የትግራይ ተወላጆች ማህበር በሰሜን አሜሪካ ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ ጥሪ መደረጉ አገባብ አይደለም ሲል ተቃውሞውን ገልጾ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ደብዳቤ ላከ።

ኢሳት የትግራይን ሕዝብ ከሌሎች እንዲነጠሉ ማድረጉንም ደብዳቤው አመልክቷል። ማህበሩ በሌሎች የአገሪቱ ዜጎች ላይ ኢህአዴግ ያደረሰውንና የሚያደርሰውን ግፍ የማይቃወም፣ ለህወሃትና ለህወሃት የበላይነት ብቻ የሚሰራ እንደሆነ  በተደጋጋሚ ይገለጻል።

ኢሳት ላይ ክስ መመስረቱን የጠቆመው መግለጫ ኢሳት ይቅርታ ሳይጠይቅ የትግራይ ህዝብ ላይ የፕሮፓ ጋንዳ ዘመቻ እያካሄደ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ ጥሪ መደረጉ ቅር ያሰኛል ብሏል። ክስ መስርቶ እየተከታተለ መሆኑንን ጠቁሟል። ከትግል ጊዜ ጀመሮ ” ውለታ ሰርተናል” ሲል የገለጸው ደብዳቤ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን እንዲያጤኑት ይጠይቃል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ዳያስፖራው ካደረገው ድጋፍ ሁሉ ለኢሳት ያደረገው ውጤታማ እንደሆነ የሚገለጹ ወገኖች፣ ሚዲያው ከሌሎች ጋር ተዳምሮ በአገሪቱ አሁን ያለው ለውጥ እንዲመጣ የሰራው ስራ እጅግ ዋጋ ያለው እንደሆነ አብዛኞች ያምናሉ። ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀው ከዓመት በፊት አስተያየት የሰጡ የኢህአዴግ ሰው ” ኢሳት ጋሬጣ ሆኖብናል” ማለታቸው ይታወሳል። ይህንን መግለጫ ተከትሎ ከኢሳት በኩል ይህ እስከታተመ ድረስ የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ እንዲህ ያሉ አስተያየቶች ለጥንካሬ የሚጠቅሙና የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን የሚያመላክቱ መሆናቸውን ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወሳል። ወደፊት በተለይ በዚህ ደብዳቤ ላይ የሚሰጥ መልስ ካለ እናትማለን። ማህበሩ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት በዝግጅት ላይ ሰላለው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ያለው ነገር የለም።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ሙሉ ድብዳቤውን እዚህ ላይ ያንብቡ። Open-letter-to-PM-Abiy-06.01.2018

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *