በሕዝብ ትግል አቶ አንዳርጋቸውን ከሞት ቅጣት የመነጨቀውን ውሳኔ ተከትሎ የፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በኢሳት እና ኦ ኤም ኤን የቴሌቪዥን የሚዲያ ተቋማት፣  በተጨማሪም በዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና ጃዋር መሀመድ ላይ የከፈተው ክስ እንዲቋረጥ በጠየቀው መሰረት ክሱ መነሳቱ ተሰማ።

33161844_2069498069994908_5697299548645359616_n

” እንዲህ ዓይነት አገረ ከማየት ፍርድ ቤታቹህ የወሰነውን ሞት ወስኑብኝ ፣ ከ1983  እስከ 1985 አገልⷛችኋለሁ እሱን ውለታ አድርጉና   ፍርድ ቤታችሁ የወሰብኝን የሞት ውሳኔ ተግባራዊ አድርጉ። እንደ ለገሰ አስፋው ፍቱኝ ብዬ አልለምናችሁም። ሰው እየሳቀ እንደሚሞት ላሳያችሁ “

” ይህንን ስሜታችሁን  እንዴት አድርጌ ልገለጸው፣ ይህን አልተበኩም ነበር፣ አይገባኝም… እድሜ ለቴክኖሎጂ ብዙ የምንነጋገረው አለ ” 

 

የኢህአዴግ ንብረት የሆነው ፋና  አእንዳለው በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ሀገራዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ወንጀሎች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ  በአዋጅ ቁጥር 943//08 አንቀፅ 6 ንዑስ ቁጥር 3/ሀ/ መሰረት ክሱ እንዲነሳ መወሰኑንን ይፋ አድርገዋል። ፋና ይህንን ከማለቱ ውጪ ክሱ ሊነሳ የቻለበትን ምክንያት አልጠቀሰም። ስለ ዓላማውም ያለው ነገር የለም። ነገር ግን አዳዲስ ” ከዛስ ” የሚያሰኙ ጉዳዮች እየተሰሙ ነው።

ዶክተር አብይ በቅርቡ ስም ባይጠሩም  ሚዲያ እንዳይተላለፍ ማገድ ብልጠት እንዳልሆነ፣ ይልቁኑም ቻናሎችን በማብዛት ሰዎች የአንድ ሚዲያ ደንበኛ እንዳይሆኑ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ መናገራቸው አይዘነጋም። ኢሳትና ኦ ኤም ኤን በቀጥታ አገር ቤት እየተላለፉ መሆኑ የሚታወቅ ነው። እናም ሚዲያዎቹ አገር ቤት እየተላለፉ ” አሸባሪ ናቸው” ብሎ ፋይላቸውን ከፍቶ ማስቀመጡ አግባብ እንዳልሆነም ሲጠቆም ነበር። በድርጅት ደረጃም ኢህአዴግ በስም ባይጠራም በውጭና በአገር ውስጥ ካሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የመነጋገር እቅድ እንዳለውም ማስታወቁ አይዘነጋም።

ዶክተር ብርሃኑ ነጋም ባልተለመደ ሁኔታ በሰሞኑ ንግግራቸው ” እኛ ለውጥ ካላመጣን አንልም” በሚል ኢህአዴግ  ውስጥ ሆነው የሚፈለገውን ለውጥ የሚያመጡ ካሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። አዲስ ባይሆንም አክለውም ስልጣን ፈላጊ እንዳልሆኑ አጠንክረው ሲገልጹ ተሰምተዋል። ከኢህአዴግ ጋር የድርድር ጥያቄ እንደቀረበላቸው ተጠይቀው ” አዲስ ነገር ሲኖር እነግራችኋለሁ” የሚል መልስ በመመለስ ተሰብሳቢውን አስፈገገው ነበር።

በቅርቡ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር የመሰረተውን ጥምረት ወደ ጎን በመተው ወደ አገር ቤት የገባው ኦዲኤፍ የተሰኘው የሌንጮ ለታ ግንባር ሌሎችም የእነሱን አርአያ እንዲከተሉ ፍላጎት እንዳለውና በዚሁ ረገድ እንደሚሰራ አስታውቋል። ጥሪም አድርጓል።

ይህ ሁሉ ከሆነ በሁዋላ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የስፖርት ዝግጅት ላይ ተጋባዥ እንዲሆኑ መጠየቁ ተሰማ። ዜናው እጅግ አነጋጋሪ በሆንበት በአሁኑ ወቅት ቀደም ሲል አጸባሪ የተባሉት ሚዲያዎችና ፖለቲከኞች ነጻ መባላቸው ታወጀ። 

ቀድሞውንም ሚዲያዎቹን በሽብርተኛነት መፈረጅ አግባብ ባይሆንም ዛሬ ክሱ እንዲነሳ የተወሰነበት ምክንያት ግልጽ አልተቀመተም፣ በየቀኑ አዳዲስ ጉዳዮችን እያሳየ፣ ነገር ግን በዋና መሰረታዊ የፖሊሲ ለውጦች ላይ የተኛው ኢህአዴግ አቶ አንዳርጋቸውን ጨምሮ አምስት መቶ አሃምሳ እስረኞችን በለቀቀበት ቀን ያሰማው ዜና አሁንም ” ከዛስ” የሚሰኝ ጥያቄዎችን አስከትሏል። አንዳንድ አስተያየቶችን ማከል እጅግ መፍጠን ባይሆንም አንዳንድ የተቃዋሚ ሃይሎች እየተደራደሩ መሆኑ ግን እርጥ ነው።

ዛሬ ከሞት መንጋጋ ነጻ የወጣው አንዳርጋቸው ” እንዲህ ዓይነት አገረ ከማየት ፍርድ ቤታቹህ የወሰነውን ሞት ወስኑብኝ ፣ ከ1983  እስከ 1985 አገልⷛችኋለሁ እሱን ውለታ አድርጉና   ፍርድ ቤታችሁ የወሰብኝን የሞት ውሳኔ ተግባራዊ አድርጉ። እንደ ለገሰ አስፋው ፍቱኝ ብዬ አልለምናችሁም። ሰው እየሳቀ እንደሚሞት ላሳያችሁ ” ሲል የተናገረው ንግግር እንባ ያራጨ ሆኗል። አንዳርጋቸው ” ይህንን ስሜታችሁን  እንዴት አድርጌ ልገለጸው፣ ይህን አልተበኩም ነበር፣ አይገባኝም… እድሜ ለቴክኖሎጂ ብዙ የምንነጋገረው አለ ” 

ከውስጥ በሚነድ የወገን ፍቅር አንድበቱን ከአራት ዓመት በሁዋላ ያሰማው አንዳርጋቸው እጅግ የከበረ አቀባበል ተደርጎለታል። ከቤተሰቦቹ ቤት ከወዳጆቹና ከደጋፊዎቹ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቷል። አንጋፋው አባቱ፣እናቱና መላው ቤተሰቦቹ እንዲሁም በቀናነት ላዘናችሁና ይህንን ቀን ስትናፍቁ ለነበራችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *