የነበሩትና ተወልደው ያደጉበት የቦንጋ ህዝብ በፊርማ አስደግፎ በተደጋጋሚ ባቀረበው ቅሬታ እስከ 1998 ዓ.ም. ድረስ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው የቆዩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን የሚያስታውሱ ” ሰውየው የት ገቡ” ሲሉ ይጠይቃሉ። የዶክተር አብይን ዝምታም አይቀበሉትም።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሃላፊ በነበሩበት ወቅትና ከዛ በፊት አቶ ብርሃኑ በበርካታ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችና በከፍተኛ ሙስና የምጠረጠሩ በመሆናቸው ተወልደው ያደጉበት ክልል ህዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያቀርብ ነበር። በተለይም በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን እሳቸው የሚመሩትና የሚያዙበት እስር ቤት እንደነበር የሚጠቁም ክፍሎች ” አሁን በሰብአዊ መብት ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ዘገባና አሳዛኝ ታሪክ የሚያሰማው ኢቲቪ ስለምን ይህንን ጉዳይ አይመለከተውም” ሲሉ ይጠይቃሉ።

በቦንጋ ሲካሄድ ከነበረው እጅግ አሳዛኝ የሰብአዊ መብት ጥሰት በተጨማሪ እድሜ ጠገብ የሆኑ የቡና ደኖች በሙስና እየተመነጠሩ ጣውላ ሲቸበቸብ የነበረው በሳቸው አማካይነት መሆኑንንም ያነሳሉ። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት አቶ ብርሃኑ የፈጸሙትን ወንጀል የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ጠንቅቆ ያወቀዋል። ቀደም ሲል እሳቸውን ወደ ህግ ማቅረብ የማይቻለው በነበራቸው የጥቅም ትሥሥር መሆኑ ቢታወቅም አሁን ግን ዝምታ መመረጡ ክልሉንና አዲሱን አስተዳደር ትዝብት ላይ የሚጥል ነው።

የዶክተር አብይ አስተዳደረም ሆነ የቀድሞው የድርጅት ባልደረባቸው አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቂ መረጃ እንዳላቸው የሚጠቁሙት ክፍሎች፣ በርካታ ፍትህ ፈላጊዎች ቦንጋና ሃዲያ ላይ ያተኮረ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ሃላፊነታቸው ወቅትና በተላያዩ ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የሰሯቸው ጉዳዮች ሊመረመሩ እንደሚገባ ያመለክታሉ።

በሸራተን ባለቤትና አጫፋሪዎች ትዕዛዝ በሎቤድ የጭነት መኪና ሊሞዚን ተጭኖ፣ የወጥ ቤት ሰራተኛ አቅርቦ፣ ውስኪ እንደውሃ የፈሰሰበትና ሽንጣም መኪኖችን አላስገባ በማለቱ የምስኪኖች ቤት ለብርሃኑ አዴሎ ወንድም ሰርግ ሲባል መፍረሱን የሚያወሱት እነዚህ ክፍሎች ” እባካችሁን ቦንጋ ኑና ይህንን ጉድ ይፋ አድርጉ” ሲሉ ለመንግስት መገናኛዎች ጥሪ አቅርበዋል። 

አቶ ብርሃኑ በስልክ በፍርድ ቤት ውሳኔ ጣልቃ በመግባት መመሪያ የሚሰጡ መሆናቸውንም የሚያስታውሱ ክፍሎች ፣ ከ” ባለሃብቱ እና ከወቅቱ ቀዳማይ እመቤት ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሸሽጓቸው ቆይቷል። አሁን ግን ወቅቱ የፈትህ ነውና ትክረት እንሻለን” ብለዋል። እነዚሁ ክፍሎች በተለያዩ መገናኛዎች በተደጋጋሚ ጉዳዩን መንግስት ምላሽ እስኪሰጥበት ድረስ አጠንክረው እንደሚሰሩበት አመልክተዋል።

በተለያዩ ወቅቶች አገር ውስጥ የሚታተሙ ሚዲያዎች በተለይም ሪፖርተር በማስረጃ የተደገፈ መረጃ ሲያወጣ መቆየቱ የሚታወስ ነው። ለአብነት ይህ ተጽፎ ነበር።

አቶ ብርሃኑ አዴሎ በቀረበባቸው ቅሬታ በድጋሚ ተነሱሪፖርተር – አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከአዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ኃላፊነታቸው በሕዝብ ቅሬታ ምክንያት እንዲነሱ ተደረገ፡፡ አቶ ብርሃኑ በሕዝብ ቅሬታ ምክንያት ከኃላፊነታቸው ሲነሱ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ላለፉት ስምንት ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ብርሃኑ፣ ታኅሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጻፈ ደብዳቤ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈው ደብዳቤ አቶ ብርሃኑ ከኃላፊነታቸው የሚነሱበትን ምክንያት ባያብራራም፣ ከታኅሳስ 24 ቀን ጀምሮ መነሳታቸውን ይገልጻል፡፡ ተቋሙን በተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩም የተቋሙ የፓተንት ክፍል ዳይሬክተር አቶ ግርማ በጅጋ ተሹመዋል፡፡ አቶ ብርሃኑ በአሠራር ችግሮች ከሠራተኞች ቅሬታዎች ይነሱባቸው እንደነበር፣ ከተቋሙ ደንበኞች ማለትም የንግድ ምልክት የሚያወጡ ወይም ምልክቶቻቸው እንዲከበሩ የሚፈልጉ የንግድ ተቋማትና ግለሰቦች ቅሬታ ይቀርብባቸው እንደነበር ምንጮች አስረድተዋል፡፡ እነዚህ ቅሬታዎች በቀጥታ ለተወካዮች ምክር ቤት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት እንደቀረቡ ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ችግሮቹን የሚያጣራ ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካይነት ተዋቅሮ የማጣራት ተግባራት ሲከናወኑ እንደነበሩ የሚያስታውሱት ምንጮች፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ደሚቱ አንቢሳና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩ አቶ አሚን አብዱልቃድር ከአጣሪ ኮሚቴ አባላቱ መካከል እንደነበሩም ገልጸው፣ ከኃላፊነት የተነሱትም ከዚሁ ጋር በተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አቶ ብርሃኑ እስከ 1998 ዓ.ም. ድረስ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ነበሩ፡፡ በወቅቱ ከተወለዱበት የደቡብ ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት በአቶ ብርሃኑ ላይ የተፈራረሙትን የቅሬታ አቤቱታ (ፔቲሽን) ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ማስገባታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የተቋቋመ አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበባቸው ሪፖርት ከካቢኔ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸውና ከኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲነሱ መደረጉም አይዘነጋም፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ አቶ ብርሃኑ አዴሎን ለማነጋገር በተደጋጋሚ የግል ስልካቸው ላይ በመደወል ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *