በአገራችን ያለው የፖለቲካ ትኩሳት የህወሓትን ህልውና አደጋ ላይ ያስገባ የትግራይን ህዝብ ስጋት ከምን ግዜም በላይ የከፋ ደረጃ ላይ ያደረሰ ሆንዋል። ከዚህ የተነሳ በርካታ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኞች በአሁኑ ወቅት ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አብቅቶለታል ዳግም አገግሞ ወሳኝ አገራዊ ሚና አይኖረውም እርስ በርሱ ግጭት ውስጥ ይገባል ሲሉ ይተነትናሉ።

ይህ ትንበያ መሰረት ይኖረው ይሆን? የትግራይ ህዝብና ህወሓትስ ምን አማራጭ መንገድ ይኖራቸዋል?

የትግራይ ህዝብ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ባደረገው ተጋድሎ አገራችን መለወጥ ችላለች። የህዝቦችን እኩልነት ተረጋግጥዋል። ጽኑ የኢኮኖሚ መሰረት ተገንብትዋል። ይህንን ሁሉ ድል ያጎናጸፈን ህዝብ ገና የድሉ ፍሬ ሳይደርቅ በቀይ ብእር ተሰርዝዋል። ዳግም እንዳይመለስ ወደ ቀድሞ የነበረበት የጦርነት ታሪክ እንድመለስ ባድመ ወልቃይት አላማጣና ኮረም የቤት ስራዎች ተዘጋጅቶውለታል።

ይሁንና ወደ የውድቀት አዘቅጥ ከመግባት ራሱን ለማዱንና ወሳኝ ሚናው ቀጣይነት እንዱኖረው ለማድረግ የተለያዩ አማራጮች እንዳሉ መገንዘብ ይቻላል።

ህወሓት ከደረሰበት ከበባ ለመውጣትና የከዱትን ብአዲንና ኦህዴድን አገር ከማፍረስና የትግራይን ህዝብ ከመግደል ከማፈናቀልና ከማሽማቀቅ እንዱታደቡ ለማድረግ በአሁኑ ወቅት ባይችልም ቢያንስ ያለውን ጽንፈኛ አዝማሚያና ክፍተት ማሳየት የሚችልበት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ነድፎ መስራትና ሳይበላ እንደበላ ሳያልፍለት እንዳለፈለትና ልዩ ተጠቃሚ እንደነበር በማስመሰል በሌሎች ህዝቦች ዘንድ በውሸት ፕሮፖጋንዳ የሰረጸውን የተዛባና የትግራይ ህዝብን የማይገልጽ ስያሜ በትክክል እንዲታወቅ ማድረግ።

ይህንን ለማሳካት ደግሞ ከየ አካባቢው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችንና እንደ ስዩም ተሾመ የመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተዋናዮችን ሙሁራንንና ወጣቶችን መጋበዝና ህዝቡን እንዱያዩ ማድረግ። የትግራይ ህዝብ በምን የኑሮ ደረጃ ላይ እንዳል እንዲያዩ በማድረግ ሳይደላው የደላው በማስመሰል የተነዛውን መርዝ ማብረስ።

ኦህዴድም ሆነ ብአዲን የሞቱለትን የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነትና የፌዴራል ስርዓት እንዲጠብቁና የትግራይ ህዝብ የተሰዋለት ዓላማ ክማኮላሸት እንዲታቀቡ ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ ማሳመን። ይህ ከሆነ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በሰላም የሚኖርበትን መንገድ ማረጋገጥና አንድነትን አጠናክሮ መቀጠልያስችላል። በዚህ ሂደት የኢህዲግ አጋር ድርጅቶች በኢህአዴግ እንዲታቀፉ በማድረግ የጽንፈኛውንና የትምክህተኛውን ያልተቀደሰ ጋብቻ ማምከን።

ይህ ካልሆነ ከኤርትራ መንግስት ጋር ሰላም ለመፍጠር ያስችላል ተብሎ የተጀመረው የመንግስት ጥረት በመደገፍ ዳር ማድረስና ሁለቱን ህዝቦች በማቀራረብ አንድነት መፍጠር። ከዚህ ጎንለጎን አፋርን ሶማሊያን በመያዝ አንቀጵ 39 ተጠቅሞ በመገንጠል ጠንካራ አገር መመስረት።

በአሁኑ ወቅት ብዙ ህዝብ ያላቸው ከአማራና ከኦሮሞ ህዝቦች በስተቀር ሌሎቹን ህዝቦች እኩል የማያሳትፍና አሃዳዊ መንግስትን የሚያጠናክር በመሆኑ ከሁለቱ ብሄሮች ውጭ ያሉ ህዝቦችን የሚደፈጥጥ በመሆኑ አንድ ላይ ሆኖ ለመታገል የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር።

ይህንን ለማድረግ መጀመሪያ በውጭና በውስጥ ያሉ የትግራይ ተወላጆችን በአንድ አላማ ማሰለፍ። በህወሓትና በዓረና መካከል ያለውን ልዩነት መፍታት ቀደም ሲል በማንኛውም ምክንያት ከድርጅቱ የወጡ ታጋዮች ጋር መወያየትና ህዝብን ለማዳን ሲባል መስማማትና በአንድ ሆኖ መስራት። ይህ ከሆነ ህወሓት አበቃለት የሚለው ትንበያ የቀን ቅዥት ሆኖ ይቀራል። የትግራይ ህዝብም ለሌላ እንግልት ሳይዳረግ ኑሮውን በሰላም ይመራል።

ካሳ በርጫ 07-02-18 አይጋ ፎረም

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *