ተፋዞ የነበረውን የፓለቲካ ትግል በማቀጣጠል ረገድ እውቅና የተሰጠው የቄሮ ትግል ይበልጥ እንደሚጠናከር ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ለዛጎል ገለጹ። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጊዜ ሊሰጣቸው እንደሚገባ የሚያምኑ ክፍሎች መኖራቸው ታውቋል። በሌላ በኩል ደግሞ ቄሮ የኦህዴድ አደረጃጀት በመሆኑ ኦህዴድ መስመሩን ከዘጋው ነገሮች የተገላቢጦሽ ሊሆኑ እነድሚችሉ ግምት የሚሰጡም አሉ።

የማይነካ የሚመስለውን የኢህአዴግ አደረጃጀት የበጣጠስው የቄሮ ንቅናቄ ከቀድሞው በበለጠ እንዲጠናከር የጉዳዩ ባለቤቶች አምነውበት እየሰሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ክፍሎች እንዳሉት ” የትግሉ ዋና ዓላም ጥገናዊ ለውጥ ሳይሆን ህዝብን የስልጣን ባለቤት ማድረግ በመሆኑ ነው”

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኦሮሚያ መገኘታቸውና ከኦህዴድ መወከላቸውም በበጎ ቢታይም ነገሮች በቀድሞው መልካቸው እንዲሄዱ የሚፈቅድ የህብረተሰብ ክፍል አለመኖሩን የዜና ምንጮች ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት የቀድሞው የአንድ ለአንድ አደረጃጀት ይሁን የተለየ፣ በዝርዝር ባይገለጽም ቄሮ የኦሮሞ የለውጥ ሃይል ከቀድሞው በበለጠ ስር የሰደደ አደረጃጀት እንዲኖረው ስራ መጀመሩ ገልጸዋል።

Related stories   Speaking Truth to Power, Samantha: Stop Defending Ethiopia’s “Proud Boys”!

ምንጮቹ እንዳሉት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጊዜ ሊሰጣቸው እንደሚገባ የሚያምኑ ወገኖች ቢያንስ አንድ ዓመት የመሸጋገሪያ አስትንፋስ እንደሚያስፈልግ ያምናሉ። አንዳንዶች ደግሞ ስድስት ወር በቂ ነው ይላሉ። በጊዜ ገደቡ ቢለያዩም ሁሉም ወገኖች በኦሮሚያና በፌደራል ደረጃ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ካልታየ ከቀድሞው በከረረ መልኩ ትግሉ እንዲቀጣጣል እምነት አላቸው።

” ጅምራቸው መልካም የሆነው ዶክተር አብይ ሕዝብን ለስልጣን የሚያበቃ ታሪክ የሚሰሩ ከሆነ ድጋፍ ያሻቸዋል” የሚሉት የዛጎል ምንጮች ” የወደቁት ለጋ ወጣቶች ደም፣ ጧሪ አልባ የሆኑት ቤተሰቦች፣ እናቶችና፣ አባቶችን በየትኛውም ጊዜ አይዘነጉም፤ ዶክተር አብይም ቢሆኑ ሰማዕት ሲሉዋቸው ይህንን ከልብ በመረዳት ነውና ትግሉን ገደል ይከቱታል ተብሎ አይታሰብም”  በማለት ተስፋቸውን ይገልጻሉ።

Related stories   The Legend of the “Greater Republic of Tigray” and the Delirious TPLF Media

አንድ ዓመት ጊዜ ቢሰጥም ትግሉን ይበልጥ የሚያጠነክር ስራ መሰራቱን መደበቅ እንደማይቻል ያመላከቱት የዛጎል ምንጭ፣ ትግሉን በውጭ ያሉ ወገኖች ትግሉን ከመደገፍ በዘለለ በሌላ ተግባር ውስጥ ለመሳተፍ መሞከራቸው ቀዳም ባሉት ጊዚያት ችግር መፍጠሩን መረዳታቸው እንደ ትልቅ መሻሻል እንደሚታይ ይናገራሉ።

በውስጥ አዋቂነት ዜናውን ያቀበሉት ወገኖች ካሁን በሁዋላ ለህዝብ መወገን ብቻ እንደሚያዋጣ ቢናገሩም የቄሮ ትግል ከቀድሞው በበለጣ ሊጥናከር እንደማይችል ግምታቸውን የሚሰጡ አሉ። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት ቄሮ የተጠቀመው የተሰበረውን የኦህዴድ አደረጃጀትና እምቢተኛንተን ነው።

ኦህዴድ እምቢተኛነቱን ካበቃና መዋቅሩን ጠግኖ ከቀጠለ ቄሮ የቀድሞውን ያህል ሊሳካለት እንደማይችል የገልጹ ” ለመተንበይ እጅግ ገና ቢሆንም፣ በጊዜ ሂደት የሚታይ ይሆናል” ሲል አስተያየታቸውን አክለዋል።

የኦሮሞን ህዝብ በማስተማርና በማንቃት ተሳታፊ የሆኑ ክፍሎች ለዶክተር አብይ ጊዜ እንደሚሰጥ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቢሰማም፣ አልፎ አልፎ ግድያን እስር መታየቱ እያደር ቅሬታ እንዲያሰሙ እያደረገ ነው። ዶክተር አብይ በበኩላቸው ደህንነቱና የጸጥታ ሃይሉ ከድርጀት ደጋፊነት የሚላቀቅበት አደርጃጀት እየተጠና መሆኑንና ወደ ተግባር እንደሚቀየር፣ በአገሪቱ ተአማኒነት ያለው ምርጫ እንደሚከናወን ማረጋገጣቸው፣ የበላይና የበታቸ የሚባል ነገር እንደማይኖር ወዘተ ቃል መግባታቸውን የተከታተሉ ተስፋ እየጣሉባቸው ነው።

Related stories   Sisi warns Ethiopia against continuing to fill Nile Dam during visit to Sudan

“ዶክተር መረራ ጉዲና በተደጋጋሚ እንደሚሉት ኢህአዴግ የሚደገፍባቸው የጸጥታና የደህንነት ሃይሉ ጣልቃ ገብነታቸው ከተገታ ህዝብ ይፈርዳል። ይህ ብቻውን በቂ ነው ” የሚሉ ወገኖች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃላ ከገቡባቸው ጉዳዮች ሁሉ አጉልተው አይተውታል። እናም ይህ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ለዚሁ ተግባር ፍንጭ ካሳዩ ድጋፍ በመስጠት መቀጠሉ አግባብ እንደሚሆን ያምናሉ። የመሳሳት መብት አንዳንዴም እንደሚፈቀድ ያሰምሩበታል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *