ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብይ አህመድ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያን መንግስት የእርቅና ድርድር ጥሪ ለሰጡት ምላሽ ምስጋና አቅርበዋል። በመልዕክታቸውም ኢትዮጵያ የኤርትራን የልዑካን ቡድንን በታላቅ አክብሮት ተቀብላ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢትዮጵያ ጥሪ ምላሻቸውን የሰጡት በየዓመቱ በሚከበረው የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በቀጥታ ቴሌቪዥን ስርጭት ባደረጉት ንግግር ነው። በጉዳይ ላይ የሚነጋገር ልዑክ ወደ አዲስ አበባ እንደሚልኩም ነው ይፋ ያደረጉት። በንግግራቸው ይህ ውሳኔ ለሁለቱ አገር ህዝቦች አዲስ እንዳልሆነም ጠቁመዋል።

በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉት ለውጦች ተገቢ ትኩረት የሚጠይቁ መሆናቸውንም አመልከተዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በሽግግር ላይ ትገኛለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ ቅድሚያ ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል። አሁን የቀረው ነገር ቢኖር ይህ ነው።

ለዚህም በዜና ከመከታተል እና ከመቀባበል በዘለለ ያለውን ሁኔታ በቀጥታ ማወቅ ስለሚያስፈልግ፤ እንዲሁም በቀጣይ ሊሰራበት ስለሚገባ የልዑክ ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደሚላክ አስታውቀዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የፕሬዚዳንት ኢሳያስን መልዕክት አስመልከቶ ምስጋና ያሰተላለፉት ወልቂጤ ችግር እየፈቱ ባሉበት ወቅት ነው።

እጅግ በስራ የተወጠሩትና በፍጹም ትጋት የአገሪቱን ችግር ለመፍታት እላይ ታች የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ” ቢሮ አይቀመጡም” ሲሉ ከጅምሩ የጠሏቸው ትችት ይሰነዝሩባቸዋል። ይሁን እንጂ በመሪ ጥማት የተቃጠሉ ዜጎች ለሳቸው ያላቸው ድጋፍ በቃላት የሚገለጽ አይደለም። ለሰላማቸው ጸሎት ከማድርግ ጀመሮ የፊታችን ቅዳሜ ” ከጎንህ ሆነን እንረዳሃለን” በሚል ድጋፋቸውን ለመስጠት የአዲስ አበባና አካባቢው ነዋሪዎች ከወዲሁ ቀጠሮ ይዘዋል። በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በሰልፉ ተገኝቶ ያለ ቀስቃሽ ለመሪዎ ክብር ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ፋና ይህንን ዘግቧል

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ገንቢ ውይይት የሚያደርግ ከፍተኛ ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ ልትልክ መሆኑን አስታወቀች።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በየዓመቱ በሚከበረው የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በቀጥታ ቴሌቪዥን ስርጭት ባደረጉት ንግግር፥ በድንበር ጉዳይ ላይ የሚነጋገር የሃገራቸውን ልዑክ ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ማሰባቸውን ተናግረዋል።

ሁለቱም ህዝቦች በጋራ ባደረጉት ትግል ነፃነታቸውን በማረጋገጥ ለሀገራቱ ብሎም ለአፍሪካ ቀንድ ወሳኝ የሆነ አድገት ለማምጣት በተነሱበት ወቅት ያጋጠመው ጦርነት ባለፉት ዓመታት ያስከተለው አደጋ ከባድ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አንስተዋል።

ይህም ጦርነት ባለፉት ዓመታት ኢኮኖሚን ወደኋላ እንዲያሽቆለቁል በማድረግም ሰዎች እንዲፈናቀሉም አደርጓል ነው ያሉት።

በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉት ለውጦች ተገቢ ትኩረት የሚፈልጉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በሽግግር ላይ ትገኛለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ አሁን ላይ የቀረው በሁለቱ ሀገራት መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ ቅድሚያ ተሰጥቶት ይሰራል ነው ያሉት።

ለዚህም በዜና ከመከታተል እና ከመቀባበል በዘለለ ያለውን ሁኔታ በቀጥታ ማወቅ ስለሚያስፈልግ፤ እንዲሁም በቀጣይ ሊሰራበት ስለሚገባ የልዑክ ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደሚላክ ነው የተናገሩት።

በተጨማሪም ዓለማዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ኤርትራ የምታዘጋጃቸው ፖሊሲዎች ከጎረቤት አገራት በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር አዛምደን የምናያቸው ይሆናልም ነው ያሉት።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ባካሄደው ስብሰባ የኢትዮ- ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በመገምገም፥ ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀብላ ለመተግበር መስማማቷን መግለጹ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃና በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር ጥሪ ማቅረቡም የሚታወስ ነው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *