ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ” ከወልቃይት ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አደርጋለሁ” በማለት መናገራቸውን የአማራ ክልል የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አመለከቱ።


Image may contain: 1 person, standing and shoes
ሃላፊው በፌስ ቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዛሬ በጎንደር ከተማ ከህዝብ  ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነው።

“የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ በህግ አግባብ ሊፈታ እንደሚችል ህዝቡ ማመን አለበት ፡፡ ህገ መንግስቱ ይህን ጉዳይ ሊፈታ ይችላል፡፡ በቀጣይም ከወልቃይት ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አደርጋለሁ ብለዋል፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ በመወያየት ያሉ ጥያቄዎች መመለስ እንችላለን፡፡ ዋናው ነገር በዚህ ሂደት ውስጥ ሀይል የተቀላቀለበት እና ወደ ቁርሾ በሚያስገባ መንገድ መሆን እንደሌለበት ህዝቡ ሊያውቅ ይገባል ” ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መናገራቸውን ነው አቶ ንጉሱ ያስታወቁት።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

” የሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ  መፍትሄ መሰጠት አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ ድንበር ላይ ያሉ ሁለቱም ወታደሮች እንዲሸሹ እና በአካባቢው ያሉ የሁለቱም ወገን ሰዎች በሰላም እንዲቀሳቀሱ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ነገ ስራዬን እጀምራለሁ፡፡ ነገ በባህር ዳር ለጣና ፎረም ጉባኤ ከሚመጡት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጋር በተናጥል ውይይት አደርጋለሁ”በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።ሌሎች የተነሱ ጥያቄ እና አስተያየቶችን በተመለከተ በአንድ ቀን ጀምበር መመለስ እንደማይቻል፣ በሂደት ላይ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመመለስ እንዲያስችል ስራዎች በመጀመራቸውን ይሄነው ብለው ቃል መግባት እንደማይፈልጉ እና  በተግባር ማሳየቱ የተሻለ እንደሆነ ጠቁመዋል። በቀጣይ በግብርና ፤ በኢንዱስትሪ ፤ በገቢና በፍትህ ላይ መንግስት የትኩረት ነጥቦች ለይቶ መልስ ለመስጠት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትግራይ ባደረጉት ንግግር የወልቃይት የማንነት ጥያቄን ከመሰረተ ልማት ጥያቄ ጋር በማያያዝና፣ የሌሎች ሃይሎች ፍላጎት እንጂ የህዝቡ እንዳልሆነ በመሳል የሰጡት ምላሽ ከፍተኛ ወቀሳና ትችት እንዲሰነዘርባቸው ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም። ዛሬ ጉዳዩ በአገሪቱ የህገመንግስት ማዕቅወፍ ውስጥ እንደሚታይ መግለጻቸው አዲስ ጉዳይ ባይሆንም፣ የወልቃይት ኮሚቴ አባላትን ለማነጋገር ቃል መግባታቸው ተሰብሳቢውን እንዳስደሰተ ለማውቅ ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *