የትግራይ ብሔርተኞች ዳግማዊ ምኒልክን ባልዋሉበት እያነሱ ካላብጠለጠሉ ፖለቲካ የሰሩ ስለማይመስላቸው በነጋ በመሸ ክብራቸው የሚነካ ነገር ያገኙ በመሰላቸው ቁጥር አጀንዳ ያደርጓቸዋል። ከሰሞኑ ባድመ የምትባል አጀንዳ አግኝተው በሊቀመንበራቸው በመለስ ዜናዊ ፊርማ ለሻዕብያ በተሰጠችው ባድመ አመካኝተው ዳግማዊ ምኒልክን እያወገዙ ናቸው። «ምኒልክ የሸጣት ባድመ ትመለስልን» በማለት እያላዘኑ ይገኛሉ።

ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እንዲህ በፎቶው በሚታየው መልኩ ህይወታቸውን ሰውተውና አሸንፈው የያዙትን ባድመ ፈርሞ ለኤርትራ ፈርሞ እና አሳልፎ የሰጠው ህወሃት እና የህወሃት መሪ ባንዳው መለስ ዜናዊ ነው፡፡

በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን መንግሥት እንኳን መሃል ያለው ባድመ ይቅርና ዛሬ ኤርትራ የሚባለው አገር ራሱ ሶስት አራተኛው ክፍል [የውጫሌውንም ሆነ የአዲስ አበባውን ስምምነት ያነቧል] የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መሬት ነበር። አንድ አራተኛውን የኤርትራ ክፍል ለጥሊያን የሰጡት ዐፄ ዮሐንስ ናቸው። ዳግማዊ ምኒልክ ግን ፈርዶባቸው ጥሊያን ራሱ ያፈረሳቸውን አምስት ውሎች መለስ ዜናዊ ከመቃብር ቆፍሮ በማውጣት እንድትፈጠር ባደረጋት አገር ኤርትራ ሲወቀሱ ይውላሉ።

ኢትዮጵያ መንግሥት በነበራት ወቅት ዐፄ ዮሐንስ ለጥሊያን የሰጡት የኤርትራ መሬት ጭምሮ በታላቁ አርበኛ በአክሊሉ ሃብተ ወልድ አስደናቂ ተጋድሎ ወደ እናት አገሩ ተመልሶ ነበር። የኢትዮጵያ ጀግኖች [እነ አክሊሉ፣ አስፍሃ ወልደ ሚካኤል፣ መላከ ሰላም ዲሜጥሮስ፣ ወዘተ] «ኢትዮጵያ ወይንም ሞት!» በሚል አስደናቂ ተጋድሎ ወደ እናት አገሯ የተመለሰችዋን ኤርትራ ብቻ ሳይሆን ባድመንም ጭምር ለሻዕብያ ያስረከበው የፋሽስት ሹምባሹ ልጅ መለስ ዜናዊ ነው። አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዲሉ የትግራይ ብሔርተኞች ግን «መሬታችን» የሚሉትን የባድመን ለሻዕብያ መሰጠት ለመቃወም ሰልፍ ወጥተው ዳግማዊ ምኒልክንና አብይ አሕመድን ያወግዛሉ።

ሌላው አሳዛኙ ነገር አንዳንድ የመሐል አገር ምሁራን ጭምር ባድመ የኢትዮጵያ እንጂ የኤርትራ አይደለም ሲሉ መከራከራቸው ነው። እነዚህን «ምሑራን» ኤርትራ የማን ነበር ብሎ የሚጠይቃቸው ቢኖር መልስ ይኖራቸው ይሆን? የአንድ አገር ክፍል የነበረ ግዛት ተቆርሶ ሌላ አገር ተፈጥሮ ባለበት ሁኔታ፤ የመለስ ዜናዊን የአልጀርስ ስምምነት ካልጠቀሱ በስተቀር፣ በምን መስፈርትና በየትኛው ታሪካዊ ማስረጃ ነው ባድመ የኢትዮጵያ እንጂ የኤርትራ አይደለም የሚል የምር ሙግት የሚከፍቱት? እስቲ እነዚህን ሰዎች በሠራዬ፣ አካለ ጉዛይና የደብረ ቢዘን ገዳም ከነ ጉልቱ ከነ ርስቱ ከባድመ በምን ይለያል በሉልኝ?

ሌላው የትግራይ ብሔርተኞች አስቂኙ ቀልድ የባድመን ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሊዓላዊነት ጋር ለማገናኘት የሞከሩበት ጨዋታ ነው። እነዚህ ሰዎች ድርጅታቸው ፋሽስት ወያኔ የጎንደርን መሬት ለሱዳን አሳልፎ ሲሰጥ በምንቃወምበት ወቅት ከኛ ጋር መሰለፋቸው ጽድቅ ሆኖ «ትግሬ ስለምትጠሉ ነው» እያሉ እኛን ይቃወሙን ነበር። ቋራ «የአማራ መሬት» ስለሆነ ድርጅታቸው የትግራዩ ነጻ አውጭ ቡድን ለሱዳን ሲሰጥ ጉዳያቸው ያልሆነውና ድርጊቱን ባወገዝን እኛን ሲቃወሙን እንዳልነበሩ እነ መለስ ዜናዊ ለሻዕብያ የሰጡት ባድመ ግን የትግራይ መሬት ስለሆነ የሉዓላዊነትና የአገር ጉዳይ አድርገን እንድናስብላቸው ይፈልጋሉ። አንዳንዴ ብልጣብልጥነትም በገደምዳሜ ነው። «እኛም አውቀናል፣ ጕድጓድ ምሰናል» የሚለውን «የአይጦች አባባል» ሲሰማ ላደገ ትውልድ በእንዲህ ሰሞኑን እየሰማነት ባለነው አይነቱ ቀሽም ጨዋታ ለማሞኘት መኮከር የራስን ቂልነት ማወጅ ብቻ ነው።

ባጭሩ የባድመ ጉዳይ የመለስ ዜናዊና ለወንጀል የተቋቋመው ድርጅት የፋሽስት ወያኔ ጉዳይ እንጂ የዳግማዊ ምኒልክና የአብይ አሕመድ ጉዳይ አይደለም። መለስ ዜናዊ ፈርሞ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጸድቆ ለኤርትራ በሰጣት ባድመ ዳግማዊ ምኒልክና አብይ አሕመድ ተጠያቂነት የሚሆኑበት አንዳች አመክንዮ ሊኖር አይችልም። መለስ ዜናዊ ባድመን ለኤርትራ ፈርሞ መስጠቱን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባድመን የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት መሆኗን እውቅና በሰጠበት ሁኔታ ዳግማዊ ምኒልክና አብይ አሕመድ ስለ ባድመ ጉዳይ ሊወቀሱ አይችልም። በሌላ አነጋገር በባድሜ ብቸኛ ተወቃሽ የኤርትራ መሬት መሆኗን ኢትዮጵያን በመወከል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጸድቆ ለኤርትራ የሰጠው መለስ ዜናዊና ድርጅቱ ወያኔ ብቻ ነው።

መለስ ዜናዊ ከኢሳያስ ጋር በአልጀርስ ተፈራርሞ ባድሜን የሰጠበትን መረጃ ሙሉውን ከዚህ ላይ ያንብቡ

Agreement between the Government of the State of Eritrea and the Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia

Eritrea-Ethiopia Boundary Commission Decision Regarding Delimitation of the Border (pdf)

Eritrea-Ethiopia Boundary Commission Decision Regarding Delimitation of the Border
Agreement between the Government of the State of Eritrea and the Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (pdf)

የአልጄርስ ስምምነት ከመፈረሙ 4 ቀናት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል!(የሰነድ ማስረጃ)

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጄርስ ስምምነትን ለመቀበል መወሰኑን ተከትሎ ጉዳዩ አነጋጋሪ ሆኗል። በተለይ በአንዳንድ የትግራይ አከባቢዎች የአልጄርስ ስምምነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል። ለዚህ ደግሞ በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ፤ በተለይ ባድመ ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች መስዕዋት ሆነዋል፣ በአከባቢው የሚኖሩ የማህብረሰቦችን ለሁለት ይከፍላል፣ እንዲሁም የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገሪቱ መሬትና ሉዓላዊነት ላይ በተናጠል የመወሰን ስልጣን የለውም እና ስምምነቱን ለመቀበል ሕዝበ ውሳኔ መደረግ አለበት የሚሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ። ከዚህ አንፃር “የኢህአዴግ መንግስት የአልጄርስ ስምምነትን ተቀብሎ ተግባራዊ ሊያደርግ አይገባም” የሚል መከራከሪያ ያቀርባሉ።

ሆኖም ግን፣ “የጉድ ሀገር ጉድ እያደር ይወጣል” እንደሚባለው፣ ከአልጄርስ ስምምነት ጋር በተያያዘ ሌላ አዲስ ጉድ ወጥቷል። ይኸውም የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአልጄርስ ስምምነትን ተቀብሎ አፅድቆታል። ህዳር 29/1993 ዓ.ም በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ 7ኛ ዓመት ቁጥር 7 ታትሞ በወጣው አዋጅ ቁጥር 225/1993 መሰረት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና በኤርትራ መንግስት መካከል የተደረገው የሰላም ስምምነት በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል።

Proclamation No 225/2000 Peace Agreement between The Government of The Federal Democratic Republic of Ethiopia and The Government of The State of Eritrea

Proclamation No 225/2000 Peace Agreement between The Government of The Federal Democratic Republic of Ethiopia and The Government of The State of Eritrea, pdf

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና በኤርትራ መንግስት መካከል በአልጄሪያ ዋና ከተማ አልጄርስ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ለማፅደቅ የወጣው አዋጅ ቁጥር 225/1993 የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55 ንዕስ አንቀፅ 1 እና 12ን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሆነ በአዋጁ ተጠቅሷል። አንቀፅ 55 (1) የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕገ መንግስቱ መሰረት ለፌደራል መንግስት በተሰጠው የስልጣን ክልል ውስጥ ሕጎችን ያወጣል በማለት ይደነግጋል። አንቀፅ 55(12) ደግሞ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የህግ አስፈፃሚው አካል የሚዋዋላቸውን ዓለም-አቀፍ ስምምነቶች ያፀድቃል” ይላል።

የአልጄርስ ስምምነት በቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የኤርትራው ፕረዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፊርማ የፀደቀው ታህሳስ 03/1993 ዓ.ም (እ.አ.አ. 12th December, 2000) መሆኑን ከላይ ካለው የስምምነቱ ሰነድ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጂ፣ የአልጄርስ ስምምነትን በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቆ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የታወጀው ህዳር 29/1993 ዓ.ም (እ.አ.አ. 8th December, 2000) ነው። በመሆኑም የሰላም ስምምነቱ አልጄርስ ላይ ከመፈረሙ አራት (4) ቀናት በፊት የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፅድቆት ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል። የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 55(4) ምክር ቤቱ “የህግ አስፈፃሚው አካል የሚዋዋላቸውን ዓለም-አቀፍ ስምምነቶች ያፀድቃል” የሚል ቢሆንም የአልጄርስ ስምምነት ከመፈረሙ በፊት በምክር ቤቱ ፀድቆ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታውጇል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *