የቀድሞው የህወሃት መሪ  ዶክተር አረጋዊ በርኸ ከፓርቲያቸው አመራሮች ጋር በመሆን ዛሬ አዲስ አበባ ሲገቡ በሰጡት መግለጫ የትግራይ ህዝብ ለውጡን እንደሚደግፍና ቀደም ሲል ተጭኖበት ያለውን ቀንበር ለማላቀቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። 

በስደት ህወሃትን ተለይተው በሆላንድ ይኖሩ የነበሩት  ዶክተር አረጋዊ  አምርረው በመለስ ዜናዊ የሚመራውን ህወሃት ይኮንኑና ይታገሉ ነበር። በተለያዩ ወቅቶችም ህወሃት ይሰራቸው የነበሩትን ወንጀሎች ከበረሃ ጀመሮ በማጋለጥ ይታወቃሉ። ዛሬ መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተቀብለው ወደ አገር ቤት ሲገቡ እንዳስታወቁት የትግራይ ህዝብ ላይ ያለውን ስጋት ከሌሎች የህብረተሰብ አካላት ጋር በመሆን ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ዶክተር አረጋዊ በርኸና የሚመሩት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ልኡክ አቶ መኮንን ዘለለው እና አቶ ግደይ ዘርአጽዮን አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ለልኡኩ አቀባበል ያደረጉት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ፥ አሁንም በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ መንግስት ጥሪውን ያቀርበባል ብለዋል።

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሀም፥ ጠቅላይ ሚኒስትድ ዶክተር አብይ ያቀረቡን ጥሪ በመቀበል ወደ ሀገር መግባታቸውን አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት መንግስት የጀመራቸውን ስራዎች እንደሚደግፉም አስታውቀዋል።

ፎቶ ፋና

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *