አፍሪካ በቅኝ ግዛት ስር ውላ በምትማቅባቸው ዓመታት ኢትዮጵያዊው ካፒቴን አለማየው አበበ የ32 ዓመት ወጣት በነበረበት እ.ኤ.አ 1957 የDC-3/c-47 የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ነበሩ፡፡

አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ 1946 ይሰጠው የነበረው የንግድበረራ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚቻል ሁኔታ በአሜሪካን አብራሪዎችና የበረራ ሰራተኞች ቁጥጥር ስር ነበር፡፡

በዚህ ወቅት ካፒቴን አለማየው በአፍሪካውያን ያልተደፈረውን የበረራ ሙያን በማጥናት ፋና ወጊ ሆነዋል፡፡  ኢትዮጵያዊው ካፒቴን አለማየው አበበ በ1951 አየር መንገዱ አሰልጥኖ ካስመረቃቸው 4 አውሮፕላን አብራሪዎች አንዱ ሲሆኑ እ.ኤ.አ በ1962 ቦይንግ 720B አውሮፕላን በማብረር አትላንቲክ ውቅያኖስን ያቋረጡ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ በመሆን ታሪክ ሰርተዋል፡፡

ካፒቴን አለማየው “ሂወቴ በምድርና በአየር” በሚል እ.ኤ.አ 2005 ላይ ባሳተሙት ማስታወሻቸው አንድ አፍሪካዊ አውሮፕላን አብራሪ ሲያጋጥሙት የነበረውን ውጣ ውረድ ፅፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በወቅቱ ይጠቀሙ የነበሩት በአብዛኛው የውጭ ዜጎች በመሆናቸውና በጥቁር አብራሪ አገልግሎት ለማግኘት ፍላጎት የላቸውም በሚል ምክንያትም ጭምር በአገራችን አብራሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ይደረግባቸው እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ካፒቴን አለማየው በፓይለትነት ዘመናቸው ምንም አይነት የማብረር እክል እንዳላጋጠማቸው ይልቁንስ አብራሪው ነጭ ባለመሆኑ ምክንያት በተሳፋሪዎች ይሰማቸው የነበረው መሸበር ግን ከባድ እንደነበር በማስታወሻቸው አስፍረዋል፡፡

ከአፍሪካ ዜና ጋር በተያያዘ በርካታ የአፍሪካ አገራት በቅኝ ግዛት ስር በነበሩበት በ1960ዎቹ ጥቁር የአውሮፕላን አብራሪ ማየት እንኳን ለሌሎች ለኢትዮጵያውያንም ጭምር እንደ ዘመን ክስተት የሚቆጠርና ያልተለመደ እንደነበርም ይነገራል፡፡

 

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 25/1925 በሀረር ክፍለ ሀገር የተወለዱት ካፒቴን አለማየው አበበ ገና በለጋ እድሜያቸው ነው አውሮፕላን ወድቆ ሲከሰከስ ተመልክተው አብራሪ ለመሆን ፍላጎት ያደረባቸው፡፡

ካፒቴን አለማየው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለ30 ዓመታት በጥብቅ ዲሲፕሊንና ታታሪነት እንዳገለገሉም የግል ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ካፒቴኑ ባለፈው ታህሳስ ወር በ93 ዓመታቸው ባጋጠማቸው ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ካፒቴን አለማየው በህይወት ዘመናቸው 6 ልጆችና 4 የልጅ ልጅሎች አፍርተዋል፡፡

ምንጭ፡ ፌስቱፌስ አፍሪካ – EBC

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *