በቅርቡ በመከላከያ ሰራዊት በደረሰው ጥቃት ከሃዘን ያላገገመችው ሞያሌ በዛሬው እለት የከተማዋን ነዋሪዎች ግራ ያጋባ ጥቃት አስተናግዳለች። ከስፍራው በተገኘ መረጃ አራት ሰዎች ሲሞቱ ከሃምሳ በላይ ቆስለዋል። ጥቃቱ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ጥበቃ ስር እያለች መፈጸሙ አንጋጋሪ ሆኗል። 

ዛሬ ረፋዱ ላይ በከተማዋ መናኸሪያ ህዝብ በተሰበሰበበት በተወረወረ ቦንብ ነው አደጋው የደረሰው። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ የከተማዋን አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ ጠቅሶ ድርጊቱን የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል እንደፈጸመ ይፋ አድርጓል። በተጨማሪም የከተማዋ የህክምና ተቋም ቁስለኞች መቀበሉን ለኬንያ ሚዲያ ማረጋገጫ እንደሰጡ አመልክቷል።

moyale c

በቅርቡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በስማሌ ክልል በመገኘት የኦሮሚያ ክልል ፐሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳንና የሶማሌ ክልል መሪ አቶ  አብዲ አሌን እጅ ለእጅ በማያያዝ ሰላም ማብሰራቸው ይታወሳል። የቀደመው ተግባር ዳግም እንደማይፈጸም የሶማሌ ክልል ቃል ገብተው ነበር።

በቅርቡ አቶ ለማ መገርሳ ከ700 ሺህ ሰዎች በላይ ከሶማሌ ክልል መፈናቀላቸውን በመጥቀስ ጥፋተኞች ተጠያቂ እንደሚሆኑ መናገራቸውን ተከትሎ የተከሰተው ይህ የቦንብ ጥቃት ድንጋጤን ፈጥሯል። የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል በዘመናዊ መሳሪያ የተደራጀና ቁጥሩም ከፍተኛ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገለጽ መቆየቱም የሚታወስ ነው።

moyale d
በዛሬው እለት የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከመንግስት ወገን ይህ እስከተጻፈ ድረስ የተባለ ነገር የለም። በአሁን ሰዓት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተለይተው ወደ ያቤሎና ሌላ ሆስፒታል ተልከዋል።
ፎቶ ጃዋር መሃመድ ፌስ ቡክ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *