የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃላፊ ዶክተር ዛይድ ራዓድ ከአባ ገዳዎች ጋር  ውይይት ባደረጉበት ወቅት ፣ ከህግ ውጪ ህይወታቸው ለጠፉ አካላት ናጣራት ተደርጎ በግህ እንዲጠየቁ እንዲደረግ መጠየቃቸው ታወቀ። የዛጎል የቅርብ ምንጮች እንዳሉት የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ፈጽመውታል የተባለው ይፋዊ ድርጊትና በሚስጢር የተሰበሰቡ መረጃዎች ለፍርድ ተደራጅተዋል።

በኦሮሚያ ክልል ላይ ላለፉት ሶስት ዓመታት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና በተቃውሞዎች ላይ ህይወታቸውን ስላጡ ግለሰቦች ምርመራ እንዲደረግ እንዲሁም ኃይልን ያለአግባብ የተጠቀሙ አካላትም ለህግ የሚቀርቡበት አካሄድ ሊዘረጋ እንደሚገባ  መጠየቁን ተከትሎ ” አቶ መለስን በዓለም የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለማቅረብ ዝግጅቱ ተጠናቆ ነበር ” ያሉት የጎልጉል ምንጭ መመሪያ የሰጡ፣ በይፋም ሆነ በሚስጢር  መመሪያ በመሰብሰቡ ወደ ተግባር የሚገባበት ጊዜ የተቃረበ ይመስለኛል፤ አስፈላጊው አካላት ዘንድ ከበቂ በላይ መረጃ ደርሷል” ብለዋል።

ቢቢሲ አማርኛ ይህንን ዘግቧል የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃላፊ ዶክተር ዛይድ ራዓድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶክተር አብይ አህመድ የተናገሯቸውን ንግግሮች ሊተገብሩ እንደሚገባ ገለፁ።

ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ መንግሥት ክልከላ ተደርጎባቸው የነበሩት ዶክተር ዛይድ በኢትዮጵያ መንግሥት የተደረገላቸውን ጥሪ ተከትሎም ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ነው ይህንን ንግግር ያደረጉት።

በጉብኝታቸውም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ያደረጓቸው ልብ የሚነኩ ንግግሮች ተስፋን እንዳጫሩ መገንዘብ እንደቻሉ ገልፀዋል።

በቅርብ ጊዜ የተከናወነው የስልጣን ሽግግር በሰላማዊ መንገድ መከናወኑን ጠቅሰው የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብአዊ መብት እንዲከበር መስራት እንዳለበትም ጠቅሰዋል።

ዶክተር ዛይድ ጨምረውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ላይ የነበሩ አለመረጋጋቶች የተፈጠሩት እኩልነት ባለመኖሩ መሆኑን ማመናቸውንም እንደ መልካም ጎን አይተው፤ “ዲሞክራሲ፤ ሰብዓዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ መብቶች በሌሉበት እውን እንደማይሆን፤ ግለሰቦች በነፃነት አስተያየታቸውን የመግለፅ መብት እንዲሁም በፈለጉበት መንገድ ያለማንም ጫና በመንግሥታዊ ሥርዓት የሚሳተፉበት መንገድ ሊኖር ይገባል” ብለዋል።

በቅርቡ እስር ላይ የነበሩ ጦማርያንና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መፈታታቸውን እንደ ጥሩ ጅማሮ አይተው “ከፍተኛ የሆነ ተስፋ እንዲሁም ፍራቻ በሰው ውስጥ እንደሰፈነ” ገልፀዋል።

ሃላፊው በቅርብ ከእስር ከወጡ ተቃዋሚዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ፓለቲከኞች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በኦሮሚያ ክልልም ከአባ ገዳዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ከአባ ገዳዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በክልሉ ላይ ባለፉት ዓመታት የተፈጠሩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና በተቃውሞዎች ላይ ህይወታቸውን ስላጡ ግለሰቦች ምርመራ እንዲደረግ እንዲሁም ኃይልን ያለአግባብ የተጠቀሙ አካላትም በኃላፊነት የሚጠየቁበትም ሁኔታ እንዲመቻች እንደጠየቁም ገልፀዋል።

ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ተቃዋሚዎች ጋር ባደረጉትም ንግግር ቀሪ እስረኞች እንዲፈቱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ፣ የእስር አያያዝና የፍርድ ቤት ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ እንዲሁም የተቀቋማት ነፃነት እንዲጠበቅ እንደጠየቁ ገልፀዋል።

እነዚህንም ጥያቄዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ጋር በተገናኙበት ወቅት እንደተወያዩባቸውም ዶክተር ዛይድ ገልፀዋል።

ውይይቱን ከተሳተፉት መካከል አንዱ የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በእስር ቤት ወስጥ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲሁም እንደ መፍትሄ ሊያቀርቧቸው የሚችሉ ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩ ገልጿል።

ከዚያም ባለፈ አዲሱን የጠቅላይ ሚኒስትር አስመልክቶ ያሏቸውን ተስፋዎችም አስመልከቶም “አጠቃላይ የሥርዓት ችግር መሆኑን ፤ አሁን የሚታየው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚደርሰው ኢህአዴግ ለ27 ዓመታት የያዘው ርዕዮተ-ዓለም ውጤት መሆኑን” ገልጿል።

የሰብዐዊ መብቶች ጉባኤ ምክትል ሊቀ-መንበር አምሃ መኮነን በበኩላቸው የኮሚሽነሩ ጉብኘት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እንደሆነ ይናገራሉ።

“ጉብኝታቸው የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ትኩረት መስጠቱን ያሳያል” ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በገዛ ፍቃዷ በሯን ክፍት ማድረጓ እንደ አንድ መልካም ጎን እንዳዩት ዶክተር ዛይድ ገልፀዋል።

በመጀመሪያ ጉብኝታቸው ወቅት ከመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከተቃዋሚዎች እንዲሁም በእስር ላይ የነበሩ ግለሰቦችን እንዳነጋገሩ ገልፀው፤ ምንም እንኳን የሚመሰገኑ ጉዳዮች ቢያገኙም ነገር ግን የሰብዓዊ መብት ይዘትና እንዲሁም ተግዳሮቶች በግልፅ እንደገመገሙና በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልል ተነስተው በነበሩ ሀገራዊ ተቃውሞዎችና ያለ አግባብ ኃይል ጥቅማ ላይ የዋሉባቸውን ቦታዎች ለማየት እንደጠየቁ ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በተባበሩት መንግሥታት የምሥራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መካከል የመግባቢያ ሰነድ እንደተፈረመና ይህም በአገሪቱም ሆነ በክልሉ ላይ ድርጅቱ ለመስራት የሚያስችል እንደሆነ ጠቅሰዋል።

“በከፍተኛ ደረጃ መሻሻል ለሚያስፈልጋቸው ፀረ-ሽብር አዋጁና የሚዲያ ህግጋት እንደገና ሊሻሻሉ የሚችሉበትን መንገድ አቅጣጫ ለመስጠትና ድጋፍ ለመስጠት ጠይቀናል” ብለዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *