1. ሰውን ጨለማ ቤት ማስቀመጥ፣ አካልን ማጉደል የእኛ የመንግስት የአሸባሪነት ድርጊት ነው።
2. ህገመንግሰቱ ጨለማ ቤት አስቀምጣችሁ ግረፉ፤ አሰቃዩ አይልም፡፡አሸባሪ እኛ ነን፡፡ ኢህአዴግ ይቅርታ ጠይቋል፤ ህዝቡም ይቅር ብሎናል፤ ህዝቡ እኛን ማሰር ነበረት፤በይቅርታ አልፎናል፡፡ 


3. ሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከወረዳ እስከ ፌዴራል ድረስ በነበሩ እስር ቤቶች ነበር። መንግስት በዚህ ስራ አሸባሪ ነበር።
4. ይህ ምክር ቤት አሸባሪ ድርጅት እንጂ ግለሰብን ብሎ አያውቅም። ጥላቻ ላይ ተመሰረተ የፖለቲካ አካሄድ ኪሳራ ነው። ዜጎችንም አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ እያስገባ ነው ።
5. በሽብር ጭምር ተከሰው ከማረሚያ ቤት የተፈቱ ሰዎች ኢህአዴግ ባስቀመጠው አቅጣጫ የተፈፀመ እንጂ ህግ መጣስ አይደለም፡፡
6. ሰው ሲፈታ አይናችን የሚቀላ በቀለኞች አንሁን፡፡ኢትዮጵያ በቂ ሀገር ናት፡፡
7. አማራ በኦሮሞ፤ትግራይ በአማራ ክልል በነጻ መንቀሳቀስ ካልቻለ ስለ አፍሪካ አንድነት ለማውራት አንችልም፡፡
8. ድንበር እና ወሰን ማምታታት አለ፡፡ አማራ እና ኦሮም፤አማራ እና ትግራይ ድንበር የላቸውም፡፡ወሰን ነው፡፡ድንበራችን ከኬኒያ ጋር ነው፡፡፡ 
9. አንድ አማራ ነቀምት፡አንድ ኦሮሞ ጅግጅጋ ላይ መኖር ካልቻለ ከባድ ነው፡፡የትም ቦታ የመኖር መብት አለን፡፡
10. የፊዴራሊዝም ስርዓቱ ትላልቅ ችግርን እንጂ ትንንሽ ችግሮችን ማቆም አይችልም፡፡በአመራርነት ይስተካከላል፡፡
11. የአፍሪካ መሪዎች ያለቪዛ አፍሪካውያን በነጻ እንዲንቀሳቀሱ ሊያደርጉ ነው፡፡ አማራ በኦሮሞ፤ትግራይ በአማራ ክልል በነጻ መንቀሳቀስ ካልቻለ ስለ አፍሪካ አንድነት ለማውራት አንችልም፡፡አንድነትን እንሰበክ፡፡
12. የአማራ እና የትግራይን፤የኦሮሞ እና የደቡብ ወሰን ጉዳዮችን በዘላቂነት እንመልሳለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለተከበረው ምክር ቤት ገልጸዋል፡፡
13. “የድበቃ ፖለቲካ ካሁን በኋላ በቃ” 
14. በምስራቅ አፍሪካ ያለው ድንበር በቅኝ ገዥዎች የተሰራ በመሆኑ “አርቲፊሻል” ነው፡፡በቅኝ ገዥዎች ፍላጎት የተሰራ ነው፡፡ የኬኒያ፣ ኦሮሞ እና የቦረና ኦሮሞ በሁለት ሀገር ይኖራሉ፡፡በትግራይም ተመሳሳይ ነው፡፡ተመሳሳይ ባህል ያላቸው ሀገራት ሁለት ሀገር ሆነዋል፡፡
15. ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ወደ አንድ ሀገርነት ልንመጣ ነው፡፡ትልቅ ሀገር ለመሆን በጋራ እንደመራለን፡፡ ትንንሽ ደሃ ሀገር መሆን የለበትም፡፡ 
16. የአልጀርስ ስምምነት በፓርላማው ቀድሞ የጸደቀ ነው፡፡ለአፍሪካ መሪዎችም ደርሷል፡፡ ዓለምም ያውቀዋል፡፡መሆን የማይገባው ጦርነት አድርገናል፡፡ አስከፊ ጦርነት ነው፡፡ጦርነት እያስታመምን አንኖርም፡፡
17. ደቡብ እና ሰሜን ኮርያ እንድ እየሆኑ ነው፡፡ ኤርትራ እና ኢትዮጵያም መቀራረብ አለባቸው፡፡ ለብሄራዊ ጥቅም እንተጋለን፡፡የኤርትራ ህዝብ ወንድማችን ነው፡፡ ህዝብ ጠይቋል፡፡ ስለዚህ የተመለሰው የህዝብ ጥያቄ ነው፡፡
18. የድብቅ ፖለቲካ ካሁን በኋላ በቃ፡፡የሥራ አስፈጻሚው ውሳኔ ለህዝባችን ቶሎ መስማት አለበት፡፡ ከህዝባችን የሚደበቅ ነገር የለም፡፡
19. የወንድሜ ልጅ ባድሜ ላይ ሙቷል፡፡፡ ዋጋ ተከፍሏል፡፡ ባረንቱ ላይም ሙተናል፡፡የመሞት ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ ሃብት አፍሰናል፡፤ አሁን ወደ ሰላም እንመጣለን፡፡
20. ህወሀትን ከትግራይ ህዝብ ለዩት፡፡የትግራይ ህዝብ ማለት ህወሀት ማለት አይደለም፤ ጥላቻ እና ቂም ይብቃ፡፡የትግራይ ህዝብ ብዙ የመልካም አስተዳድር ችግር አለበት፡፡ውሃ መጠጣት እንኳን የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
21. የእርስ በርስ ጥቃት ዘር ወደመተላለቅ የሚመራ አጉል የፖለቲካ አካሂድ እና የጥቂቶች አላማ ነው። ይሄ እንዳሆን ግን ህዝባችን ልበ ሰፊ ነው 
22. ሽብር ስልጣን ላይ ለመቆየት ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊት ላይ መሳተፍና ስልጣን ለመያዝ ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊት ማድረግን ያካትታል።
23. ግንቦት 7 ኦነግ፣ ኦብነግ ውጊያ ፋሽን ያለፈበት ጉዳይ ነው አቁማችሁ ኑ በሀሳብ ብልጫ ውሰዱ፡፡
24. ለኢትዮጵያ እኛ ብቻ አይደለንም የምንቆረቆር፤ ሁሉም ይቆረቆራል፡፡
25. ከዘረኝነት ነጻ የሆነ ፖለቲካና ሃይማኖት ሊኖር ይገባል።
26. ተዘግተው የነበሩ ድረ-ገጾች ተከፍተዋል፡፡እንዳይጽፉ ተከልክለው የነበሩ አምደኞች በነጻነት እንዲጽፉ ለማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
27. ሚዲያዎች የህዝብ ድምጽ እንዲሆኑ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡በቀጣይ የህዝብ ድምጽ እንዲሆኑም እንሰራለን፡፡
28. የኢኮኖሚ አሻጥርን ለማስቀረት ኢኮኖሚው ላይ ይሰራል፡፡
29. የኢትዮ-ኤርትራ ውሳኔ ህዝቡን መሰረት በማድረግ የተወሰነ ነው፡፡
30. በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ለ18 ዓመት ዓመታት ነግሶ የቆየውን ሞት አልባ ጦርነት ለማቆም የመፍትሄ እርምጃ እየተወሰደ ነው፡፡የሰላም ጥሪም ለኤርትራ ቀርቧል፡፡ ለሶስት ዓመት ሰፍኖ የቆየው አለመረጋጋት መሻሻል አሳይቷል፡፡አንዳንድ ቡድኖች ለውጡን አልደገፉም፡፡ይሁን እንጂ መንግስት ለሀገር አንድነት የሚሰራ ይሆናል፡፡
31. የኢኮኖሚ ማሻሻያው ያስፈለገው የውጭ ብድር ለመክፈል፤ የሚዘገዩ ፕሮጀክቶችን ቶሎ ለመጨረስ፤የስራ እድል ለመፍጠር፡የገቢ ስራዓትን ለማዘመን አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡ 
32. በትንሽ ብር የጀመርነው ፕሮጀክት ከእጥፍ በላይ እየሆነ ነው፡፡ለዚህም ነው የግሉን ዘርፍ ማሳተፍ የተፈለገው፡ የመንግስት ሞኖፖሊ ሊቀር ይገባል፡፡ኔትወርክም ጥራት የለውም፡፡
33. 12 ሚሊየን ህዝብ ያላት ሶማሊያ አራት የቴሌኮም ኩባንያ ሲኖራት እኛ ግን 100 ሚሊየን ህዝብ ይዘን ያለን ኩባንያ 1 ብቻ ነው።
34. መርከቦቻችን ቁመው ነው የሚውሉት፡፡ ጎረቤት ሀገራት ይበልጡናል፡፡ የሎጂክስትስ ስራችን ኋላቀር ነው፡፡ከዓለም 160ኛ ነን፤ ይህ ካልተስተካከለ ፈጣን ኢኮኖሚን መሸከም አንችልም፡፡ 
35. መጠኑ ይስፋም ይነስ እንጂ ሌብነት ከጫፍ እስከ ጫፍ አለ። በሃይማኖት ተቋማት በትምህርት ተቋማት በመንግስት ተቋማት አለ። ማሰር የማይችል መንግስት አድርጎ የሚያስበን ሰው አለ፤ ግን ማሰር ከአባቶቻችን ጀምሮ ነበር፤ አዲስ ነገር አይደለም፤ እጃቸውን መሰብሰብ ያለባቸው ግን አሉ።
36. ሃብት የዘረፉ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፡፡ ሌቦች አሉ፡፡ሌቦች እንዳልታወቀባቸው ነገር እየሸረቡ ነው፡፡ እርምጃ እንወስዳለን፡፡ስርዓቱ እኩል አይን የለውም፡፡ አጣርተን እናስራለን እንጂ አስረን አናጣራም፡፡ 
37. የዲሞክራሲ ምንጩ ህዝብ ነው ጸረ ድሞክራሲ ከሆነ ግን መንግስት ህግን ማስከበር ግድ ይላል። ህግ አሰከባሪዎችን ጠላት አድርጎ ማሰብ ተገቢ አይደለም። 
38. መከላከያንም ማንም ዜጋ አይቶ መገምገም አለበት ፤መከላከያ በትንሽ ገንዘብ ህይወታቸውን የሚሰጡበት ቦታ እንጂ የሚፈራ አጥር አይደለም።
39. ጃንሆይን አፍኖ መግደል መልካም እንዳልሆነ ከመንግስቱ መማር አለብን፡፡ቤተመንግስት የኮሌኔል መንግስቱ መግረፊያ አለ፡፡ይሕ የጥላቻ ታሪክ ያብቃ፡፡
40. በውስጥ ያለ ፍቅር ለአገር ብቻ ሳይሆን በዓለም እንደመጣለን፡፡ወደ ደቡብ ዛሬ ሂደን ነገ እናወያያለን፡፡ኦሮሞ ከሶማሊያ ፣አማራ ከትግራይ ጋርም አለመግባባት አለ፡፡እንፈታለን፡፡ እንደመር፡፡እንወያያለን፡፡
41. በገፍ የታሰሩት እየተለቀቁ ነው፡፡የቀረ ካለ እንፈታለን፡፡፡እስረኛ ባንድ ጀምበር አይለቀቅም፡፡ ህግ እና ስርዓት አለው፡፡በዚህ መሰረት ይከወናል፡፡
42. ገለልተኛ የፍትህ ተቋም እንገነባለን፡፡ የተሟላ ዲሞክራሲ የለም፡፡የተከማቸ ችግር ስላለ ቀስ እያልን እንፈታለን፡፡ የእስር ፍቺን በደም ማየት ተገቢ አይደለም፡፡ህግ ይሻሻላል፡፡
43. ሙስና አምስተኛው መንግስት ነው የሚባለው የተደራጀ መዋቅራዊ ቡድን በመሆኑ ነው፡፡ መዋቅራዊ በመሆኑ በመገናኛ ብዙኃን ጭምር በመታገዝ ልንታገለው ይገባል፡፡
44. የመንግስት ባለስልጣን በስራ ላይ እያለ ነጋዴ፣ ሀብታም መሆን አይችልም፤ ነጋዴ፣ ሀብታም መሆን ካማረው ቢሮውን ለቆ መሄድ አለበት፡፡
45. “እኛ ተቸግረን ለልጆቻችን ችግር፣ ጥላቻ፣ ጸብና ግጭት ማውረስ የለብንም፤ እርቅና ሰላም ነው የሚያስፈልገን፣ኢትዮጵያውያን ለሰላም የሚከፈል ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆን አለባቸው”
46. እንደ ቴሌ፡ አየር መንገድ ፣የኃይል አቅርቦት ዘርፉ እና አንዳንድ የመንግስት ተቋማት የተወሰነው ድርሻቸው የሚሸጠው እዳቸውን ጭምር መክፈል ስላቃታቸው ነው፡፡ ለግል ዘርፉ ክፍት ማድረጋችን
• በውድድር ላይ የተመሰረተ ጥራት ያለው አገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል፡፡
• ሽግግሩ ጥንቃቄ የሚፈልግ ስለሆነ እስከ ሁለት ዓመት ሊወስድ ይችላል፡፡
• የሀብት ብክነትን ያስቀራል፡፡
47. በ2010 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ገቢ በ 7.7 ቢሊየን ወርዷል፡፡ የውጭ ምንዛሬውም ቀንሷል፡፡ በመሆኑም ጥቁር (የጓዳ) ገበያውን እንቆጣጠራለን፡፡የሀገሪቱ የውጭ እዳ ከ 24 ቢሊየን ዶላር በላይ ደርሷል፡፡
48. ከእዳው ውስጥ 56 ነጥብ 1 በመቶው የመንግስት ሲሆን 43 ነጥብ 9 በመቶው እዳ ደግሞ በመንግስት የልማት ድርጅቶች የተመዘገበ ነው።
49. የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት በአንድ አሃዝ ላይ ቢሆንም(ከ11 በመቶ ቀርዷል ማለት ነው) ተሟሙቆ ቀጥሏል፤ 
50. የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ 863 የአሜሪካ ዶላር ደርሷል።

Nigussu Tilahun በ Mih Amhara

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *