“ሰሞኑን ሚድሮክ ኩባንያ በለገደንቢ የወርቅ ፍለጋና ቁፋሮ ሥራ እንዲሰራ የተሰጠው ፍቃድ ለሌላ 10 ዓመት መታደሱ ተገልፆአል ። ይህም ብዙዎቻችንን አስቆጥቷል።

“ለአለፉት 20 ዓመታት ኩባንያው በሕዝባችን ላይ፥ በአካባቢው፥ እና በቤት ውስጥና በዱር እንስሳት ላይ ያደረሰውና አሁንም እያደረሰ ያለውን ጉዳት (የሰው ሞት፥ የአካል መጉደል፥ የፅንስ ማስወረድ፥ ሁለ-ገብ የጤና መቃወስ፤ የአየር፥ የውሃ፥ እና የአፈር መበከል፤ የእንሰሳት ማለቅ፥ የአእዋፍት መሰደድ ወዘተ) እንዳላየ በማለፍ መንግሥት የፈቃድ እድሳት መፍቀዱ ለሕዝባችን ስቃይ ቅንጣት ታህል ግድ እንደሌለው አስረግጧል።

“የሚመለከታቸው የአካባቢውና የክልሉ ባለስልጣናት ጉዳዩ በተደጋጋሚ ቢገለፅላቸውም “እስካሁን ድረስ ከሃሜት የዘለለ፥ ያየነው፥ ደረሰ የሚባል ጉዳት የለም፤ ወዘተ” በማለታቸው ለሕዝቡ ያላቸውን ንቀት አሳይተዋል።

“እስከአሁን ሕዝቡ፥ መንግሥት ፍቃዱን እንዲሰርዝና ሚድሮክን እንዲያሰናብት፥ ለሕዝቡም በግልና በጋራ ለደረሰባቸው ጉዳት በሕግ አግባብ ካሳ እንዲከፍል እንዲያስገድድ ለማድረግ በሰላማዊ ሰልፍና በአቤቱታ ጫና እያደረገ ይገኛል።

“መንግሥት ፍቃዱን በመሰረዝ ተገቢውን ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ቄሮና ሕዝባችን በቀጥታ በኩባንያው ላይ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳሉ።

“ሚድሮክ ማለት ትልቅ ድርጅት ነው። ሚድሮክ የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን አምራች ድርጅት ብቻ አይደለም። በስሩ የሚያስተዳድረው ሞሐ የመጠጥ ፋብሪካ፥ ሻላ ወተት፥ ደርባን ሲሚንቶ፥ MPI፥ ድል ቀለም፥ ዋልያ ብረታብረት፥ የመሳሰሉትን ፋብሪካዎች አሉት።

“ከነዚህ ድርጅቶች መካከል አብዛኛው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያሉ ናቸው። አንዳንዶቹም ኦሮሚያ ክልልን አቋርጠው በሚያልፉ ተሽከርካሪዎችና የተለያዩ ማሽነሪዎች እየተገለገሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ሥራ እንደሚያከናውኑ ይታወቃል።

“የለገደንቢን የወርቅ ማዕድን ማውጫ ለማስቆም የግድ ሻኪሶ መሄድ ሳያስፈልግ፥ ቄሮ በያለበት በበሩ የሚያልፉትን የሞሐ መጠጥ ፋብሪካ መኪኖችን፥ የሾላ ወተት ፋብሪካ መኪኖችን፥ የደርባን ሲሚንቶ ፋብሪካ መኪኖችን፥ ወዘተ ማስቆም ይችላል። “በዛውም ከሚወሰዱት እርምጃዎች የተነሳ ሚድሮክ እስከዛሬ ላጠፋው ጥፋት የእጁን ያገኛል።

“የኦሮሞ ሕዝብ ሚድሮክንም ሆነ እርሱን የሚንከባከበውን መንግሥት የሚታገስበት አቅም፥ የሚሸከምበት ጀርባ የለውም። አምባገነኖች ከዚህ በኋላ የኦሮሞን ህዝብ ተጭነው መግዛት እንደማይቻላቸው ትልቅ ትምህርት ይሰጣቸዋል!!

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

1 Comment

  1. ምን ማለት ነው የጠፋውን አስተካክሎ በሀገሪቱ እድገት ውስጥ ያለውን አስተዋጽኦ ማስቀጠል እንጂ አንሸከመውም ምናምን ማለትን ምን አመጣው?
    እሄን ከመናገር በፊት እኔ ለሀገሬ ከወሬ ባለፈ ምን ሰራሁ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *