በጋምቤላ ተካሂዶ በነበረው 10ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል 2000 ሰዎች ለተመገቡት ምግብ በሚል 12,000,000 ብር  ወ/ሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ መከፈሉን የሚያረጋግጥ ሰነድ ይፋ ሆነ። የሰነዱን ይፋ መሆን ተከትሎ ወይዘሮዋም ሆኑ ክልሉ ያሉት ነገር የለም።

ሰነዱን ይፋ ያደረጉት አካላት እንዳሰሉት ከሆነ ክፍያው በአንድ ሰው ስድስት ሺህ ብር ነው። ሰነስዱን በመቀባበል በማህበራዊ ገጾች ያንሸራሸሩ እንዳሉት ክፍያው የተጋገነና ሊታመን የማይችል ነው። ክፍያው ለካቢኔ ቀርቦ የጸደቀ መሆኑንን ሰነዱ ቀንና ቁጥር ገልጾ አመልክቷል። ደብዳቤውን ከግርጌ ያንብቡ።

ወይዘሮ ትልቅ ሰው ባህር ዳር የሚገኘው የግራንድ ሪዞርት ባለንብረት ሲሆኑ አፍቃሪ ኢህአዴግ እንደሆኑ ይነገራል። በሆቴላቸውም ላይ ያልታወቁ ሰዎች ቦንብ ጥለውበት እንደነበር ይታወሳል።

ክልሉ ለዚሁ በዓል የሚውል ሶስት መቶ ስልሳ አራት ሚሊዮን ብር ከፌደራል መበደሩን የመንግስት ሚዲያዎች ዘገበው ነበር። ይህንኑ እዳውንም ከበጀቱ ላይ እያወራረደ እንደሚገኝ ብተለያዩ ሚዲያዎች ተመልክቷል።


Share and Enjoy !

Shares
Related stories   The National Movement of Amhara(NaMA) Denounces International Violations of the Sovereignty of Ethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *