የጀግና ረሃብ ያነከተው ሕዝብ ሞላጫና ስለት እንደበት ያላቸውን ፖለቲከኛ ነን ባዮች በስሜት እያወደሰ መልሶ በሃዘን አፉን ሲጠርግባቸው ማየት የተለመደ ነው። የጀግና ረሃብ የማይሆኑ ቁማርተኞች ላይ ደጋግሞ አንጥፎናል። ጠባሳችን በቀላሉ የሚሽር ባለመሆኑና ካለፈው የጫጫታ ፖለቲካ ድምር መማር ባለመቻላችን  ኢህአዴግ ጢቢ ጢቢ ይጫወትብናል

በቀለ ገርባ7

የኢትዮጵያን ባንዲራ አንቋሸሹ የተባሉት ይህንን ሲናገሩ የተሳደቡ ከንፈሮች ምን ይላሉ? …የኢትዮጵያ ባንዲራ ከልጅነታችን ጀምሮ ይዘነው ያደግን፣ ይዘነው የተሰለፍን፣ ስናከበረው የኖርን፣ በውስጣችን አብሮ አድጎ የመጣ ባንዲራ ነው። ዛሬ ዝም ብለን ልንጠላው አንችልም … አቶ በቀለ ገርባ

 

አቶ በቀለ ገርባ ወደ አሜሪካን ከመጡ ከሰዓታት በሁዋላ ውግዘት እንደ ተቀጣጥይ ፈንጂ ተለቀቀ። በኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ በኩል “የኢትዮጵያን ባንዲራ አራከሱ” በሚል ተቃውሞ ሳይሆን ስድብ ሳይበሩን ሞላው። ጉዳዩ የሚገርም ስለነበር እሳቸው በኦሮምኛ ተናገሩት የተባለውን አዳመጥኩ። የተተረጎመውንም አነበብኩ። በጀግና ጥማት የተመታ፣ አስተዋይ መሪ የራበው፣ የሚያምነውና ፈሪሃ አምላክ ያለው መሪ የናፈቀው ሰው ” ቢወድቅ እንኳን እንዴት ወደ ላይ ይወድቃል” ስል አስተያየቴን በሃዘኔታ ሰጠሁ። ድርጊቱንም ተራ ጫጫታ ስል ሰየምኩት። አዎ የበርሜል ተራ ኳኳታ!!

ጋዜጠኛ Melkam-selam Molla ኦቦ በቀለ ገርባ በኦሮምኛ ተናግረውታል የተባለውን ማብራሪያ የአማርኛ ትርጉም ገፁዋ ላይ እንደሚከተለው አስፍራለች

ኦቦ በቀለ ገርባ ለምን አቀባበል እንዳልተደረገላቸው ለOMN በሰጡት ቃለ መጠይቅ  ኦሮምኛ ለማትችሉ ትርጉሙን እነሆ
ለኔና ለእስክንድር ነጋ ትልቅ አቀባበል ሊያደርጉልን እንደነበረ ቀድመው ነግረውን ነበር ይሁን እንጂ እኔ እንደዚህ አይነት አቀባበል ነግሬያቸው ነበር ምክኒያቱም ይመጣሉ ተብለው የተነገሩን በሺዎች የሚቆጠሩ እንደሆኑ ነው እነዚህ ሰዎች ሲመጡ ደግሞ መንግስትየማይቀበለውን ባንዲራዎች ይዘው ሊመጡ ይችላሉ በዛ ላይ የተለያዩ መፈክሮችን ቢያሰሙ እኔ እንደዛ አይነት በመገኘቴ ሊያስጠይቀኝ ይችላል ብዬ በመስጋቴ ነው በዛ ላይ ነገ ወደ ኢትዮጵያ መመለሴ አይቀርም ባለው ህግ ስር ስለምተዳደር ያኔ ደግሞ ሊያስጠይቀኝ ይችላል ከማለት ስጋት ተነስቼ ነው በዛ ላይ ውስጤ ያላመነበትን ነገር ሃላፊነት ውስጄ ችግር ውስጥ መግባት ስላልፈለኩ ነው ለዛ ነው እንጂ ስለ እውነት ትልቅ አቀባበል ሊደረግልን ታስቦ ስልክ ራሱ ለብዙ ጊዜ ነበር የተደወለልን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊቀበሉን እንደተዘጋጁና ከመቶ በላይ መኪኖች እንደተዘጋጁ ነግረውን ነበር ነገር ግን እኔ ነኝ እንደማልፈልግ የነገርኳቸው ይህንንም የወሰንኩት በራሴ ነው ይሁን እንጂ የኛ ሰዎ የምገባበትን ሰአት የሚያውቁ አቀባበል አድርገውልኛል እኔም ከዛ በላይ አልፈልግም ነበር ስላዘጋጁልኝም አቀባበል በጣም አመስግኜ በራሴ ፍላጎት እንደቀረሁ ላሳውቅ እወዳለሁ”

ከዚያ ሁሉ ውግዘት በላይ ያሳሰበኝ አንድ ነገር ነው። አንድ ሰው አንድ ነገር “አልወድም” ቢል እንኳ እንዴት ነው “ውደድ” የሚባለው? በግድ? በስድብ? በውግዘት? በአድማ? በማብጠልጠል? ክብርን በመንካት? ከዚህ ጭንቀቴ ስነሳ የአገራችን ፖለቲካ ፈትፋቹ የበዛበት፣ የጨረባ ሰርግ ነው ብል ለሚሰነዘረው ወቀሳ ቁብ የለኝም።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

አገርን ሳይሆን ቡድንን ማዕከል ያደረገ አሰላለፍ የት ያደርሰን እንደሆነ ማሰብ በሽታ ላይ ይጥላል። እነ አቶ መለስ በፍረጃ የጀመሩት ትግል ፍሬው አገሪቱን እያነፈራት ባለበት በዚህ ሰዓት እንዴት የመፈራረጅ ፖለቲካ ላይ ተተክለን ካልሞትን እንላለን። በቀለ ገርባ ” ምክንያት መስጠትና መታሰር የለብኝም” ሲሉ ያሰቀመጡት እውነት ” ትግሉ አላለቀም” የሚል ነው። ቢታሰሩ ትግሉ ጨራሽ ይጎድልበታል። ይህንን ማለት እንዴት ያሰድባል?

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

የኢትዮጵያን ባንዲራ ለይተው አለመናገራቸውን በማስታወስ ሲያስረዱ “የተከለከሉ” በማለት የሁሉም ቡድኖች ባንዲራ ወይም መለያ፣ ወይም አርማ አቀባበሉ ላይ ቢታይ አገር ቤት ትግሉን ለመቀጠል ሲመለሱ ” ምክንያት” ሆኖባቸው እንዳይታሰሩ በማሰብ መናገራቸው ሩቅ አሳቢ እንጂ እንዴት ተወቃሽ ያደርጋቸዋል?

አቶ በቀለ ስለ ጎንደር፣ ሰለ ወልቃይትና ሰለ ሰው ልጆች መከበር ያቀረቡት እምነታቸው እጅግ ትርጉም አለው። የወልቃይትን ጉዳይ የማንነት ብቻ እንዳልሆነ፣ የድንበር ጉዳይ በመሆኑ እስከ መጨረሻው የትግሉ አካል መሆን እንደሚፈልጉ፣ የጎንደር ሕዝብ እስር ቤት እያሉ ምስላቸውን አንስቶ ላደረገው ትዕይንት ልዩ ክብር እንዳላቸው በገሃድ ተናግረዋል።

 
 
 
 
[wpvideo tKTUbA53]

አቶ በቀለ የሰው ልጆች ሁሉ በመረጡት ሲዳኙ ብቻ ሰላምና ዴሞክራሲ እንደሚሰፍን ሲያመልክቱ፣ ትግሉን ዳር ለማድረስ እንደሚተጉ በመግለጽ ነው። ለመታገልና ለማስተባበር ደግሞ እስር ቤት መቀመጥ የለባቸውም። ዲያስፖራው እሳቸውን ጨምሮ እስር ላይ ያሉ እንዲፈቱ ላበረከተው አስተዋጾ አመስግነዋል።  በፈጣሪ ስም ክበረት ሰጥተዋል።

ይሁን እንጂ ለሰው ልጆች መብት መከበርና ነጻ መሆን ሲታገሉ ከነበሩት መካከል እጅግ ጥቂት የሚባሉ በመረጃ እጥረት፣ “እኔ ብቻ” ከሚል መረን የወጣ አስተሳሰብ፣ መነሻቸው በግልጽ ከማይታወቅ አካላት ሲሰነዘሩ የነበሩ አስተያየቶችን ጨምሮ ብዙ ታዝበናልና አሁንም ለወደፊቱ እርምት ቢወሰድበት?

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

አቶ በቀለ ገርባ ካጠፉ በሰለጠነ መንገድ እንዲማሩበት ሊተቹ፣ ሊገሰጹና ሊወገዙ ግድ ነው። ግን ቁንጽል ጉዳይ ተይዞና ከአንድ ኮዳ የሚጨለፍ መረጃ በማንገብ ለዘለፋ መክለፍለፍ መድረሻው ኪሳራ ብቻ በመሆኑ በማንም ላይ ሊደረግ አይገባም።

 
 
 
 
[wpvideo hbYB8j6K]

አቶ በቀለና አቶ እስክንድ ነጋ ወደ አሜሪካ ሲመጡ ትኩረት ሊሰጠው የነበረው አብይ ጉዳይ እንዴት መጡ? ለምን መጡ? ማን አመጣቸው? መጥተው ምን ሰሩ? ምን ውጤት አለው? የሚለው ሊሆን ይገባ ነበር። አቶ በቀለ በገሃድ እንደተናገሩት እሳቸውንና አቶ እስክንድር ጨምሮ የተጋበዙት አቶ ኦባንግ ሜቶ በሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የተሰኘው ድርጅት ነው።

አቶ ኦባንግ ሜቶ ወደ አሜሪካ እንዲመጡ ግብዣቸውን ሲያስቡና ሲያካሄዱ በአሜሪካ መንግስት ደረጃ እውቅና አግኝተው፣ ፈቃድና ደጋፍ ተጸጥቷቸው፣ ሌሎችም ጉዳዮች በህግ አግባብ ተደግፈው መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ዙሪያ ከአቶ ኦባንግ ጋር የምናደርገውን ቆያታ በሳምንቱ ማብቂያ ላይ እናትማለን።

አቶ ኦባንግ፣ ጥቁሩ ሰው በሰከነና ስልትን መሰረት በማድረግ የሚያከናውኗቸውን ጉዳዮች በየጊዜው ይፋ ማድረግ የማይፈልጉ፣ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ባለበት ሁሉ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ታጋይ መሆናቸው የሚታወቅው ነው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *