ያማማቶ ወደ አዲሱ ሃላፊነታቸው ሲመጡ ኤርትራንና ኢትዮጵያን የማስማማት ስራ እንደሚሰራ መናገራቸውን ዛሬ ላይ ማስታወስ ቅድሚያውን እንደሚይዝ የሚናገሩ አሉ። ሌሎች ደግሞ አሜሪካ ግንኙነትዋን ከተለያዩ ጥቅሞቿ አንጻር ከኤርትራ ጋር ለማደስ ዝግጅት ማጠናቀቋን የሚገልጹ መረጃዎች አሉ። 

ኤርትራ የለሁበትም በምትለው ከሽብርተኞች ጋር የተያያዘ ክስ ከ2009 ጀምሮ ማዕቀብ የተጣለባት ኤርትራ፣ እቀባው ከበርካታ ጉዳዮችና አካባቢያዊ ኩነቶች እንድትገለል ቢያደርጋትም ሁሉን ተቋቁማ ዛሬ ድረስ ለአሜሪካ እጅ አለመስጠቷን እንደ ትልቅ ኩራት የሚያነሱ ጥቂት አይደሉም። እነዚህ ክፍሎች በማዕቀቡም ሆነ በፖለቲካ መገለል ሳቢያ ኤርትራ ክፉኛ መደቆሷን ያምናሉ።

ከመካከለኛው ምስራቅ የአረብ አገራት ጋር ከፍተኛ ግንኙነት ያላቸውና  የባህር ይዞታ እየሸነሸኑ በማከራየት የሚጠቀሙት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ስለ ጉብኘቱ እስካሁን ያሉት ነገር ያለም። የአሜሪካን ባለስልጣናትንም እንደሚያገኙ አላስታወቁም። ከዛሬ ሶስት ዓመት ግድም በፊት የታሰሩት የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞች ጉዳይ አስመልክቶም የወጣ መረጃ የለም።  ዋዜማ እና ቢቢሲ ከታች ያለውን ዘግበዋል።

ዋዜማ ራዲዮ – በውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ምክትል ሀላፊ ዶናልድ ያማማቶ የተመራ የአሜሪካ የልዑካን ቡድን ወደ ኤርትራ አቀና።
የልዑካን ቡድኑ ከስኞ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በአስመራ በሚኖረው ቆይታ ከሀገሪቱ ባለስልጣናትና በአስመራ ተቀማጭ ከሆኑ የዲፕሎማቲክ ማህበረስብ አባላት ጋር ይነጋገራል።የልዑካን ቡድኑ ተልዕኮውን በይፋ አላሳወቀም።

የጉብኝቱ ዋና ተልዕኮ በኤርትራ መንግስት ተይዘው ለእስር የተዳረጉ የአሜሪካ ኤምባሲ ስራተኞች ጉዳይ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ነግረውናል።
እግረ መንገድም በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የድንበርና የፖለቲካ ችግር መፍታት በሚቻልበት መንገድ ላይ የልዑካን ቡድኑ ሀሳብ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የልዑካን ቡድኑን አግኝተው ለማነጋገር ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ማረጋገጫ አልሰጡም።

በአስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ስራተኛ የሆኑ ኤርትራውያን ሰራተኞች ያለፉትን ሶስት አመታት በእስር ላይ ናቸው። ስራተኞቹ ለአሜሪካ መንግስት መረጃ ታቀብላላችሁና ታሴራላችሁ የሚል ውንጀላ ቀርቦባቸው ነበር የታሰሩት።
ያማማቶ ኤርትራ ከጅቡቲና ከኢትዮጵያ ጋር የገባችበት የድንበር ቀውስና ጦርነትን በዘላቂነት መፍታት ዋና ተልዕኳቸውሊሆን እንደሚችል በእርግጠኝነት አስተያየት የሰጡን አሉ።

ለአሜሪካ መንግስት ምስጢር ቅርበት ያላቸው ምንጮች በበኩላቸው አሜሪካ በጅቡቲ ያላት የጦር ሰፈር አንድም በርካታ ሀገራት ተመሳሳይ የጦር ሰፈር በመክፈታቸው ሌላም የጅቡቲ መንግስት የአየር ተቆጣጣሪዎች በተደጋጋሚ ባሳዩት እንዝላልነት በተከሰቱ አደጋዎች ሳቢያ የጦር ሰፈሩን ወደ ኤርትራ የማዘዋወር ሀሳብ እየተብላላ ነው ይላሉ። ይህን አስተያየት ዋዜማ ከገለልተኛ ወገን አላጣራችም።

በቅርቡ ሁለት የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ቸልተኝነት ተላትመው መውደቃቸው ይታወሳል። ጅቡቲያውያኑ የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጫት አብዝተው በመቃምና በሌሎች የድስፕሊን ችግሮች በተደጋጋሚ ለተፈጠሩ ችግሮች ተጠያቂ መሆናቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት ያምናሉ። የጦር ሰፈር ኪራይንም በተመለከተ ጅቡቲ ያደርገችው ጭማሪ ዋሽንግተንን እንዳላስደሰተ ይነገራል።

አሜሪካ ከአስመራ ጋር ግንኙነቷን ማደስ ከፈለገች በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ችግር መፈታት እንዳለበትም የዲፕሎማቲክ ምንጮች ያሰምሩበታል።

ዶናልድ ያማማቱ በዚሁ ሳምንት ወደ ጅቡቲና ኢትዮጵያ አቅንተው በጋራና አካባቢያዊ ጉዳዩች ለመመካከር ዕቅድ መያዛቸውን ከአሜሪካ የውጪጉዳይ መስሪያቤት የተገኘ መረጃ ያመልክታል።

BBC Amharic– ከበርካታ ዓመታት በኋላ በአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን ወደኤርትራ የተደረገ ጉዙ እንደሆነ የተነገረለት ጉብኝት በአንድ የውጪ ጉዳይ ባለስልጣን እየተደረገ ነው።

የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ከሶማሊያው ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላት ተብላ በማዕቀብ ስር ወደምትገኘው ኤርትራ ያልተለመደ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የሆኑት ዶናልድ ያማሞቶ ከኤርትራ ባለስልጣናት ጋር ለመገናኘት ወደ አስመራ ያቀኑት ሃገሪቱ የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት ድጋፍ እየፈለገች ባለበት ወቅት ነው።

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት የጦር መሳሪያን ጨምሮ ማዕቀቡን የጣለው ከስምንት ዓመታት በፊት የተካሄደን ምርመራ ተከትሎ ኤርትራ አልሸባብን ጨምሮ ሌሎች በሶማሊያ ያሉ ታጣቂ ቡድኖችን ትደግፋለች በሚል ነበር። ነገር ግን የኤርትራ መንግሥት ይህንን እንዳልፈፀመ ሲያስተባብል ቆይቷል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ምክትል አምባሳደር ዶናልድ የማማቶ ከረጅም ግዜ በኃላ በኤርትራ ላይ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።

ለሦስት ቀናት በሚቆየው የአማባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ጉብኝት ከከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ያወጣው መግለጫ ያመላክታል።

በተባበሩት መንግሥታት አጣሪ ቡድን ምርማራ መሰረት የፀጥታው ምክር ቤት በኤእርትራ ላይ የጣለው ማዕቀብ ለሁለት ጊዜ እንዲራዘም ተደርጓል።

በዚህም ምክንያት ኤርትራ ከምዕራባዊያን ሃገራት በተለይ ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ግንኙነቷ ሻክሮ ቆይቷል።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በበኩላቸው አገራቸው ከኢትዮጵያ የገባችበት ለ20 ዓመት የቆየ ዕልባት ያላገኘ የድንበር ውዝግብ ላለመፈታቱ በተደጋገሚ አሜሪካንን ተጠያቂ ሲያደርጉ ይስተዋላል።

የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የሆኑት የዶናልድ ያማሞቶ ጉብኝት ኢትዮጵያንና ጅቡቲን የሚያካትት የአፍረካ ቀንድ ሃገራት ጉዞ ቢሆንም፤ የኤርትራው ጉብኝታቸው ግን የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።

አምባሳደር ያማሞቶ በአስመራ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሠራተኞች ጋርም የሚወያዩ ሲሆን፤ ቀጥሎም በጅቡቲ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የአሜሪካና የጅቡቲ የሁለትዮሽ ውይይት ላይ የሚሳታፉ የአገሪቱ ልኡካን ቡድንን መርተው ወደዚያው እንደሚያቀኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በመቀጠልም አምባሳደሩ ወደ ኢትዮጵያ በማምራት ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ጉዳዮችና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሏል።

ለመጀመርያ ግዜም ከአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል።

አምባሳደር ያማሞቶ ከሁለት ዓመት በፊት በኤርትራና ኢትዮጵያ ያለው አለመግባባት ለመፍታት እቅድ እንደነበራቸው ለጋዜጠኞች መናገራቸው ይታወሳል።

በዚሁ ጉብኝታቸው ሁለቱ አገሮችን ለማግባባት ይጥራሉ የሚል ግምት በብዙዎች ዘንድ ያለ ሲሆን፤ እስከአሁን በዚህ ጉዳይ ላይ ይምከሩ አይምከሩ በውል ማረጋገጥ አልተቻለም።

ላለፉት ሃምሳ ዓመታት የኤርትራ ጉዳይ ሲከታተሉ መቆየታቸውን የሚናገሩት ፕሮፌሰር ፍስሃፅየን መንግስቱ የአምባሳደር ያማሞቶ የአስመራ ጉብኝት የተለያየ ትርጉም ሊሰጠው እንደሚችል ይናገራሉ። “አንደኛ አሜሪካ በቀጣናው ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው። ሁለተኛ፣ የኤርትራ መንግስት በፀጥታው ምክርቤት የተጣለበትን ማእቀብ ለማስነሳት ከአሜሪካ ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖረው ስለሚፈልግ ይመስለኛል” ብሏል።

ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት ሊሻሻልል ይችላል ወይ? የሚለውን ሲመልሱ ” የኤርትራ መንግስት ለኤርትራ ህዝብ ያልጠቀመ ለኢትዮጵያ ሊጠቅም አይችልም” ይላሉ።

በኤርትራ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ተስፋ እንደሌለው ይናገራሉ።

“በውጭ ተፅዕኖ የሚመጣ ለውጥ ዘላቂ ኣይደለም። እንደ እኔ አስተያያት ዘላቂ መፍትሄ በኤርትራ ያለው ሁኔታ ሲያገኝ ብቻ ነው” ይላሉ።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *