ሰሞኑንን የአቶ አንዳርጋቸው  ጽጌ ከእስር መፈታት በስፋት እተነገረ ቢቆይም፣ የይቅርታ ድብዳቤያቸው ፕሬዚዳንት ሙላቱ ዘንድ ቀርቦ እንዲፈቱ መወሰኑ ታወቀ። ከቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህ እንደሚሆን ተናግረው ነበር።

Image result for andargachew tsigeየትግራይ ተወላጆችን በቤተ መንግስት ሰብሰበው የነበሩት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “አቶ አንዳርጋቸውን በማሰራችን የተጠቀምነው ነገር የለም።የተረፈን ጥላቻና ከእንግሊዝ መንግስት 11 ቢሊዮን ዶላር ማጣታችን ብቻ ነው።” ማለታቸውና አቶ አንዳርጋቸው በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚፈቱ መናገራቸው የአቶ አንዳርጋቸውን መፈታት ለሚቃወሙ ህክምና ለመስጠት ነበር።

አንዳርጋቸው ጽጌ ከታሰሩ በሁዋላ በየዕለቱ ይፋ የሚሆኑት ምስሎቻቸው እጅግ ልብን የሚነኩ፣ የሚያስገርሙና ስብእናቸውን የሚያመላክት እንደሆነ በርካቶች አስተያየት የሚሰጡበት ነው። በኤርትራ በረሃ ህይወታቸውን እንዴት እንዳሳለፉ የሚያሳዩት የአቶ አንዳርጋቸው ምስሎች ልዩ ታሪክና ማብራሪያ እንዳላቸው በርካቶች ይጠብቃሉ። 

አብዛኞች እንደሚሉት አቶ አንዳርጋቸው ቅድሚያ ለቤተሰቦቻቸው ያስፈልጋሉ። የተያዙበት መንገድ ብዙ የሚያነጋግር፣ ለመቀበል የሚያስቸግርና፣ የጠራ መረጃ ያልቀረበበት ቢሆንም አቶ አንዳርጋቸው ከሚወዷቸው ቤተሰባቸው ጋር ሲቀላቀሉ ለማየት የሚጓጉ ወገኖች ጥቂት አይደሉም።

ዝግጅት ክፍሉ

የአንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ቅድሚያ ለልጆቹና ለቤተሰቦቹ፣ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን መልካም ዜና መስማት አስደሳች ነው፤ የልጆቹ እንባ ያማል፤ አዎ አንዳርጋቸው ያስፈልጋቸዋል እንኳን ደስ ያላችሁ!! ዝግጅት ክፍላችን ቀሪው ዘመናችሁ ልባችሁ የሚጠገንበት፣ ፍቅራችሁን የምታጣጥሙበት፣ የቤተሰብ ወጋችሁን የምትኮመኩሙበት ይሁንላችሁ!!

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *