“ማረሚያ ቤት ብዙ ነገር አስተምሮኛል። ብዙ እንዳነብ እና ከታላላቆቼ እና ከተማሩ ሰዎች ብዙ እንዳውቅ አግዞኛል” በሚል ስለ እስር ቤት ህይወታቸው ተናግረው የነበርይት አቶ ታዬ ደንደና ለሶስተኛ ጊዜ በድንገት ታሰሩ። ቤተሰብ የት እንዳሉ አይውቅም። አቶ ታዬ ሊታሰሩ እንደሚገባ በማህበራዊ ገጾች ላይ ዛቻ ነበር። ዛቻውም የሞያሌውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ” ድርጊቱን በስህተት የተፈጸመ ነው ማለት ህዝብን መስደብ ነው” በማልታቸው እንደሆነ ተገምቷል።

በጥቅምት ወር 2017 ለቢቢሲ የእስር ቤት ህይወታቸውን አስመልክቶ ቃላቸውን የሰጡት አቶ ደንደና በቁጥጥር ስር የዋሉት ጠዋት ወደ ስራ እያመሩ ባሉበት ሰዓት በታጠቁ ሃይሎች ነው። በቁጥጥር ስር ከዋሉም በሁዋላ ወደየት እንደተወሰዱ የታወቀ ነገር የለም።

Related stories   PM Abiy, U.S Senator Inhofe Hold Encouraging Conversation about Tigray

ባለቤታቸው ወይዘሮ ስንታየሁ አለማየሁ ባለቤታቸው መታሰራቸውን ብቻ እንደሚያውቁ፣ ነገር ግን ወዴት እንደተወሰዱና የት እንዳሉ እንደማያውቁ ቢቢሲ አመልክቷል።

ለመታሰራቸው የቀረበ ምክንያት ባይኖርም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈጸሚያ መመሪያ መሰረት ከኮማንድ ፖስቱ ውጭ በፀጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት ቢከለከልም፣ አቶ ታዬ ‘የሞያሌው ግድያ በስህተት የሆነ አይደለም’ ማለታቸውን ተከትሎ ሳይታሰሩ እንደማይቀር ቢቢሲ ግምቱን ሰጥቷል።

አቶ ታዬ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበሩበት ወቅት ለበርካታ ጊዜያት ለእስር መዳረጋቸ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ለመመረቅ 16 ዓመታት እንደፈጀባቸው ይታወሳል። አቶ ታዬ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩ በሁዋላ ሶስት ዓመት ቆይተው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ በነጻ ተለቀዋል። ከሶስት ዓመት በሁዋላ ፍርድ ቤት ነጻ ያላቸው አቶ ታዬ ያለ በቂ ምስረጃ የሚታሰሩ ሰዎች ካሳ ያስፈልጋቸዋል የሚል እምነት እንደሚያራምዱ በአንደበታቸው ተናግረዋል። 

“ማረሚያ ቤት ብዙ ነገር አስተምሮኛል። ብዙ እንዳነብ እና ከታላላቆቼ እና ከተማሩ ሰዎች ብዙ እንዳውቅ አግዞኛል” ሲሉ ስሜታቸውን የገለጹት አቶ ታዬ

Related stories   ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!

“ማረሚያ ቤት ማለት በቀን ለ24 ሰዓታት የፈለከውን ነገር ማድረግ የምትችልበት ቦታ ማለት ነው። መናደዴን ትቼ ሦስት ነገሮችን ለማሳካት ወስኜ ተነሳሁ፤አንድ ከመፃህፍት እንዲሁም በእውቀት እና በዕድሜ ከሚበልጡዋቸው መማር፤ ሁለት መፃህፍትን ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ መተርጎም እንዲሁም ሦስተኛው የማረሚያ ቤት ጓደኞቹን የኦሮምኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማር” ሲሉ እስር ቤት የኖሩበትን ዘመን እንደተጠቀሙበት ተናግረውም ነበር።

Related stories   የኢዜማ 23 የፓርላማ እጩዎች እነማን ናቸው?

አቶ ታዬ ቀደም ሲል በጨለንቆ፣ አሁን ደግሞ በሞያሌ የተካሄደውን እልቂት በጽኑ የኮነኑ፣ ወንጀለኞቹም በክልሉ መደበኛ ፍርድ ቤት ከነአዛዣቸው ሊቀርቡ ይገባል በሚል ለህግ ልዕልና የተከራከሩ ናቸው። የሳቸውን መታሰር አስመልክቶ ያሰራቸው አካልም ሆነ ክልላቸው ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ ያለው ነገር የለም።

አቶ ታዬ ከጥቂት ወራት በፊት ከቢቢሲ ጋር ያደረጉትን ቆይታ እዚህ ጋር ይመልከቱ።

አንድ ድግሪ ለማግኘት 16 ዓመታት የፈጀበት ኢትዮጵያዊ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *