በሻሸመኔ በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የደረሰው የመቁሰልና የሞት አደጋ ምንም ዓይነት እውነት በሌለው የፈጠራ መረጃ መሆኑንን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አለማየሁ እጅጉ ለአገር ውስጥ መገናኛ ተናገሩ። ያልተጣራና ያልተጨበጡ መረጃዎችን በማህበራዊ ገጾች ማሰራጨት ወዳልተፈለገ ድምዳሜ ሊያደርስ እንደሚችል አሳስበዋል።

ኮሚሽነርሩ እንዳሉት አቶ ጀዋር መሐመድን ለመቀበል በሻሸመኔ እጅግ ቁጥሩ ሰፊ የሆነ ህዝብ ተሰብስቦ ነበር። ይሁን እንጂ ዓላማቸውና ማንነታቸው እስካሁን በውል ያልታወቁ/ በምርመራ ላይ ያሉ/ ክፍሎች ቦንብ ተገኘ በሚል ባስበሱት ግርግር አደጋው ሊደርስ እንደቻለ አመላክተዋል። ንብረትነቱ የፖሊስ የሆነና በጸጥታ ስራ ላይ የተሰማራ ተሽከርካሪ መንደዱንም ገልጸዋል።

በሕዝብ ጥቆማና በፖሊስ ክትትል ለአደጋው መንስኤ ናቸው የተባሉ መቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስታወቁት ኮሚሽነሩ፣ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን ገልጸዋል። አያይዘውም ለጽጥታ ሲባል የተዘጉ መንገዶች መከፈታቸውንና ሁከቱ መብረዱን ተናግረዋል። ሕዝብ እንደ ወትሮው ሁሉ መረጃ እየሰጠ መሆኑንና ምርመራው ሲጠናቀቅ ይፋ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ምንጩ ያልታወቀና ዓላማው ግልጽ ያልሆነ የፈጠራ አተራማሽ መረጃዎች ማስተላለፍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተለመደ መጥቷል። ማህበራዊ ሚዲያውም ይህንኑ ያልነጠረ መረጃ በማሰራጨት እጅግ ከፈተኛ ውድመትና ሰብአዊ ቀውስ እያስከተሉ ነው። በማርቆስ አቶ በረከት ታይተዋል በሚል ንብረት ወድሟል። ሰዎች ተጎድተዋል። ከተማዋ ተንጣለች። ይህ የቅርብ ጊዜ ሲሆን፣ በማህበራዊ ሚዲያ በማይታወቅ ስምና አድራሻ የተመዘገቡ ሰዎች በተለያየ ወቅት ምንጫቸው ምን እንደሆነ የማይታወቅ መረጃ ሲያራግቡ እንደነበርና ይህ ተግባር አሁንም እንደቀጠል ነው።

ከትናንት በስቲያ ለአገራቸው ምድር የበቁትን ፓትሪያርክ ለመጎብኘት ወደ መኖሪያቸው ያመሩት ዶክተር አብይ ” እስከንለወጥ ድረስ” ሲሉ የገለጹት ጉዳይ ቢኖር ይህ ያልተጨበጠ መረጃ ዝም ብሎ የማሰራጨት ችግር መፍትሄ የሚያሻው ጉዳይ ነው። 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *