ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን ያልተጠበቀ የለውጥ አየር በመንፈስ ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ ህዝብም  የገዢው አካል እየወሰደ ያለውን አንዳንድ እርምጃዎችና ውሳኔዎች ባብዛኛው በበጎ ዓይን ተመልክቷቸዋል። የተጀመረው ለውጥ ዳር እንዲደርስና ህዝባችን ከጨቋኙ ሥርዓት በአስተማማኝ መልክ እንዲላቀቅ፤  ህግንና የህዝብ መብትን የሚያከብር፤ የህዝብን አንድነትን የሚያስጠብቅና፤ ከፋፋይ ፖለቲካን የሚያስወግድ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ተቋቁሞ ለማየት በጉጉትና በተስፋ ይጠባበቃል።

ዶክተር ዓቢይ አህመድየኢትዮጵያ መሪ ሆነው ከተመረጡ ጀምሮ  የሚያደርጓቸው ንግግሮችና የሚወስዷቸው ውሳኔዎች ተስፋ ሰጪነታቸው አሌ የሚባል አይደለም።

Consortium of Ethiopian Civic Society Organizations (TIBIBIR).

ይሁንናም በአገራችን ያንዣበበውን የለውጥ አየር ለመመረዝ፤ የህዝቡን ተስፋ ለማጨለምና ያለፈውን የ27 ዓመታት የጭቆና ዘመን ለማስቀጠል በግልፅና በስውር ሌት ተቀን የሚኳትኑ መሠሪ ሀይሎች እየትንቀሳቀሱ መሆናቸውን የለውጥ ፈላጊ ሀይሎችና ሰፊው ህዝብ መገንዘብ ይኖርባቸዋል። በቅርቡ በአዋሳ፤በወላይታ ሶዶ፤ በኢትዮጵያ ሱማሌ፤በወልቂጤ፤ በቤኒ-ሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ወያኔዎች  የፈጠሯቸው የርስ-በርስ ግጭቶች ለውጡን ለማደናቀፍ የታቀደ ሸር እንደሆነ ጥርጥር ሊኖር አይችልም። ነገር ግን የወያኔን መሠሪ ተንኮሎች መገንዘብ ብቻውን በቂ አይደለም። የለውጥ አምካኝ ሃይሎችን ሴራ ለማክሸፍ ለውጥ- ፈላጊ ሀይሎች ውሃ ቀጠነ በማለት መለያየታቸውን አቁመው የጋራ አጀንዳ መንደፍና አንድ ሠፊ የህብረት እንቅስቃሴ ማደራጀት ይኖርባቸዋል።

ይህን አስመልክቶ አሁን ያለንበት ወቅት ከመቸውም ጊዜ በላይ ይህን መሳይ አስቸኳይ መፍትሄ ማፈላለግን የግድ ይላል። በኛ አስተያዬት መፍትሄው ትብብር መፍጠር ወይም የተፈጠሩትን ማጠናከር ብቻ ነው። ይህ አካሄድ ቢያንስ ሦስት ፋይዳዎች አሉት። በመጀመሪያ ያለውን ጨቋኝ ሥራአት ዕድሜ ለማራዘም የሚንቀሳቀሱትን ሃይሎች ከህዝቡ ለመነጠል፤ብቻቸውን ለማስቀረትና የሴራ ዕቅዳቸውን ለማክሸፍ እጅግ አስፈላጊ እርምጃ ነው። የሥራአቱን አቀንቃኞች በዚህ መልክ ማዳከም ከተቻለ ዶክተር ዓቢይና አጋሮቻቸው የጀመሩት የለውጥ ሂደት እንዳይደናቀፍ ብሎም እንዳይቀለበስ ለማድረግ ይቻላል።  አሁን ባለው የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ከዶክተር ዓቢይና ከለውጥ አጀንዳቸው ጎን መወገን አማራጭ የለውም። እርሳቸው እየሞከሩ ያለውን ለውጥ አለመደገፍ ወይም ከዳር ቆሞ መመልከት ለወያኔ በትር እንደማቀበል ሊቆጠር ይገባል።

ሁለተኛ፤ የለውጥ ፈላጊ ሀይሎች ትብብር ሠፊው ህዝብ ባሁኑ ጊዜ ያገኘው ተስፋ እንዳይጨልምና ባለፈው ዓመት ያሳየው የትግል ስሜት እንዳይዳከም ይረዳል። በ97 ሀገራዊ ምርጫ ጊዜ የለውጥ ሃይሎች ቅንጀትንና ህብረትን ሲመሠርቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል ለዴክራሲያዊ ለውጥ ተነሳስቶና ተባብሮ እንደነበር ማስታወስ ለትብብር አስፈላጊነት ማስረጃ ከመሆኑም በላይ ዓራአያነቱ ግልፅ ነው።

በመጨረሻም፤  ሥራአቱን ለማሻሻልም ሆነ ለመቀየር፤ ከገዢው ፓርቲ ጋር ለመደራደርም ሆነ ሁሉን አቀፍ የባለድርሻወች የሽግግር ሂደት ለማምጣት፤ በብቃትም  ለመሳተፍ ካሁኑ የጋራ አጀንዳ መቅረፅና ህብረት መፍጠር የግድ ያስፋልጋል። ይህ ካልሆነ አሁንም እንዳለፈው ጊዜ ተፎካካሪ ሀይሎች ህዝቡን በደካማ ፓርቲዎች ዙሪያ ከከፋፈሉት ሁሉን አቀፍ፤ ዲሞክራሳዊ፤ ነፃና ፍትሃዊ የሽግግር ሥራአት ለማምጣት ከባድ ከምሆኑም በላይ አሁን የተፈጠረውን የለውጥ ተንሳሽነት ውጤት አልባ ሊያደርገው ይችላል።

ስለሆነም በአገር ቤትና በውጭ የሚገኙ የፖለቲካና የማህበረ-ስባአዊ ስብስቦች ጥቃቅን ልይነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱና የጋራ አቋምና የትግል መሣሪያ የሚሆን ትብብር እንዲፈጥሩ ሁሉም ለውጥ ፈላጊ ወገኖች (በነፍስ-ወከፍም ሆነ በቡድን ደረጃ ) ግፊት ማድረግ አለባቸው፤

በአገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር የምንገኝ ወገኖች ለለውጥ ፈላጊ የፖለቲካና የማህበረሰባአዊ ስብስቦች ማንኛውንም ወቅታዊ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል፤ “ትብብር” በበኩሉ በዚህ ረገድ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ ቃል ይገባል፤ በተለይም የአሜሪካ ሁለተኛው ምክር ቤት SR 168ን እንዲያሳልፍ አስፈላጊውን ግፊት በተለያዩ ዘዴዎች (ቴሌኮንፊርንስ፤ ፓልቶክ፤ ኢሜል) ያደርጋል፤

የህወሀትን እኩይ ተግባሮችና ዕቅዶች ባለ ዓቅሙ ሁሉ ለህዝብ ይፋ ያወጣል፤

በመጨረሻም፤ ትግላችን ከህወሀት ዘረኛ መሪዎች ጋር እንጂ ከሠፊው የትግራይ ህዝብ ጋር እንዳልሆነ በተገኘው አጋጣሚና የህዝብ መገናኛ ግልፅ ያደርጋል።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ትግል ከዘረኝነትና ከጭቆና ትላቀቃለች!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *