ለበርካታ ጋዜጠኞች ከሥራ መፈናቀል፤ ከአገር መሰደድ ምክንያት እንደሆኑ የሚነገርላቸው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅነት ዘርዓይ አስገዶም ከሥልጣናቸው ተነሱ። አቶ ዘርዓይ በሥልጣን በቆዩባቸው ዓመታት ሦስት ብቻ በአማርኛ የሚታተሙ ጋዜጦች ነበሩ

የህወሓት ዓላማ በማስፈጸም የሚታወቁት አቶ ዘርዓይ ፣ለረዥም ጊዜ ከነበሩበት ሃላፊነት መነሳታቸው በሚዲያ ነጻነት ዙሪያ ለውጥ ለማድረግ መታሰቡን አመላካች እንደሆነ ነው የተመለከትው፤ እንደ ታላቅ አዎንታዊ እርምጃም ተወስዷል።

አንዳንድ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በላይ በቀለ፣ መሠረት አታላይ፣ ዮናስ ዲባባ፣ አስካለ በላይ፣ ካሳሁን ፈይሳ፣ እና ሌሎችም የሙያው ሰዎች በአቶ ዘርዓይ የተነሳ ከሥራቸው እንዲለቁ መገደዳቸው በስፋት ሲገለጽ ቆይቷል፤

አቶ ዘርዓይ በሥልጣን በቆዩባቸው ዓመታት ሦስት ብቻ በአማርኛ የሚታተሙ ጋዜጦች የነበሩ ሲሆን በክልላዊ ነጻነት የሚንቀሳቀሱትን የአማራ ሚዲያና የኦሮሚያ ብሮድካስትን በመዝለፍ የሚታወቁ መሆኑን የዞን ፱ ጦማሪ አጥናፍ ብርሃኔ ትዊት አድርጓል። የጋዜጠኛነት ወይም የጋዜጣ ማተም ፈቃድ ለማውጣት ቢሮው የሚሄዱ ሁሉ ከፍተኛ የሆነ የማንነት ምርመራ እንደሚካሄድባቸውና ፈቃድ እንደሚከለከሉ አጥናፍ ጨምሮ ጠቅሷል።

http://www.goolgule.com/wp-content/uploads/2018/05/solomon-appointed.jpg

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በተጻፈ ደብዳቤ ዘርዓይ አስገዶም ከቦታቸው ተነስትው በምትካቸው የደኢህዴኑ ሰሎሞን ተስፋዬ ተሹመዋል። አዲሱ ተሿሚ የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን ምክትል ሥራ አስኪያጅ በመሆን ያገለገሉ ናቸው።

አቶ ሰሎሞ የድርጅት ተሿሚ በመሆናቸው ብዙ ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ ቢገመትም፣ የአቶ ዘርዓይ መነሳት ግን ድርጅቱን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በነጻነት እንዲሠራ የሚያስችለውና በክልል የሚዲያ ሥራዎች ላይ ተጽዕኖ እንዲነሳ የሚያደርግ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህም በተጨማሪ ለጋዜጠኝነትና የጋዜጣ ኅትመት ሥራ ፈቃድ ለማውጣት የሚደረገውን ከማንነት ጋር የተያያዘ አፈናና ክልከላ በማስቆም ለግሉ ፕሬስ አንጻራዊ ነጻነት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘርዓይ አስገዶም፤ ሃጫሉ ሁንዴሣ “ቄሮ አራት ኪሎ ግባ” በማለት በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀረበውን ዜማ አጥብቆ የተቃወሙና “ጸረ ሕዝብ ነው” በማለት መኮነናቸው ይታወሳል። አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትርና አቶ ለማ መገርሳን ጨመሮ ከፍተኛ የኦህዴድ ባለስልጣናት በተገኙበት ዘፈኑ በቀጥታ ስርጭት በኦሮሞያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) በመተላለፉ ኦቢኤንን በመኮነን የዛቻ ንግግር ማድረጋቸው በበርካቶች ዘነድ ተቃውሞንእንዲሰነዘርባቸው አድርጓል፤ የአማራ ሚዲያንም የቴዲ አፍሮ ዘፈን ላይ የሚታየው ኮከብ አልባው ሠንደቅ ዓላማ በስብሰባዎች ላይ ሲታይ ምንም ሳይሉ በማስተላለፋቸው ዘርዓይ ወቀሳ ማቅረባቸውም አይዘነጋም፤
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሶስት የህትመት ውጤቶች ብቻ አላት
(ፎቶ፤ ዘርዓይ አስገዶም፤ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ)

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *