በመደበኛ ፍርድ ቤት የጊዜያዊ ቀጠሮ ሲታይ የነበረው የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር ስዩም ተሾመ ጉዳይ በአስቸኳይ አዋጁ በሚቋቋም ፍርድ ቤት እንዲታይ ተወሰነ። የመደበኛው ፍርድ ቤት ይህንን የወሰነው ፖሊስ በጠየቀው መሰረት ነው።

በግልጽ ስሜቱን በብዕሩ የሚገልጸውና፣ ጠንካራ አስተያየቶችን በተደጋጋሚ በማቅረብ የሚታወቀው ስዩም ተሾመ የታሰረው የወታደራዊ አስተዳደር በታወጀ ማግስት ነው። መምህር ስዩም ቁጥራቸው በርካታ ወታደሮች በመኖሪያ ቤቱ በድንገት መጥተው እንዳሰሩት እሀቱና ባልደረቦቹ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

ይህንኑ ተከትሎ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች እስሩን በመቃወም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ጠያቀዋል። እየጠየቁም ነው። ኢህአዴግ ከገባበት ቀውስና ከቀድሞው ስህተቶቹ መማር የማይችል መሆኑንን አግዝፎ በማሳየት ሲሞገት የቆየው ስዩም በጊዚያዊ ቀጠሮ ጉዳዩ ሲታይ የነበረው በፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ነበር።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ጌታቸው ሺፈራው በፌስ ቡክ ገጹ እንደዘገበው የአምቦ ዩኒቨርሲቲና ጦማሪ ስዩም ተሾመ ጉዳይ ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጭ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚቋቋም ፍርድ ቤት እንዲታይ የተወሰነው ፖሊስ ለፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በደብዳቤ በጠየቀው መሰረት ነው።

ትንታጉ በእረኛ ስዩም ተሾመ የካቲት 30/2010 ዓም በዋለው ችሎት ለመጋቢት 13/2010 ዓም የአስራ አራት ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶበት አለመቅረቡ ይታወሳል። ጦማሪ ስዩም ክስ ያልተመሰረተበት፣ ዋስትናም ያልተሰጠው ወይንም ክሱ ያልተቋረጠ በመሆኑ ፖሊስ ሊያቀርበው ይገባ እንደነበር በተጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ ፌደራል ፖሊስ ጦማሪ ስዩምን ያለቀረበበት ምክንያት እንዲገልፅ፣ ተጠርጣሪውንም እንዲያቀርብ ለመጋቢት 17/2010 ዓም ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ትናንት መጋቢት 17/2010 ዓም ጦማሪ ስዩም ተሾመ ፍርድ ቤት አልቀረበም። ፌደራል ፖሊስ ጦማሪ ስዩምን ከመደበኛው ፍርድ ቤት ውጭ በጊዜያዊ አዋጁ በተቋቋመ ፍርድ ቤት የማቅረብ መብት እንዳለው ገልፆ፣ የጊዜያዊ ቀጠሮ መዝገቡ እንዲዘጋ ጠይቋል። የፌደራል መጀመርያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በፌደራል ፖሊስ ጥያቄ መሰረት የጦማሪ ስዩም ተሾመን የጊዜያዊ ቀጠሮ መዝገብ እንደዘጋ ለማወቅ ተችሏል።

የካቲት 28/2010 ዓም የታሰረውን ጦማሪ ስዩም ተሾመ ፖሊስ የካቲት 30/2010 ዓም በፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ከቀረበ በኋላ በቀጣይ በሁለት ቀጠሮዎች ችሎት ሳይቀርብ ነው ውስኔው የተላለፈው። የአስቸኳይ አዋጁ ፍርድ ቤት መቼ እንደሚቋቋምና ስራ ጀምሮ ፍርድ እንደሚፈርድ እስካሁን አልተገለጸም። የወታደራዊ አስተዳደሩ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ እጅግ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ወገኖች በተነገረና ባልተነገረ ወይም ባልተገለጸ ምክንያት መታሰራቸው ይታወቃል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

በተለይም ከኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር መዋቅር ሃላፊዎች፣ የፖሊስና የጸጥታ ተጠሪዎችና የፖሊስ መኮንኖች የፍርድ ጉዳይ በተመሳሳይ በአስቸኳይ ጊዜ በሚቋቋመው የፍርድ ቤት ወይም በሌላ መደበኛ ችሎት ስለመታየቱ የታወቀ ነገር የለም።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *