* ”ከታሰሩት ውስጥ የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ ያባከኑ አሉበት “ * “ይቅርታ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሆነው ረስቸዋለሁ ”

ልኡል ወሊድ ቢን ታላል ይባላሉ ። ሰማቸው ከሃብታቸው ጋር ከሳውዲ አልፎ በመላው አለም የተናኘ የሳውዲ ንጉሳን ቤተሰቦች አባል ናቸው። ባለሃብቱ ልኡል ወሊድ ቢን ታላል የሳውዲ መንግስት አስተዳደር እንደማንኛውም የሃገሪቱ ዜጋ ባለሃብት ከመሳተፍ ውጭ በየትኛውም የመንግስት ኃላፊነት ላይ የሉበትም ።

ልኡል ወሊድ ከወራት በፊት መንግስት ለግብዣ ተጠርተው ሪያድ በሚገኘው የሪል ካርተን ሆቴል ባላሰቡት የሙስና ጉዳይ ለወራት ታግተው ስለነበረበት ሁኔታ ዘርዘር ያለ መረጃ በመስጠት የወራት ዝምታቸውን ሰብረዋል ። ልኡሉ ከእገታ ከወጡበት ጊዜ አንስቶ ለታዋቂው የብሎምበርግ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ኢሪክ አሽተር ጋር በሰጡት ከአንድ ሰአት በዘለቀ ቃለ ምልልስ ስለአያዛቸው ፤ በምርመራ ተደብደበዋል ስለመባሉ ፤ ከእገታው ለመውጣት ለመንግስት ከፍለዋል ስለተባለው ገንዘብና አደረጉት ስለተባለው ስምምነት ፤ ኪንግደም ስለተባለው ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ግንባታ መዘግየት ፤ በቀጣይ ለመስራት ስላሰቧቸው ስራዎች ፤ ከንጉሱና ከአልጋ ዎራሹ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ተጠይቀው ምላሻቸው ሰጥተዋል ።

ጋዜጠኛ ኤሪክ ልኡል ወሊድን “ዛሬ ለመናገር ለመን አስፈለገዎ ? “ ” ለምን ተያዙ ? “ ከሚለው ክችም ያለ ጥያቄውን አስቀድሞ “ የበደሉዎትን ይቅር ይሏቸዋል “ ብሏቸው ነበር ። ልኡል ወሊድም ከመታሰራቸው በፊት በአንድ የሪያድ በርሃ ላይ የምሽቱን የበርሃ ኮከብ እየቆጠረ አብሯቸው ይዝናና ለነበረው የቅርብ ወዳጃቸው የብሎምበርጉ ጋዜጠኛ ኤሪክ ዘና ብለው ይመልሱለታል ። “ መታሰሬን ተከትሎ በርካታ ታዋቂ የመገናኛ ብዙሃን የሌለ የፈጠራ መረጃ ያሰራጩ ነበር ። ቶርች እንደተደረግኩ እንደተደበደብኩ ያናፍሱ ነበር ፤ ግን የተባለው ሁሉ ሃሰት ነው “ በሚለው ዝምታቸውን ሰብረውታል ። እውነቱን በአደባባይ ለመናገር ካነሳሳቸው የስም ማጥፋት የሃሰት ያሉት መረጃ ጀምሮ ” ለምን በሪድ ካርተን ሆቴል ለረዥም ጊዜ ታሰሩ ?“ ተብለው ተጠይቀው ሲመልሱ “ለምን እንደተያዝኩ እኔም አይገባኝም … የሳውዲን መንግስት ጠይቅ ? “ ብለዋል ልኡል ወሊድ !

ሙስናና የሚያወግዙትን ዜጋ የመንግስትን ሃብት ከዘረፉት ጋር አብረው መታሰራቸው ትክክል እንዳልነበር የተናገሩት ልኡል ወሊድ ከታሰሩት ውስጥ የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ ያባከኑ እንደሚገኙበት ሳይደብቁ ተናግረዋል። ከእስር ሲዎጡ ከመንግስት ጋር ስምምነት የደረሱበትን ጉዳይ በግልጽ ማሳወቅ ያልፈለጉት ልኡል ወሊድ ያም ቢሆን በሙስና እጃቸው ተጨማልቆ ጥፋታቸውን ቀርቦና ገንዘብ ከፍለው ከእገታ አለመውጣታቸውን ግልጽ አድርገዋል ። በተፈጠረው ሁኔታ የይቅርታ ልብ እንዳላቸው ብልሁ ጋዜጠኛ ኤሪክ ጠይቋቸው ”ይቅርታ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሆነው ረስቸዋለሁ ” በማለት ቀጥተኛ ምላሽ ሰጥተዋል ። በተፈቱ በ24 ሰአት ውስጥ ከንጉሱና ከአልጋ ወራሹ ጋር በቅርብ እንደሚገናኙ ግልጽ ያደረጉት ሳውዲው ቢሊዮኔር ልኡል ወሊድ ቢን ታላል በሳውዲ የተጀመረውን የ2030 የተሃድሶ እንቅስቃሴ ደጋፊነታቸውን በዝርዝር አስረድተዋል። ወሊድ በሰጡት ማብራሪያ ከሳውዲ ሴቶች የመኪና መንዳት መብትና ውሳኔ ጀምሮ በቀረው የመንግስት እርምጃ እሳቸው ቀድሞውኑ ይጎተጉቱት የነበረው ጉዳይ በመሆኑ ለሳውዲ ንጉስና ለአልጋ ወራሹ ያላቸውን ድጋፋቸው በይፋ ተናግረዋል ።

በአሜሪካ ትላልቅ መዋዕለ ንዋይ ያፈሰሱት ልኡል ወሊድ ቢን ታላል በዚሁ ቃለ ምልልስ ከአሜሪካው ፕሬዚደንት ከዶናልድ ትራንፕ እጩ እያሉ በትዊተር ስለመወራረፋቸው ፤ ትራንፕ ስልጣን ከያዙ በኋላ እንደ ሀገር መሪ በአሜሪካ በወሰዱት የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደ ባለ ሃብት መጠቀማቸውንና መደሰታቸውን ጠቁመዋል ። ወሊድ በማከልም ፕሬዚደንት ትራንፕ ከቀድሞው ፐሬዚደንት ባራክ ኦባማ የተሻለ ራዕይ ያላቸው መሪ ናቸው የሚል እምነት እንዳላቸውና የፍልስጥኢምን ጉዳይም እልባት ይሰጡበታል ብለው እንደሚያምኑ በቃለ ምልልሱ ተናግረዋል።

የሳውዲ ጉዳይ ለማወቅ ለምትሹ ድንቅ ቃለ ምልልስ ነው ። አድምጡት !

ፍትህ ለብላቴናው መሐመድ ማለታችሁን አትርሱ !
ፍትህ ለብላቴናው መሐመድ #JusticeForMohammed

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 12 ቀን 2010 ዓም

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *