የኦሮሚያ ፐሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ አዲስ ሹመት የሻሸመኔ ከንቲባ የነበሩትን ወ/ሮ  ጠይባ ሃሰንን ምክትል ፐሬዚዳንት አድርጓቸዋል። ወይዘሮዋ በክልሉ ተነስቶ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ሻሻመኔ የተፈጸሙትን ግድፈቶች በድፍረት ሲተቹና ሲያጋልጡ የነበሩ ናቸው።

አቶ በቀለ ገርባ በአዳማ አቀባበል ሲደረግላቸው ከጎናቸው ሆነው ንግግር ሲያደርጉ የነበሩት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከአዳማ ከንቲባነታቸው ተነስተው ወደ ኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ሃላፊነት ተመድበዋል። ምደባው በተለምዶ ማግለያ እንደሆነ ይነገራል።

ኢህአዴግ ሊያገላቸው የሚፈልጋቸውን ሰዎች ወደ ጽህፈት ቤት የማዛወር ልምድ አለው። የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ከሆኑ በሁዋላ ድምጻቸው መጥፋቱ የሚታወስ ነው። አቶ ብርሃኑ በክልልም ይሁን በፌደራል ደረጃ ድምጻቸው ከጠፋ ስድስተኛ ዓመታቸውን አሳልፈዋል። ፋና የአዲሱን ሹመት እንደሚከተለው አቅርቦታል።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን መስጠቱ ተገለፀ። የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ሹመቶች የተሰጡት የክልሉ የማስፈፀም አቅም ከፍ ለማድረግ ነው። በተጨማሪም የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የክልሉ መንግስት ለፌደራል መንግስት የሚያደርገውን አስተዋፅኦ ከፍ ለማድረግ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል።


የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ በዚህም መሰረት፦ 

1. ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር

2. ዶክተር ግርማ አመንቴ የኦሮሚያ ክልል የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ሀላፊ

3. ዶክተር ነገሪ ሌንጮ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ 

4. አቶ አሰግድ ጌታቸው የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ፅህፈት ቤት ሃላፊ 

5. ወይዘሮ ጫልቱ ሰኚ የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ቢሮ ሀላፊ 

6. ዶክተር ሚልኬሳ ሚደጋ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ 

7. ዶክተር አለሙ ስሜ የኦሮሚያ የውሃ፣ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ 

8. አቶ ሲሳይ ገመቹ የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ ሃላፊ 

9. ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ የለገ ጣፎ ለገ ዳዲ ከተማ ከንቲባ 

10. ወይዘሮ እልፍነሽ ባዬቻ የአዳማ ከተማ ከንቲባ 

11. ወይዘሮ ዘይነባ አደም የአሰላ ከተማ ከንቲባ 

12. አቶ ሞሀመድ ከማል የአርሲ ዞን አስተዳዳሪ 

13. አቶ ለሊሳ ዋቅወያ የምእራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ 

14. አቶ ጫሊ ቤኛ የቡራዩ ከተማ ምክትል ከንቲባ 

15. አቶ ደስታ ቡኩሉ የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ 

16. አቶ ካባ ሁንዴ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ

17. አቶ አሰፋ ኩምሳ የኦሮሚያ የውሃ ስራዎችና ዲዛይን ኢንተርፕራይዝ ሃላፊ 

18. አቶ አበራ ቡኖ የምእራብ ጉጂ ዞን አስተዳዳሪ 

19. አቶ ነብዩ ዳብሱ የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ 

20. አቶ ቦጋለ ሹማ የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።

በተጨማሪም ኦህዴድ

1. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የኦህዴድ ማእከላዊ ፅህፈት ቤት ሃላፊ 

2. አቶ አዲሱ አረጋ የኦህዴድ የፖለቲካና የገጠር አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ 

3. አቶ ከፍያለው አያና የኦህዴድ የፖለቲካና የከተማ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አድርጎ ሹሟል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *