የሕዝብ አመጽ መካረሩን ተከትሎ ኢህአዴግ ውስጥ የተነሱ የለውጥ ሃይሎች ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የታየውን ለውጥና ለውጡን ተከትሎ እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች ያልተደሰቱ ክፍሎች ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ቅሬታቸውን ሊደብቁ በማይችሉበት ደረጃ ሲያስተጋቡ ቆይተዋል።

በሰፊ የህዝብ ንቅናቄና የአደባባይ ድጋፍ እውቅና ያገኘውን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር ለመቦርቦር እየተወሰደ ያለው ትልቁና ዋናው ስትራቴጂ ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው ስለመሆኑ ሚስጥሮች ይፋ ሆነዋል። ስትራቴጂውም የአብይ አስተዳደር አገሪቱን ወደ ቀውስ እየመራት መሆኑንን በወትዋቾችና በአካል በመገኘት የማሳመን ስራ አጠናክሮ መስራት ነው።

የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ሄደው ጠ/ሚ/ር ዓቢይን ለማውረድ ያቀረቡት ጥያቄ ድራማ” በሚል ርዕስ ጎልጉል የተሰኘ የድረ ገጽ ጋዜጣ በጁን ፪፰ እንዳተተው ዶከተር አብይና ካቢኔያቸውን በኩዴታ መልክ ለማሰወገድ ከህወሃት በኩል ለአሜሪካ ካፈተኛ ባለስልጣናት ቀርቧል። የተሰጠው መልስ ግን ” አይሆንም፤ አታስቡት” የሚል ነበር። ዛጎል ባላት መረጃ የህወሃት ከፍተኛ ሰዎች ከነባር ወዳጆቻቸው ጋር አሜሪካ ተገናኝተዋል። በተለይም ፔንታጎን ውስጥ ያሉ ወዳጆች እውሳኔ ደረጃ ላይ ባይደርሱም ግን አድምጠዋቸዋል።

በሌላ በኩል ከአዲሱ አመራር ወደ ስልጣን መምጣት ጋር ተያይዞ በቤኒሻንጉል፣ በሃዋሳ፣በሶማሌ ክልል እና በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል የተነሳው ግጭት፣ ግድያ፣ ረብሻና መፈናቀል ከጀርባው ከፍተኛ በጀት የሚፈስበት፣ አገሪቱ በምስራቅ አፍሪቃ ላይ አደጋ ያንዣበበ ቀውስ ውስጥ መሆኗን ለማሳየት የተደረገ መሆኑንን በይፋም ባይሆን በገደምዳሜ ሲገለጽ ሰንብቷል።

ይህው ውስጥ ውስጡን እየጋመ ያለው የውክልና ረብሻ ጭንቀት ቢፈጥርም በአብዛኛው የሚሰጠው የህዝብ አስተያየት ይህ ለውጥ ከቶውንም ቢሆን ሊደናቀፍ እንደማይችል ነው። ለለውጡ ሂደት ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የድህንነት ተቋምና ፖሊስ እንዲሁም የመንግስት ሚዲያዎች ሙሉ በሙሉ ለውጡን ተቀብለዋል። በተለይም መከላከያ ሰራዊትና ደህንነቱ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙሉ ድጋፍ እንዳለው ጠቁመዋል።

በዚህ መነሻና በበለጸጉት ድጋፍ ሰጪ አካላት ዘንድ ድጋፍ ያጣው የኩዴታ አካሄድ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል ሆኖ በመገኘቱ ሰላምን በማደፍረስ የሰላም አስከባሪ ሆኖ ወደ እርካብ ለመመለስ እቅድ መያዙን ነው ጎልጉል ያመላከተው። ጎልጉል ብቻ ሳይሆን ብሮንዊን ብሩቶን የተባሉት በአትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር ” ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!” ሲሉ በእንግሊዘኛ ባሰፈሩትና ጎልጉል ወደ አማርኛ በመለሰው ጥልቅ ጽሁፋቸው ውስጥ ይህንኑ ጉዳይ የሚያጠናክር መረጃ ይሰጣሉ።

ይህ ዘመቻ ሰሞኑን ቅርጹን ቀይሮ አለም አቀፍ ይዘት እንዲኖረው እየተደረገ ነው። ይህ በእጅ አዙር እንደሚከናወን የሚነገርለት ትርምስ አገሪቱን ወደ ከፋ ቀውስ እየከተታት መሆኑንን የዓለም ዓቀፍ ሃይላይ እንዲያውቁት፣ ስጋቱን እንዲጋሩት፣ ከዚያም አልፈው ህዝብ ድጋፍ እየሰጠው ያለውን አዲሱን አስተዳደር ተጠያቂና የአገሩን ሰላም ማስጠበቅ እንዳቃተው ተደርጎ የምሳየቱ ስራ በተመረጡ ስትራቴጂዎች እየተካሄዱ እንደሆን ጉዳዩን የሚከታተሉ አካሎች ይጠቁማሉ።

እነዚሁ ክፍሎች እንዳሉት ይህ ቅስቀሳ ዶከተር አብይ ባጭር ጊዜ የገነቡትን ታላቅ ስም እና ስኬት በማጠልሸት የታሰበውን የመንግስት ግልበጣ ፈቃድ ለማግኘት ነው። ዓላማው ይህ ቢሆንም ጉዳዩ ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዳሉት የለውጥ አራማጅ መሪን እንጂ ለውጥን መግደል አይቻልም እንዲሉ ጉዳዩ በሁሉም ወገን ቀላል እንዳልሆነ ያመላክታሉ።

የⶃማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የሰጡት መረጃ በህግ የሚያስጠይቅ ሆኖ ሳለ መንግስት ዝምታ መመረጡ አግባብ እንዳልሆነ የሚጠቁሙት ክፍሎች፣ ለውጡ የተፈራበትና የለውጡን ዋና ዓላም ህዝብን ኢላማ ያደረገ እንደሆነ በማስመሰል የሚሰበከውን ስብከት የሚያመክን ስራ በወጉ አለመሰራቱንም ይናገራሉ።

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *