የሶማሊ ክልል ሊቀመንበርና የኦሮሚያ አቻቸው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን መመሪያ ተከትሎ በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ስምምነት መፈጸማቸው ተሰማ። ግጭት በላባቸው ስፍራዎች ሁሉ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት ለሚያከናውነው የሰላምና ማረጋጋት ተግባር አብረው ለመስራት ቃል ገብተዋል።

ዛሬ ኢቲቪ እንዳስታወቀው የሁለቱ ክልል መሪዎች በደረሱት ስምምነት መሰረት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላት የማረጋጋትና የችግሩ ምንጭ ናቸው የተባሉ አካላትን የማጣራት ስራ እየሰሩ ነው። ከዚሁ ጎን ለጎን የህዝብ ለህዝብ ውይይት በአስቸኳይ እንዲጀመር ስራ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

ቀደም ሲል ተመሳሳይ ውስኔ የተደረሰ ቢሆንም የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የሚያደርሰውን ጥቃት እንዲያቆም አልተደረገም። በክልሉ በሚደርስ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲጠየቁ ሁኔታዎች እየተመቻቹባቸው ያሉት የክልሉ መሪ ለውጡን እንደሚደግፉና አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

ከሶማሌ ክልል አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የኦሮሚያ ተወላጆች መፈናቀላቸውና ከፍተኛ ስቃይ እንደደረሰባቸው የሚታውቀስ ነው። በአወዳይ የሶማሊ ክልል ተወላጅ በሆኑ ላይም ጥቃት መሰንዘሩ አይዘነጋም።ይሁን እንጂ ከኦሮሚያ ወገን ጥቃቱ ሲቆም በሶማሌ ልዩ ሃይል በኩል የሚሰነዘረርው ጥቃት ሊያስቆመው የሚችል ሃይል ማጣቱ ጉዳዩ ማን ከጀርባ ሆኖ ነው የሚመራው የሚል ጥያቄ አስነስቶ ቆይቷል። ሰሞኑን ይፋ በሆነ የዚዲዮ መልዕክት የስማሌ ክልል መሪ አብዲ የቀድሞው የደህንነት አሃላፊ ጫና እንደሚያደርጉባቸው ይፋ አድርገው ነበር።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *