ስለ አብዲ ኢሌ አስተያየት የሚሰጡ የክልሉ ተወላጆች ነገራቸው መካከል ” እንዴት ይህ ሰው ለዚህ ሃላፊነት በቃ” በሚል ግርምታቸውን ያስቀምጣሉ። ዋናው ጥያቄ ሊሆን የሚገባው እንዲህ ያለ ወሮ በላ ለዓመታት በወንጀል ሲጨማለቅ ለምን ዝም ተባለ የሚለው ጉዳይ ደግሞ ዋናው ጉዳይ ነው።

ይህ አፉን ያለ ልክ የሚከፍት ዱርዬ ማንና እነማንን ተማምኖ የንጹሃንን ደም ሲጠጣ፣ የአገር ሃብት ሲዘርፍና ሲያካፍል፣ ገንዘብ በጭነት መኪና ጭኖ ሲረጭ፣ ሲያስር፣ ሲገርፍ፣ አንድ ጉድጓድ ሰዎችን ሲቀብር፣ ሴቶችን ሲደፍር፣ …. እንደኖረ ህዝብ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ፍትሃዊ ፍርድም ይፈልጋል።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

ይህ ድንቁርና የሰፈረበት ዱርዬ እንዲህ ልዩ ሃይል ተደራጅቶለት የንጹሃንን ደም ሲጠጣ አደባባይ በገሃድ ሆኖ ሳለ ዝም መባሉ፣ የሰው ልጆችን ከአውሬ ጋር እያሰረ ሲያሰቃይ፣ አይዞህ እየተባለ እንዴት ሲሸለምና ሲሞገስ እንደኖረ ማወቅና ፍርድን ማግኘት የህዝብ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የመንግስትም ግዳጅ ነው።

ህጻናትንና አረጋውያንን በገፍ በጭነት መኪና እየጫነ በየበረሃው ሲደፋ የኖረ ወሮ በላ እስከዛሬ ከሰራው ግፍ የሚመጥን ቅጣት ሲቀበል፣ የፍርድ ሂደቱ በቀጥታ ለህዝብ እንዲተላለፍ፣ ህዝብ በቀጥታ እንዲያየው ሊሆን እንደሚገባ ህዝብ ያምናል። ይፈልጋል። እናም ዛሬ በይፋ በቁጥትር ስር የዋለው ወሮበላና አለቆቹ በገሃድ የፍርድ ሂደት ሲዳኙ ማየት የህዝብ ሁሉ ፍላጎት ስለሆነ ይንንን አለማድረግ አይቻልም።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ከዚህ ወሮ በላ በተጨማሪ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባላትም ከሱ እኩል ህዝብ እንዲማርባቸው በይፋ ፍርድ ቤት ሲዳኙ ማየት የግድ ነው።

  1. አቶ አብዲጀማል ቀሎንቢ – የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግና ፍትህ ቢሮ ኃላፊ
  2. ወይዘሮ ራህማ መሀሙድ – የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
  3. አቶ ዴቅ አብዱላሂ – የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብራሂም መሀመድ
  4. አቶ ዴቅ አብዱላሂ – የውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
  5. አቶ ኢብራሂም መሀሙድ ሙባሪክ – የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና
  6. አቶ ኡመር አብዲ – የኢሶህዴፓ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ናቸው፡።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *