የሶማሌ ክልልን ለአስር ዓመት እንዲመሩ ልዩ ፈቃድ ተሰጥቶት የነበረው አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ራሱን እንዳያጠፋ፣ ሌሎች የወንጀሎቹ አቀናባሪዎች፣ አጋሮሽ፣ አማካሪዎች፣ የጥቅም ተጋሪዎች፣ እንዳሻው እንዲገል፣ ሴቶችን እንዲፈር፣ ብር እንዲረጭ፣ እንዲመለክ፣ ህዝብና አገር ላይ መረን እንዲወጣ የፈቀዱ አካልት እንዳያስገድሉት ጥንቃቄ እንደሚደረገለት ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለዛጎል ጠቆሙ።

ይህ እንዲሆን ልዩ መመሪያ የተላለፈው አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር እንዲውል ኦፐሬሽን ከተጀመረበት ሰዓት ጀምሮ የከረረ ተቃውሞ የሚያሰሙ ወገኖች በመኖራቸው፣ አቶ አብዲ እና አብረዋቸው በወንጀል ተሳታፊ የሆኑ የስራ ባልደረቦቹ አስፈላጊውን መረጃ ሁሉ በቢሯቸው ሆነው በመዘርገፋቸው ለጥንቃቄ በሚል ነው።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ላለፉት አስርት ዓመታት በሶማሌ ህዝብ ላይ እጅግ የሚዘገንን ወንጀል የፈጸመው አብዲ፣ በሺህ የሚቆተሩ ዜጎችን ገሏል። ሴት እህቶችን ደፍሮ እንዲደፈሩ አድርጓል፣ በሺህ የሚቆጠሩ ወገንችን አስሯል። በመኪና ሙሉ ገነዘብ እየጫነ መንገድ ላይ ይረጫል። አንድ ህግ ባለበት አገር ውስጥ የመንግስት በጀትን እያወጣ ያድላል። እንዲህ የሚያደርገው በአደባባይ ቢሆንም ጠያቂ አልነበረውም። ይልቁኑም ከፌደራል በጥቅም የተያያዙትና ሁሌ ብር የሚወስዱ ወገኖች እንደነበሩ ከክልሉ ተወላጆች መካከል አቶ አብዱል ዋሳህ የሚባሉ ምሁር በኢቲቪ በኩል እየተደነቁ ሲናገሩ ታይተዋል። እሳቸው እንዳሉት ይህ ሰው እንዴት ክልሉን ሊመራ እንደቻለ በራሱ አነጋጋሪ ነው። በወንጀል ሲጨማለቅ ለምን ዝም ተባለ ? እንዴት ዝም ተባለ? የሚለው ጉዳይ ጉዳዩን ወደሁዋላ መለስ ብሎ እንዲታይ ያደርገዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

የተለያዩ ምስክሮች እንዳሉትና አብዲ ራሱ በሰጠው ዝርዝር መረጃ ከጀርባና ከፊት ሆነው ሲያጅቡት የነበሩት የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ከመጠየቅ እንደማያመልጡ እኚሁ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑት የዜናው ምንጭ ተናግረዋል። የሂወማን ራይትስ ዎች በክልሉ የሚሰራውን ግፍና ኢሰብአዊ ድርጊት ሲያጣጥል የነበረው የአቶ መለስ መንግስት፣ በአቶ ሃይለማሪያምም ከተተካ በሁዋላ የሚፈጸመውን ግፍና በደል ማመን ተስኖት ነበር።

እንደ መሪ ሳይሆን በአንድ ትልቅ ግቢ ውስጥ እንደሚኖር ቃልቻ እንዳሻው ሲፋንን የነበረው አብዲ ከፍርድ ሂደቱ በፊት ህይወቱ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳይደርስ ክትትል የሚደረግበት ምክንያት በርካታ መሆኑን ያመለከቱት ምንጭ፣ ሌሎችም በቁጥጥር ስር የዋሉ አጋሮቹ እንዳሉ አክለው ገልጸዋል። እንደ ዜናው ከሆነ መንግስት የፍርድ ሂደቱን ህዝብ በቀጥታ ስርጭት እንዲያየው ሃሳብ አለ። አብዛኛው ህዝብ የፍርድ ሂደቱ ክፍት ሆኖ እንደ ሌሎች ዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ለሌሎች ሁሉ ማስተማሪያነት እንዲያገለግል ፍላጎት አለው።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ከዝርፊያ፣ ከተራ ወንጀል፣ ከመብት ጥሰትና ቡድኖችን በማስተባበር በንብረትና በሃይማኖት ተቋማት ላይ ካደረሰው ጥፋት በተጨማሪ  በአገር ክህደት ወንጀልም እንደሚከሰስና ይህንን ክህደት እንዲፈጽም የመከሩ፣ የረዱ፣ ያስተባበሩ፣ በቅርብ ሆነው ተሳትፎ ያደረጉ ሁሉ በተመሳሳይ ክስ ሊመሰረትባቸው እንደሚገባ የህግ ባለሙያዎች ሃሳብ እየሰጡ መሆኑም ታውቋል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *