ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ 456 ሰዎችን የያዘ የህዝብ ለህዝብ ቡድን ነገ ወደ አስመራ ያቀናል። የህዝብ ለህዝብ ቡድኑ ወደ አስመራ የሚጓዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በነገው እለት በሚጀምረው የአስመራ በረራው መሆኑም ታውቋል።

የህዝብ ለህዝብ ቡድኑ ወስጥም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶች እና ለዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ተለያይተው በኢትዮጵያ ሲኖሩ የነበሩ ኤርትራውያን ይገኙበታል ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ሲበርም ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጋር ሳይገናኙ የቆዩ በርካታ ኤርትራውያንን ይዞ እንደሚመጣም ታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሀምሌ 1 2010 ዓ.ም ጀምሮ በኤርትራ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነበር የአየር ትራንስፖርት እና ሌሎች አገልግሎቶች በሁለቱ ሀገራት መካከል እንደሚጀር ከስምምነት የተደረሰው።

ከስምምነቱ ውስጥም ኤምባሲ መልሶ መክፈት፣ የአየር ትራንስፖርት እና ሀገራቱ በስልክ እንዲገናኙ ከስምምነት መደረሱ አይዘመጋም። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ በነገው እለት በይፋ የሚጀምር ይሆናል።

ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት መልሶ የተጀመረ ሲሆን፥ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የኤርትራ ኤምበባሲ መከፈቱም ይታወሳል። ኢትዮጵያም ኤምባሲዋን በአስመራ ለመክፈት ዝግጅት ላይ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Fana.b

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *