አቶ ስብሃት ነጋ በፊት ለፊት ከሚታወቀው ሃላፊነታቸው በዘለለ በህወሃትም ሆነ በኢህአዴግ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪና ናቸው፤ አቶ ስብሃት አቶ መለስን በማንገስ የሚታወቁና በድርጅቱ ውስጥ ያላቸው ሚና የገዘፈ በመሆኑ በህየውት እያሉ ከሃላፊነት ይነሳሉ ብለው የሚገምቱ አልነበሩም፤

አዲስ የተጀመረው የሪፎርም አካል እንደሆነ የተነገረለት ሹም ሽር መቀጠሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አስታውቋል፤ በዚሁ መሰረት አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ አምስት ከፍተኛ ሃላፊዎች ስራ እንዲለቁና በጡረታ እንዲያርፉ ተወስኗል፤

ፋና የሚከተለውን ብሏ

አምስት የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጡረታ እንዲያርፉ መደረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጽህፈት ቤቱ፥ ሀገሪቱ እያካሄደች ያለችው ሪፎርም የተሳካ እንዲሆን የማድረጉ ስራ እንዲሁም ለህዝቡ የልማትና ለውጥ ፍላጎት ተገቢ ምላሽ የመስጠቱ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያግዙ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ ብሏል።

ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እያካሄዱት ያለው የካቢኔ ለውጥ እንደሚገኝበትም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በአዳዲስ ኃላፊዎች እንዲመሩ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ያለው ጽህፈት ቤቱ፥ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለበርካታ ዓመታት በመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም በጡረታ እንዲያርፉ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት በጡረታ እንዲያርፉ የተደረጉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች

1. አቶ ስብሐት ነጋ- የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል

2. ዶክተር ካሱ ኢላላ- ከፖለሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል

3. አቶ በለጠ ታፈረ- ከተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም፣ ዕቅድና ፖሊሲ ዝግጅት ፕሮጀክት

4. አቶ ታደሰ ኃይሌ – ከንግድና ኢንዱስትሪ የፖሊሲ ዕቅድ አፈጻጸምና ክትትል

5. አቶ መኮንን ማንያዘዋል- ከፖሊሲ ምርምር ማዕከል

በቀጣይም ረዥም ጊዜ በመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉ በጡረታ እንዲያርፉ የማድረጉ ሥራ እንደሚቀጥልም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *