቲ " ሽንቁረ ብዙ" ሪፖርት የተከፋዮች የቲውተር ዜና ድምር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *