ፖሊስ ከወትሮው በተለየ ሆን ብሎ እንዝላልነት አሳይቷል በሚል ክስ እየቀረበበት ነው። ባለፈው ቅዳሜ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመግደል መሞከሩን ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሃላፊዎች በቁጥትር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነው አዲስ ሹመት የተሰጠው።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ናቸው ሹመቱን የሰጡት። በዚም መሰረት ሜጀር ጀነራል ደግፌ በዲን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።
Related stories Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho
Powered by Inline Related Posts
በተጨማሪም ረዳት ፖሊስ ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ አና አቶ ዘልአለም መንግስቴን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አድርገው ሾመዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የአዲስ አበባ እና የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን የመሾም ስልጣን አላቸው።