ይህን ወጣት ማድመጥ ያማል። እጅግ ነብስን ይፈታተናል። ይህንን ያህል የከፋና አረመኔያዊ ተግባር የሚፈጸመው በወገን፣ በአገር ውስጥ መሆኑ ሃዘኑን የከፋ ያደርገዋል። እንዲህ ያሉ ወንጀሎች ብዙ ናቸው። በዚህ ዓይነቱ ድርጊት የሚደሰቱ መኖራቸው ያሳፍራል። ያሳዝናል። መኖርንም ይፈታተናል።

እግር ቆርጦ ቁስል እየፈቱ በጉጠት ማምገልና መቆስቆስ … ፍጹም አውሬነት ነው። አንድ እግሩን እንዲያጣ የተደረገን ሰው መጸዳጃ ቤት ውስጥ መወርወር ምን ማለት ነው፤ ይህንን እየፈጸሙ እንቅልፍ የሚተኙ ወገኖች!! እድሜና የቀን ጉዳይ ይሆን እንጂ ገና ብዙ እንሰማለን። ይህንን ታሪክ ለህዝብ ይፋ ላደረጉ ሚዲያዎች በሙሉ ምስጋና ይገባል።

 

"ሞትን ተመኝቼ ነበር ነገር ግን አልሞትኩም…" ይላል አቶ ከፍያለው ተፈራ። በእስር ቤት እያለ ስለደረሰበት እንግልት ለቢቢሲ እንዲህ በማለት ነው የተናገረው።https://www.bbc.com/amharic/news-44518726

Публикувахте от BBC News Amharic в Понеделник, 18 юни 2018 г.

 
 


 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *