ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ቻይና ያመራሉ። ዋናው ጉዟቸው ከፈረንጆቹ መስከረም 3 እስከ 4 ድረስ በቤጂንግ በሚካሄደው በቻይና አፍሪካ ፎረም ላይ እንደሚሳተፉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚሉት ግን ቀጣይ ኢንቨስትመንትና እዳን በተመለከት ውይይት ይደረጋል።

ከፎረሙ ጎን ለጎንም ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪ ኪያንግ ጋር ተገናኝተው ወይይት እንደሚያደርጉ ከጽፈህት ቤታቸው የወጣው መረጃ ያመለክታል። 

ለዛጎል መረጃ የሰጡ እንዳሉት በአገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ የተጋዘውን ገንዘብና ሃብት አስመለክቶ ቻይና መረጃ በመስጠት፣ ከድርጊቱ ጀርባ ያሉትን አካላት አስመልክቶ መረጃ እንድተሰጥ በተለያየ መልኩ የቀረበውን ጥያቄ አስመክቶ አዎንታዊ ምላሽ እንድትሰጥ፣ አንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ የተጫነውን እዳ አስመልክቶ የፊት ለፊት ምክክር ይደረጋል። ይህንኑ አስመልክቶ ስምምነት ይደረሳል የሚል እምነት አለ፤

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *