በኮሚሽኑ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የፋይናስ ወንጀሎች ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር ደበበ ድጋፉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በቁጥጥር ስር የዋለው ገንዘብም ጭማሪ አሳይቷል።

እስከአሁን ከ6 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ፣ 56 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ ከ4 ሺህ በላይ የእንግሊዝ ፓውንድና የሌሎች ሰባት ሀገራት መገበያያ ገንዘቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በተካሄደው ዘመቻ በቁጥጥር ስር የዋሉት የተጠርጣሪዎች ቁጥም 40 የደረሰ ሲሆን፥ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ዘመቻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የጥቁር ገበያውን በዋናነት የሚመሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በትናንተናው እለት ፋና ይህንን ዘግቦ ነበር።

ከ5 ሚሊየን ብር በላይና በርካታ የውጭ ሀገር ገንዘቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ከ5 ሚሊየን ብር በላይና በርካታ የውጭ ሀገር ገንዘቦች በቁጥጥር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር የዋሉት ገንዘቦችም 5 ሚሊየን 466 ሺህ ብር 632 ብር፣ 4 ሺህ 16 እንግሊዝ ፓውንድ፣ 56 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ 2 ሺህ 70 ዩሮ፣ 6 ሺህ 505 ድሪሃም ናቸው።

እንዲሁም በርካታ የደቡብ አፍሪካ ራንድ፣ የቱርክ ሊሬ፣ ጅቡቲና የሶማሌ ሽልግ እንዲሁም የማሊ ፍራንክ መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

በኮሚሽኑ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የፋይናስ ወንጀሎች ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር ደበበ ድጋፍ፥ ገንዘቦቹን በመያዝ በጋንዲ ሆስፒታል፣ ኢትዮጵያ ሆቴልና ሌሎች አካባቢዎች በህገወጥ መንገድ ሲዘረዝሩ እንደተያዙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቀዋል።

ኤፍቢሲ እንደዘገበው ምክትል ዳይሬክተሩ፥ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከ30 ሱቆች በላይ ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር በመተባበር እንዲታሸጉ መደረጉን ገልፀዋል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *